የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ይሖዋ የፍትሕ መጓደልን ይጠላል
    መጠበቂያ ግንብ—2012 | ነሐሴ 1
    • “ሰው ሰውን ለመጕዳት ገዥ የሚሆንበት ጊዜ አለ።” (መክብብ 8:9) ይህ ሐሳብ የተጻፈው 3,000 ከሚያህሉ ዓመታት በፊት ቢሆንም የምንኖርበት ዓለም ያለበትን ሁኔታ ጥሩ አድርጎ የሚገልጽ ነው። የሚኖሩት የትም ይሁን የት፣ ሁሉም ሰዎች ሥልጣናቸውን አላግባብ የመጠቀም ዝንባሌ አላቸው። ሥልጣናቸውን አላግባብ የሚጠቀሙ ሰዎች ብዙውን ጊዜ የጥቃታቸው ሰለባ የሚያደርጉት ምንም አቅም የሌላቸውንና ምስኪኖችን ነው። ታዲያ ይሖዋ እንዲህ ስላለው የፍትሕ መጓደል ምን ይሰማዋል? ሕዝቅኤል 22:6, 7, 31 ላይ ያለውን ሐሳብ በመመርመር የዚህን ጥያቄ መልስ ማግኘት እንችላለን።​—ጥቅሱን አንብብ።

  • ይሖዋ የፍትሕ መጓደልን ይጠላል
    መጠበቂያ ግንብ—2012 | ነሐሴ 1
    • ሕዝቅኤል ያወገዘው መሪዎቹን ብቻ ሳይሆን የእነሱን ፈለግ ተከትለው የይሖዋን ሕግ ያልታዘዙትን ሌሎች ሰዎች ጭምር እንደሆነ ግልጽ ነው። ሕዝቅኤል አክሎ ሲናገር “አባቶችና እናቶች በውስጥሽ ተዋረዱ” ብሏል። (ቁጥር 7) ሕዝቡ፣ ይሖዋ ለወላጆች የሰጣቸውን ቦታ በማቃለል ለብሔሩ ሕልውና እንደ ምሰሶ የሆነው የቤተሰብ ተቋም እንዲፈራርስ አድርገዋል።​—ዘፀአት 20:12

      ብልሹ ምግባር ያላቸው ሰዎች በሕዝቡ መካከል የነበሩ ረዳት የሌላቸው ምስኪኖችን ይበዘብዙ ነበር። እነዚህ ሰዎች የሚፈጽሙት እያንዳንዱ መጥፎ ድርጊት አምላክ ለእስራኤላውያን የሰጣቸውን ፍቅር የተንጸባረቀበት ሕግ እንዳቃለሉ የሚያሳይ ነው። ለምሳሌ ያህል፣ እስራኤላውያን በመካከላቸው ለሚኖሩ የባዕድ አገር ሰዎች ለየት ያለ አሳቢነት እንዲያሳዩ የአምላክ ሕግ ያዝዝ ነበር። (ዘፀአት 22:21፤ 23:9፤ ዘሌዋውያን 19:33, 34) ይሁን እንጂ ሕዝቡ ‘መጻተኞችን ይጨቁኑ’ ነበር።​—ቁጥር 7

      ከዚህም ሌላ ሕዝቡ ረዳት የሌላቸውን ማለትም ‘ድኻ አደጎችንና መበለቶችን’ ያንገላቱ ነበር። (ቁጥር 7) ይሁንና ይሖዋ ወላጅ ወይም የትዳር ጓደኛ የሞተባቸው ሰዎች ለሚያስፈልጓቸው ነገሮች ለየት ያለ ትኩረት ይሰጣል። አምላክ፣ ረዳት የሌላቸውን ልጆችና መበለቶችን በሚበድሉ ሰዎች ላይ ራሱ እርምጃ እንደሚወስድ ቃል ገብቷል።​—ዘፀአት 22:22-24

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ