የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ‘በግንባራቸው ላይ ምልክት አድርግ’
    የይሖዋ ንጹሕ አምልኮ መልሶ ተቋቋመ!
    • 7, 8. የማጥፊያ መሣሪያ የያዙት ሰዎች ተልእኳቸውን የሚፈጽሙት እንዴት ነው? በመጨረሻስ ምን ሆነ?

      7 ታዲያ የማጥፊያ መሣሪያ የያዙት ስድስት ሰዎች ተልእኳቸውን የሚፈጽሙት እንዴት ነው? ሕዝቅኤል ይሖዋ ለእነዚህ ሰዎች የሰጠውን መመሪያ ሰምቷል፤ ሰዎቹ የቀለም ቀንድ የያዘውን ሰው ተከትለው እንዲሄዱና በግንባራቸው ላይ ምልክት ከተደረገባቸው ሰዎች በስተቀር ሁሉንም ሰው እንዲገድሉ ታዘዋል። ይሖዋ ‘ከመቅደሴ ጀምሩ’ የሚል መመሪያ ሰጥቷቸዋል። (ሕዝ. 9:6) የማጥፊያ መሣሪያ የያዙት ሰዎች ሥራቸውን የሚጀምሩት በኢየሩሳሌም እምብርት ከሚገኘውና የይሖዋን ሞገስ ካጣው ቤተ መቅደስ ነው። በመጀመሪያ የተገደሉት ‘በቤተ መቅደሱ ፊት ለፊት የነበሩት ሽማግሌዎች’ ማለትም በቤተ መቅደሱ ውስጥ ለሐሰት አማልክት ያጥኑ የነበሩት ሰባዎቹ የእስራኤል ሽማግሌዎች ናቸው።—ሕዝ. 8:11, 12፤ 9:6

  • ‘በግንባራቸው ላይ ምልክት አድርግ’
    የይሖዋ ንጹሕ አምልኮ መልሶ ተቋቋመ!
    • 9, 10. ከኢየሩሳሌም ጥፋት ከዳኑት ታማኝ ሰዎች መካከል እነማን ይገኙበታል? እነዚህን ሰዎች በተመለከተስ ምን ማለት ይቻላል?

      9 ሁለተኛ ዜና መዋዕል 36:17-20⁠ን አንብብ። የሕዝቅኤል ትንቢት ፍጻሜውን ያገኘው በ607 ዓ.ዓ. የባቢሎን ሠራዊት ኢየሩሳሌምንና ቤተ መቅደሷን ባጠፋበት ጊዜ ነበር። ይሖዋ ‘በእጁ እንዳለ ጽዋ’ የሆኑትን ባቢሎናውያንን ተጠቅሞ በከዳተኛይቱ ኢየሩሳሌም ላይ ቁጣውን በማፍሰስ የቅጣት ፍርዱን አስፈጸመ። (ኤር. 51:7) ጥፋቱ ጅምላ ጨራሽ ነበር? በፍጹም። ሕዝቅኤል ባየው ራእይ ላይ በባቢሎናውያን የማይገደሉ ሰዎች እንደሚኖሩ ተገልጿል።—ዘፍ. 18:22-33፤ 2 ጴጥ. 2:9

      10 ሬካባውያንን፣ ኢትዮጵያዊው ኤቤድሜሌክን፣ ነቢዩ ኤርምያስንና ጸሐፊው ባሮክን ጨምሮ የተወሰኑ ታማኝ ሰዎች ከጥፋቱ ተርፈዋል። (ኤር. 35:1-19፤ 39:15-18፤ 45:1-5) እነዚህ ሰዎች በኢየሩሳሌም ውስጥ ‘እየተፈጸሙ ባሉት አስጸያፊ ነገሮች ሁሉ ያዝኑና ይቃትቱ’ እንደነበር ሕዝቅኤል ያየው ራእይ ይጠቁማል። (ሕዝ. 9:4) ገና ጥፋቱ ከመድረሱ በፊት፣ ለክፋት ያላቸውን ልባዊ ጥላቻና ለንጹሕ አምልኮ ያላቸውን ታማኝነት እንዳሳዩ ምንም ጥያቄ የለውም፤ በዚህም ምክንያት ከጥፋቱ ለመትረፍ በቅተዋል።

      11. የማጥፊያ መሣሪያ የያዙት ስድስት ሰዎችና የጸሐፊ የቀለም ቀንድ የያዘው ሰው እነማንን ይወክላሉ?

      11 እነዚህ ታማኝ ሰዎች ከጥፋት ለመትረፍ የሚያስችል ምልክት ቃል በቃል ተደርጎባቸው ነበር? ሕዝቅኤልም ሆነ ሌላ ማንም ነቢይ በኢየሩሳሌም ከተማ እየተዘዋወረ በታማኝ ሰዎች ግንባር ላይ ምልክት እንዳደረገ የሚገልጽ ታሪክ የለም። በመሆኑም የሕዝቅኤል ትንቢታዊ ራእይ የሚያሳየው ከሰብዓዊ ዓይን እይታ ውጭ በሆነው በመንፈሳዊው ዓለም ይከናወን የነበረውን ነገር መሆን አለበት። በራእዩ ላይ የታዩት የማጥፊያ መሣሪያ የያዙ ስድስት ሰዎችና የጸሐፊ የቀለም ቀንድ የያዘው ሰው፣ ምንጊዜም የይሖዋን ፈቃድ ለመፈጸም በተጠንቀቅ የሚጠብቁትን ታማኝ መንፈሳዊ ፍጡራን ይወክላሉ። (መዝ. 103:20, 21) ይሖዋ በከሃዲዋ ኢየሩሳሌም ላይ የተወሰደውን የፍርድ እርምጃ ለመምራት በመላእክቱ ተጠቅሞ እንደነበረ አያጠራጥርም። መላእክቱ ፍርዱ ጅምላ ጨራሽ ሳይሆን ጥፋት የሚገባቸውን ብቻ መርጦ የሚያጠፋ እንዲሆን አድርገዋል፤ በዚህ መንገድ ከጥፋቱ በሚተርፉት ሰዎች ግንባር ላይ ምልክት እንዳደረጉ ሊቆጠር ይችላል።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ