-
“አንድ ብሔር አደርጋቸዋለሁ”የይሖዋ ንጹሕ አምልኮ መልሶ ተቋቋመ!
-
-
3. (ሀ) “ለይሁዳ” ተብሎ የተጻፈበት በትር ምን ያመለክታል? (ለ) አሥሩን ነገድ ያቀፈውን መንግሥት የሚያመለክተው በትር በኤፍሬም ስም የተጠራው ለምንድን ነው?
3 ይሖዋ ሕዝቅኤልን ሁለት በትሮች እንዲወስድና በአንዱ ላይ “ለይሁዳ” በሌላው ላይ ደግሞ “ለዮሴፍ ይኸውም ኤፍሬምን ለሚወክለው በትር” ብሎ እንዲጽፍ አዘዘው። (ሕዝቅኤል 37:15, 16ን አንብብ።) እነዚህ ሁለት በትሮች ምን ያመለክታሉ? “ለይሁዳ” ተብሎ የተጻፈበት በትር የይሁዳንና የቢንያምን ነገድ ያቀፈውን ባለሁለት ነገድ መንግሥት ያመለክታል። ከይሁዳ ነገድ የሆኑ ነገሥታት በሁለቱ ነገዶች ላይ ይገዙ ነበር። ካህናቱም ኢየሩሳሌም በሚገኘው ቤተ መቅደስ ውስጥ ያገለግሉ ስለነበር የክህነት ሥርዓቱም ከሁለቱ ነገዶች ጋር የቅርብ ትስስር ነበረው። (2 ዜና 11:13, 14፤ 34:30) በመሆኑም የይሁዳ መንግሥት በዳዊት መስመር በኩል የሚመጣውን ንግሥናና በሌዊ ነገድ ሥር የነበረውን የክህነት አገልግሎት ያቀፈ ነበር። ‘ኤፍሬምን የሚወክለው በትር’ አሥሩን ነገዶች ያቀፈውን የእስራኤል መንግሥት ያመለክታል። ይህ በትር በኤፍሬም ስም የተጠራው ለምንድን ነው? አሥሩን ነገዶች ያቀፈው መንግሥት የመጀመሪያ ንጉሥ የኤፍሬም ነገድ ተወላጅ የሆነው ኢዮርብዓም ነበር። ከጊዜ በኋላ ደግሞ የኤፍሬም ነገድ በእስራኤል ውስጥ ኃያል ነገድ ሆነ። (ዘዳ. 33:17፤ 1 ነገ. 11:26) አሥሩን ነገድ ያቀፈው የእስራኤል መንግሥት በዳዊት መስመር በኩል የሚመጣውን ንግሥናም ሆነ በሌዊ ነገድ ሥር የነበረውን የክህነት አገልግሎት እንደማያካትት ልብ በል።
-
-
የሁለቱ በትሮች አንድ መሆንየይሖዋ ንጹሕ አምልኮ መልሶ ተቋቋመ!
-
-
ሣጥን 12ሀ
የሁለቱ በትሮች አንድ መሆን
ይሖዋ ሕዝቅኤልን በአንደኛው በትር ላይ “ለይሁዳ” በሁለተኛው ላይ ደግሞ “ለዮሴፍ ይኸውም ኤፍሬምን ለሚወክለው በትር” ብሎ እንዲጽፍ ነገረው።
“ለይሁዳ”
በጥንት ዘመን
ሁለቱን ነገዶች ያቀፈው የይሁዳ መንግሥት
በዘመናችን
ቅቡዓን ክርስቲያኖች
“ለዮሴፍ ይኸውም ኤፍሬምን ለሚወክለው በትር”
በጥንት ዘመን
አሥሩን ነገዶች ያቀፈው የእስራኤል መንግሥት
በዘመናችን
ሌሎች በጎች
-