-
ስለ መሲሑ የሚናገር ትንቢት—የሚያምር የአርዘ ሊባኖስ ዛፍየይሖዋ ንጹሕ አምልኮ መልሶ ተቋቋመ!
-
-
5. በኢየሱስ ንጉሣዊ አገዛዝ ጥላ ሥር ታዛዥ የሆኑ የሰው ልጆች ያለምንም ስጋት ተረጋግተው ይኖራሉ
-
-
“አንድ እረኛ . . . አስነሳለሁ”የይሖዋ ንጹሕ አምልኮ መልሶ ተቋቋመ!
-
-
10 ትንቢቱ ፍጻሜውን ያገኘው እንዴት ነው? ይሖዋ ልጁን ኢየሱስ ክርስቶስን ከዳዊት ንጉሣዊ ዘር (‘ከረጅሙ አርዘ ሊባኖስ’) ላይ ቀጥፎ በሰማያዊቷ የጽዮን ተራራ (‘ረጅምና ግዙፍ በሆነው ተራራ’) ላይ ተከለው። (መዝ. 2:6፤ ኤር. 23:5፤ ራእይ 14:1) በዚህ መንገድ ይሖዋ፣ በጠላቶቹ ዘንድ “ከሰዎች ሁሉ የተናቀ” ተደርጎ የተቆጠረውን ልጁን “የአባቱን የዳዊትን ዙፋን” በመስጠት ከፍ ከፍ አድርጎታል። (ዳን. 4:17፤ ሉቃስ 1:32, 33) መሲሐዊው ንጉሥ ኢየሱስ ክርስቶስ እንደ ታላቅ አርዘ ሊባኖስ በመላው ምድር ላይ በመንሰራፋት ለተገዢዎቹ በሙሉ የበረከት ምንጭ ይሆንላቸዋል። በእርግጥም ልንተማመንበት የሚገባው ገዢ እሱ ነው። በኢየሱስ ንጉሣዊ አገዛዝ ጥላ ሥር በመላው ምድር የሚኖሩ ታዛዥ የሰው ልጆች “መከራ ይደርስብኛል የሚል ስጋት” ሳያድርባቸው ‘ተረጋግተው ይኖራሉ።’—ምሳሌ 1:33
-