-
“አንድ እረኛ . . . አስነሳለሁ”የይሖዋ ንጹሕ አምልኮ መልሶ ተቋቋመ!
-
-
የመጀመሪያው ታላቅ ንስር የባቢሎንን ንጉሥ ናቡከደነጾርን ያመለክታል (አንቀጽ 6ን ተመልከት)
6. የእንቆቅልሹን ፍቺ ተናገር።
6 የእንቆቅልሹ ፍቺ ምንድን ነው? (ሕዝቅኤል 17:11-15ን አንብብ።) በ617 ዓ.ዓ. የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነጾር (የመጀመሪያው “ታላቅ ንስር”) ኢየሩሳሌምን ከበበ። ከዚያም የይሁዳ ንጉሥ የነበረውን ንጉሥ ዮአኪንን (‘አናት ላይ ያለውን ቀንበጥ’) ከዙፋኑ አንስቶ ወደ ባቢሎን (‘የነጋዴዎች ከተማ’) ወሰደው። ናቡከደነጾር ሴዴቅያስን (ከምድሪቱ ንጉሣዊ ዘር አንዱን) ወስዶ በኢየሩሳሌም በሚገኘው ዙፋን ላይ አስቀመጠው። አዲሱ የይሁዳ ንጉሥ ታማኝ ገባር ንጉሥ ለመሆን በአምላክ ስም እንዲምል ተደርጎ ነበር። (2 ዜና 36:13) ሴዴቅያስ ግን መሐላውን ንቆ በባቢሎን ንጉሥ ላይ በማመፅ የግብፁ ንጉሥ ፈርዖን (ሁለተኛው “ታላቅ ንስር”) ወታደራዊ እርዳታ እንዲሰጠው ጠየቀ፤ ሆኖም ያሰበው አልተሳካለትም። ይሖዋ ሴዴቅያስ መሐላውን በማፍረስ የፈጸመውን ክህደት አውግዟል። (ሕዝ. 17:16-21) በመጨረሻም ሴዴቅያስ ከዙፋኑ እንዲወርድ የተደረገ ሲሆን በባቢሎን እስር ቤት ውስጥ እያለ ሞተ።—ኤር. 52:6-11
-
-
ስለ መሲሑ የሚናገር ትንቢት—የሚያምር የአርዘ ሊባኖስ ዛፍየይሖዋ ንጹሕ አምልኮ መልሶ ተቋቋመ!
-
-
2. ናቡከደነጾር ሴዴቅያስን ኢየሩሳሌም በሚገኘው ዙፋን ላይ አስቀመጠው
-