የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • የአንባቢያን ጥያቄዎች
    መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2016 | መጋቢት
    • አንደኛ፣ አጥንቶቹ “ደርቀዋል” ወይም “በጣም ደርቀው ነበር” ተብለው እንደተገለጹ ልብ ማለት ያስፈልጋል። (ሕዝ. 37:2, 11) አጥንት ብቻ መገኘቱ ሰዎቹ ከሞቱ በጣም ረጅም ጊዜ እንዳለፋቸው የሚጠቁም ነው። ሁለተኛ፣ እነዚህ አጥንቶች መልሰው ሕያው የሆኑት በአንድ ጊዜ ሳይሆን ቀስ በቀስ እንደሆነ ተገልጿል። መጀመሪያ ላይ “የሚንኮሻኮሽ ድምፅ ተሰማ፤ አጥንቶቹም እርስ በርስ መገጣጠም ጀመሩ።” ከዚያም “ጅማትና ሥጋ” ለበሱ። ቀጥሎም አጥንቶቹ፣ ጅማቶቹና ሥጋው በቆዳ ተሸፈኑ። በኋላም “[እስትንፋስ] ገባባቸው፤ እነሱም ሕያው” ሆኑ። በመጨረሻም ይሖዋ ዳግመኛ ሕያው የሆኑትን ሰዎች በምድራቸው ላይ አሰፈራቸው። እነዚህ ነገሮች ጊዜ እንደሚወስዱ ግልጽ ነው።—ሕዝ. 37:7-10, 14

  • የአንባቢያን ጥያቄዎች
    መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2016 | መጋቢት
    • ስለ ሁለተኛው ነጥብ ማለትም በራእዩ ላይ መልሶ ስለ መቋቋም የሚገልጸው ሐሳብ የተፈጸመው መቼና እንዴት ነበር? የአምላክ ሕዝቦች በመንፈሳዊ ያንሰራሩት ቀስ በቀስ ነበር። ራእዩ “የሚንኮሻኮሽ ድምፅ” እንደተሰማ ይናገራል፤ ይህ ድምፅ መሰማት የጀመረው ደግሞ ከፍጻሜው ዘመን በፊት ባሉት ጥቂት መቶ ዓመታት ውስጥ ነበር። በእነዚያ ዓመታት የሐሰት ትምህርት ከፍተኛ ተሰሚነት የነበረው ቢሆንም አንዳንድ ታማኝ ሰዎች አቅማቸው እስከፈቀደ ድረስ ለእውነተኛው አምልኮ ጥብቅና ቆመዋል። አንዳንዶቹ ተራው ሕዝብ በሚጠቀምበት ቋንቋ መጽሐፍ ቅዱስን ለመተርጎም ጥረት አድርገዋል። ሌሎች ደግሞ የአምላክን ቃል ሲያነቡ ያገኟቸውን እውነቶች አውጀዋል።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ