-
የአንባቢያን ጥያቄዎችመጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2016 | መጋቢት
-
-
አንደኛ፣ አጥንቶቹ “ደርቀዋል” ወይም “በጣም ደርቀው ነበር” ተብለው እንደተገለጹ ልብ ማለት ያስፈልጋል። (ሕዝ. 37:2, 11) አጥንት ብቻ መገኘቱ ሰዎቹ ከሞቱ በጣም ረጅም ጊዜ እንዳለፋቸው የሚጠቁም ነው። ሁለተኛ፣ እነዚህ አጥንቶች መልሰው ሕያው የሆኑት በአንድ ጊዜ ሳይሆን ቀስ በቀስ እንደሆነ ተገልጿል። መጀመሪያ ላይ “የሚንኮሻኮሽ ድምፅ ተሰማ፤ አጥንቶቹም እርስ በርስ መገጣጠም ጀመሩ።” ከዚያም “ጅማትና ሥጋ” ለበሱ። ቀጥሎም አጥንቶቹ፣ ጅማቶቹና ሥጋው በቆዳ ተሸፈኑ። በኋላም “[እስትንፋስ] ገባባቸው፤ እነሱም ሕያው” ሆኑ። በመጨረሻም ይሖዋ ዳግመኛ ሕያው የሆኑትን ሰዎች በምድራቸው ላይ አሰፈራቸው። እነዚህ ነገሮች ጊዜ እንደሚወስዱ ግልጽ ነው።—ሕዝ. 37:7-10, 14
-
-
የአንባቢያን ጥያቄዎችመጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2016 | መጋቢት
-
-
ከዚያም በ1800ዎቹ መገባደጃ ላይ ቻርልስ ቴዝ ራስልና አጋሮቹ የመጽሐፍ ቅዱስ እውነት እንዲታወቅ በቅንዓት እንቅስቃሴ ማድረግ ጀመሩ። መንፈሳዊው አጽም በምሳሌያዊ ሁኔታ ሥጋና ቆዳ መልበስ የጀመረ ያህል ነበር። ቅን ልብ ያላቸው ሰዎች በጽዮን መጠበቂያ ግንብ እና በሌሎች ጽሑፎች አማካኝነት መንፈሳዊ እውነቶችን ማወቅ ችለዋል። በኋላ ደግሞ በ1914 መታየት የጀመረው “የፍጥረት ፎቶ ድራማ” እንዲሁም በ1917 የወጣው ያለቀለት ሚስጥር (እንግሊዝኛ) የተባለው መጽሐፍም ሆነ ሌሎች መሣሪያዎች የአምላክን ሕዝቦች መንፈሳዊነት አጠናክረዋል። በመጨረሻም በ1919 የአምላክ ሕዝቦች በመንፈሳዊ ሕያው ሆኑ፤ ከዚያም በአዲሱ መንፈሳዊ ርስታቸው ሰፈሩ። ውሎ አድሮ፣ ምድራዊ ተስፋ ያላቸው ክርስቲያኖች ከእነዚህ ቅቡዓን ቀሪዎች ጋር ተቀላቀሉ፤ “እጅግ ታላቅ ሠራዊትም ሆኑ።”—ሕዝ. 37:10፤ ዘካ. 8:20-23b
-