-
“አምላክ የገለጠልኝን ራእዮች ማየት ጀመርኩ”የይሖዋ ንጹሕ አምልኮ መልሶ ተቋቋመ!
-
-
15. ሕዝቅኤል ስለ መንኮራኩሮቹ መጠንና አሠራር ምን ገልጿል?
15 የመንኮራኩሮቹ ግዝፈት ሕዝቅኤልን በጣም አስደምሞታል። “የመንኮራኩሮቹም ጠርዝ እጅግ ረጅም ከመሆኑ የተነሳ የሚያስፈራ ነበር” በማለት ጽፏል። ሕዝቅኤል ቁመታቸው እስከ ሰማይ የሚደርሰውን የሚያብረቀርቁ ግዙፍ መንኮራኩሮች ለማየት ወደ ላይ ሲያንጋጥጥ በዓይነ ሕሊናህ ይታይህ። ሕዝቅኤል “የአራቱም መንኮራኩሮች ጠርዝ ዙሪያውን በዓይኖች የተሞላ ነበር” የሚል የሚያስገርም ተጨማሪ መግለጫ ሰጥቷል። ከሁሉ በላይ የሚያስደንቀው ግን የመንኮራኩሮቹ እንግዳ አሠራር ሳይሆን አይቀርም። ሕዝቅኤል “መልካቸውና አሠራራቸው ሲታይ በአንድ መንኮራኩር ውስጥ በጎን በኩል ሌላ መንኮራኩር የተሰካ ይመስላል” የሚል ማብራሪያ ይሰጠናል። ይህ ምን ማለት ነው?
-
-
“አምላክ የገለጠልኝን ራእዮች ማየት ጀመርኩ”የይሖዋ ንጹሕ አምልኮ መልሶ ተቋቋመ!
-
-
17 ይህን የሚያክል ረጅም ቁመት ያላቸው መንኮራኩሮች አንዴ እንኳ ሲሽከረከሩ ሰፊ ርቀት ሊሸፍኑ ይችላሉ። በዚህ ላይ ራእዩ ሠረገላው እንደ መብረቅ ባለ ፍጥነት እንደሚጓዝ ይገልጻል! (ሕዝ. 1:14) ከዚህም በላይ ይህ ሠረገላ በአራት አቅጣጫ መጓዝ የሚችሉ መንኮራኩሮች ያሉት መሆኑ ሰብዓዊ መሐንዲሶች ሊያልሙት እንኳ የማይችሉት ቅልጥፍና እንዳለው ያመለክታል። ሠረገላው ፍጥነቱን መቀነስ ወይም መዞር ሳያስፈልገው በቅጽበት አቅጣጫውን መቀየር ይችላል! እንዲህ ያለ እንቅስቃሴ የሚያደርገው ግን እንዲሁ በጭፍን አይደለም። የመንኮራኩሮቹ ጠርዝ በዓይኖች የተሞላ መሆኑ ይህ ሠረገላ በሁሉም አቅጣጫ በዙሪያው ያለውን እያንዳንዱን ነገር እንደሚያይ ይጠቁማል።
መንኮራኩሮቹ እጅግ ግዙፍ ከመሆናቸውም ሌላ በአስገራሚ ፍጥነት ይንቀሳቀሱ ነበር (አንቀጽ 17ን ተመልከት)
-