-
“አንድ ብሔር አደርጋቸዋለሁ”የይሖዋ ንጹሕ አምልኮ መልሶ ተቋቋመ!
-
-
4. ሕዝቅኤል ቀጥሎ በበትሮቹ ላይ ያደረገው ነገር ምን ያመለክታል? (በመግቢያው ላይ ያለውን ሥዕል ተመልከት።)
4 ቀጥሎም ሕዝቅኤል “አንድ በትር ይሆኑ ዘንድ” ሁለቱን በትሮች አንድ ላይ እንዲይዛቸው ተነገረው። ግዞተኞቹ በጭንቀት ተውጠው ሕዝቅኤልን እየተመለከቱት “የእነዚህ ነገሮች ትርጉም ምን እንደሆነ አትነግረንም?” ሲሉ ጠየቁት። እሱም ትንቢታዊ ድራማው ይሖዋ ራሱ የሚያደርገውን ነገር የሚያመለክት እንደሆነ ነገራቸው። ይሖዋ ሁለቱን በትሮች በተመለከተ እንዲህ ሲል ተናግሯል፦ “አንድ በትርም አደርጋቸዋለሁ፤ እነሱም በእጄ ላይ አንድ በትር ይሆናሉ።”—ሕዝ. 37:17-19
5. ሕዝቅኤል በድራማ መልክ ያሳየው ትንቢት ትርጉሙ ምንድን ነው? (“የሁለቱ በትሮች አንድ መሆን” የሚለውን ሣጥን ተመልከት።)
5 ከዚያም ይሖዋ ሁለቱ በትሮች አንድ መሆናቸው ምን ትርጉም እንዳለው ገለጸ። (ሕዝቅኤል 37:21, 22ን አንብብ።) ሁለቱን ነገድ ካቀፈው የይሁዳ መንግሥት የተውጣጡ ግዞተኞችና አሥሩን ነገድ ካቀፈው የእስራኤል መንግሥት (ከኤፍሬም) የተውጣጡ ግዞተኞች ወደ እስራኤል ምድር ተመልሰው በዚያ “አንድ ብሔር” ይሆናሉ።—ኤር. 30:1-3፤ 31:2-9፤ 33:7
-
-
የሁለቱ በትሮች አንድ መሆንየይሖዋ ንጹሕ አምልኮ መልሶ ተቋቋመ!
-
-
‘በእጅህ አንድ በትር ይሆናሉ’
በጥንት ዘመን
በ537 ዓ.ዓ. የአምላክ ሕዝቦች ከተለያዩ ብሔራት ተመልሰው ኢየሩሳሌምን ዳግመኛ ገነቡ፤ እንዲሁም አንድ ብሔር ሆነው ይሖዋን ማምለክ ጀመሩ።
በዘመናችን
ከ1919 ጀምሮ የአምላክ ሕዝቦች ቀስ በቀስ ተደራጁ፤ እንዲሁም “አንድ መንጋ” ሆነው በአንድነት ይሖዋን ማገልገል ጀመሩ።
-