የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • “ሕያው ትሆናላችሁ”
    የይሖዋ ንጹሕ አምልኮ መልሶ ተቋቋመ!
    • 12 ከጊዜ በኋላ ደግሞ ቻርልስ ቴዝ ራስልና የሥራ ባልደረቦቹ የመጽሐፍ ቅዱስን እውነቶች ለመግለጥ በቅንዓት እንቅስቃሴ ማድረግ ሲጀምሩ አጥንቶቹ “ጅማትና ሥጋ” ለበሱ። የጽዮን መጠበቂያ ግንብ እና ሌሎች ጽሑፎች ቅን ልብ ያላቸው ሰዎች መንፈሳዊ እውነቶችን እንዲያገኙ ረድተዋል፤ በዚህ የተነሳ እነዚህ ሰዎችም ከአምላክ ቅቡዓን አገልጋዮች ጋር ተቀላቀሉ። በ1900ዎቹ ዓመታት መጀመሪያ ላይ “የፍጥረት ፎቶ ድራማ” የተባለው ፊልም፣ ያለቀለት ሚስጥር የተባለው መጽሐፍና ሌሎችም መሣሪያዎች መዘጋጀታቸው ቅቡዓን ክርስቲያኖችን ይበልጥ አጠናክሯቸዋል። ከዚያ ብዙም ሳይቆይ አምላክ ሕዝቦቹን ‘በእግራቸው እንዲቆሙ’ ለማድረግ እርምጃ ወሰደ። (ሕዝ. 37:10) ይህ የሆነው መቼና እንዴት ነው? በጥንቷ ባቢሎን የተከናወኑትን ሁኔታዎች መመልከታችን የዚህን ጥያቄ መልስ ለማግኘት ይረዳናል።

      “ሕያው ሆነው በእግራቸው ቆሙ”

      13. (ሀ) በሕዝቅኤል 37:10, 14 ላይ የሚገኘው ትንቢት ከ537 ዓ.ዓ. ጀምሮ ፍጻሜውን ያገኘው እንዴት ነው? (ለ) ከአሥሩ ነገድ ሕዝቦች መካከል አንዳንዶቹ ወደ እስራኤል ምድር እንደተመለሱ የሚጠቁሙት የትኞቹ ጥቅሶች ናቸው?

      13 በባቢሎን የነበሩት አይሁዳውያን ከ537 ዓ.ዓ. ጀምሮ ይህ ራእይ ፍጻሜውን ሲያገኝ ተመልክተዋል። እንዴት? ይሖዋ ከግዞት ነፃ ወጥተው ወደ እስራኤል ምድር እንዲመለሱ በማድረግ ‘ሕያው ሆነው በእግራቸው እንዲቆሙ’ አስችሏቸዋል። ቁጥራቸው 42,360 የሚሆን እስራኤላውያንና 7,000 ገደማ የሚሆኑ እስራኤላዊ ያልሆኑ ሰዎች ኢየሩሳሌምንና ቤተ መቅደሷን መልሰው ለመገንባት እንዲሁም በእስራኤል ምድር ለመኖር ባቢሎንን ለቀው ወጡ። (ዕዝራ 1:1-4፤ 2:64, 65፤ ሕዝ. 37:14) ከ70 ዓመታት ገደማ በኋላ ደግሞ 1,750 የሚያክሉ ግዞተኞች ከዕዝራ ጋር ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ። (ዕዝራ 8:1-20) ስለዚህ በድምሩ ከ44,000 በላይ አይሁዳውያን ወደ አገራቸው ተመልሰዋል፤ በእርግጥም “እጅግ ታላቅ ሠራዊት” ሆነዋል። (ሕዝ. 37:10) በተጨማሪም አሦራውያን በስምንተኛው መቶ ዘመን ዓ.ዓ. ከአሥሩ ነገድ መንግሥት በግዞት የወሰዷቸው ሰዎች ዘር የሆኑ እስራኤላውያንም፣ ቤተ መቅደሱን መልሶ በመገንባቱ ሥራ የበኩላቸውን ድርሻ ለማበርከት ወደ እስራኤል ምድር ተመልሰዋል።—1 ዜና 9:3፤ ዕዝራ 6:17፤ ኤር. 33:7፤ ሕዝ. 36:10

      ከሁለተኛው መቶ ዘመን ዓ.ም. እስከ 1919 የነበሩት ቅቡዓን ክርስቲያኖች።

      ሣጥን 10ለ፦ ‘በደረቁት አጥንቶች’ እና ‘በሁለቱ ምሥክሮች’ መካከል ያለው ዝምድና ምንድን ነው?

      14. (ሀ) በሕዝቅኤል 37:24 ላይ የሚገኘው ሐሳብ ትንቢቱ በላቀ ሁኔታ ፍጻሜውን የሚያገኝበትን ጊዜ እንድናውቅ የሚረዳን እንዴት ነው? (ለ) በ1919 ምን ተከናወነ? (“‘በደረቁት አጥንቶች’ እና ‘በሁለቱ ምሥክሮች’ መካከል ያለው ዝምድና ምንድን ነው?” የሚለውን ሣጥን ተመልከት።)

      14 ይህ የሕዝቅኤል ትንቢት በላቀ ሁኔታ ፍጻሜውን ያገኘው እንዴት ነው? ይሖዋ ከዚህ ጋር ተዛማጅ በሆነ ሌላ ትንቢት ላይ ለሕዝቅኤል እንደገለጠለት፣ ስለ መልሶ መቋቋም የሚገልጸው ይህ ትንቢት በላቀ ሁኔታ ፍጻሜውን የሚያገኘው ታላቁ ዳዊት ኢየሱስ ክርስቶስ ንጉሥ ሆኖ መግዛት ከጀመረ በኋላ ነው።b (ሕዝ. 37:24) በእርግጥም በ1919 ይሖዋ ለሕዝቦቹ መንፈሱን ሰጥቷቸዋል። በዚህም የተነሳ “ሕያው ሆነው” ከታላቂቱ ባቢሎን ግዞት ነፃ ወጥተዋል። (ኢሳ. 66:8) ከዚያ በኋላ ይሖዋ “በምድራቸው” ማለትም በመንፈሳዊው ገነት ውስጥ እንዲሰፍሩ ፈቅዶላቸዋል። ታዲያ በዘመናችን ያሉት የይሖዋ ሕዝቦች “ታላቅ ሠራዊት” የሆኑት እንዴት ነው?

      በዕድሜ የገፉ አንድ ወንድም በሕዝቅኤል መጽሐፍ ውስጥ ባነበቡት ነገር ላይ ሲያሰላስሉ።

      ሣጥን 10ሐ፦ ተመልሰን በእግራችን እንድንቆም የሚያስችል እርዳታ

      15, 16. (ሀ) በዘመናችን ያሉት የይሖዋ ሕዝቦች “ታላቅ ሠራዊት” የሆኑት እንዴት ነው? (ለ) ይህ የሕዝቅኤል ትንቢት በሕይወታችን ውስጥ የሚያጋጥሙንን ፈታኝ ሁኔታዎች እንድንቋቋም የሚረዳን እንዴት ነው? (“ተመልሰን በእግራችን እንድንቆም የሚያስችል እርዳታ” የሚለውን ሣጥን ተመልከት።)

      15 ክርስቶስ በ1919 ታማኝና ልባም ባሪያን ከሾመ በኋላ ብዙም ሳይቆይ የአምላክ አገልጋዮች፣ ከግዞት በተመለሱት እስራኤላውያን መካከል ነቢይ ሆኖ ያገለግል የነበረው ዘካርያስ የተናገረው የሚከተለው ትንቢት ሲፈጸም ተመልክተዋል፦ “ሕዝቦችና የብዙ ከተማ ነዋሪዎች በእርግጥ ይመጣሉ።” ነቢዩ፣ ይሖዋን የሚፈልጉትን እነዚህን ሰዎች “ከብሔራት ቋንቋዎች ሁሉ የተውጣጡ አሥር ሰዎች” በማለት ገልጿቸዋል። እነዚህ ሰዎች “አንድን አይሁዳዊ” ማለትም መንፈሳዊ እስራኤላውያንን አጥብቀው በመያዝ “አምላክ ከእናንተ ጋር መሆኑን ስለሰማን ከእናንተ ጋር እንሄዳለን” ይላሉ።—ዘካ. 8:20-23

      16 በዛሬው ጊዜ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎችን ያቀፈ “እጅግ ታላቅ ሠራዊት” አለ። ይህ ታላቅ ሠራዊት በዋነኝነት መንፈሳዊ እስራኤላውያንን (ቅቡዓን ቀሪዎችን)፣ በተዘዋዋሪ ደግሞ ‘አሥሩን ሰዎች’ (ሌሎች በጎችን) ያቀፈ ነው። (ሕዝ. 37:10) ቁጥሩ እየጨመረ በሚሄደው በዚህ ሠራዊት ውስጥ የታቀፍን የክርስቶስ ወታደሮች እንደመሆናችን መጠን ንጉሣችንን ኢየሱስን በቅርበት እየተከተልን ከፊታችን የሚጠብቀንን በረከት ለማግኘት እንገሰግሳለን።—መዝ. 37:29፤ ሕዝ. 37:24፤ ፊልጵ. 2:25፤ 1 ተሰ. 4:16, 17

  • ንጹሕ አምልኮ ቀስ በቀስ መልሶ ተቋቋመ
    የይሖዋ ንጹሕ አምልኮ መልሶ ተቋቋመ!
      • ናታን ኖር፣ ጆሴፍ ራዘርፎርድና ሃይደን ኮቪንግተን።

        “ሕያው ሆነው በእግራቸው ቆሙ”

        የይሖዋ ሕዝቦች በ1919 ‘ሕያው ከሆኑ’ በኋላ የስብከት ሥራቸውን አጧጧፉ

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ