-
“አንድ ብሔር አደርጋቸዋለሁ”የይሖዋ ንጹሕ አምልኮ መልሶ ተቋቋመ!
-
-
5. ሕዝቅኤል በድራማ መልክ ያሳየው ትንቢት ትርጉሙ ምንድን ነው? (“የሁለቱ በትሮች አንድ መሆን” የሚለውን ሣጥን ተመልከት።)
5 ከዚያም ይሖዋ ሁለቱ በትሮች አንድ መሆናቸው ምን ትርጉም እንዳለው ገለጸ። (ሕዝቅኤል 37:21, 22ን አንብብ።) ሁለቱን ነገድ ካቀፈው የይሁዳ መንግሥት የተውጣጡ ግዞተኞችና አሥሩን ነገድ ካቀፈው የእስራኤል መንግሥት (ከኤፍሬም) የተውጣጡ ግዞተኞች ወደ እስራኤል ምድር ተመልሰው በዚያ “አንድ ብሔር” ይሆናሉ።—ኤር. 30:1-3፤ 31:2-9፤ 33:7
-
-
“አንድ ብሔር አደርጋቸዋለሁ”የይሖዋ ንጹሕ አምልኮ መልሶ ተቋቋመ!
-
-
7. በ1 ዜና መዋዕል 9:2, 3 ላይ የሚገኘው ዘገባ ‘በአምላክ ዘንድ ሁሉ ነገር እንደሚቻል’ የሚያረጋግጠው እንዴት ነው?
7 ከሰብዓዊ አመለካከት አንጻር፣ የግዞተኞቹ ነፃ መውጣትም ሆነ አንድ መሆን ፈጽሞ የማይታሰብ ነገር ሊመስል ይችላል።a “በአምላክ ዘንድ ግን ሁሉ ነገር ይቻላል።” (ማቴ. 19:26) ይሖዋ፣ የተናገረው ትንቢት ፍጻሜውን እንዲያገኝ አድርጓል። የባቢሎን ግዞት በ537 ዓ.ዓ. ያበቃ ሲሆን ከሁለቱም መንግሥታት የተውጣጡ ግለሰቦች ወደ ኢየሩሳሌም ተመልሰው እውነተኛውን አምልኮ መልሶ በማቋቋሙ ሥራ የበኩላቸውን ድጋፍ መስጠት ጀመሩ። በመንፈስ መሪነት የተጻፈው የሚከተለው ዘገባ ይህን ያረጋግጣል፦ “የተወሰኑ የይሁዳ፣ የቢንያም፣ የኤፍሬምና የምናሴ ዘሮች በኢየሩሳሌም ተቀመጡ።” (1 ዜና 9:2, 3፤ ዕዝራ 6:17) በእርግጥም ልክ ይሖዋ በትንቢት እንደተናገረው አሥሩን ነገድ ያቀፈው የእስራኤል መንግሥት አባላት ሁለቱን ነገድ ካቀፈው የይሁዳ መንግሥት አባላት ጋር ተቀላቅለዋል ወይም አንድ ሆነዋል።
8. (ሀ) ኢሳይያስ ምን ትንቢት ተናግሮ ነበር? (ለ) በሕዝቅኤል 37:21 ላይ ምን ሁለት ዋና ዋና ነጥቦች ይገኛሉ?
8 ከ200 ዓመታት ገደማ በፊት ነቢዩ ኢሳይያስ እስራኤልና ይሁዳ በምርኮ ከተወሰዱ በኋላ ስለሚሆነው ነገር ትንቢት ተናግሮ ነበር። ይሖዋ “በየቦታው የተሰራጩትን እስራኤላውያን” እና “የተበታተኑትን የይሁዳ ሰዎች ከአራቱም የምድር ማዕዘኖች፣” “ከአሦር” ጭምር እንደሚሰበስብ ተንብዮ ነበር። (ኢሳ. 11:12, 13, 16) በእርግጥም ይሖዋ፣ በትንቢት በተናገረው መሠረት “እስራኤላውያንን ከሄዱባቸው ብሔራት” አምጥቷቸዋል። (ሕዝ. 37:21) እዚህ ጥቅስ ላይ ሁለት ዋና ዋና ነጥቦችን ልብ ማለት ያስፈልጋል፦ በዚህ ወቅት ይሖዋ ግዞተኞቹን “ይሁዳ” እና “ኤፍሬም” በማለት ፋንታ እንደ አንድ ሕዝብ በመቁጠር “እስራኤላውያን” ብሎ ጠርቷቸዋል። በተጨማሪም እስራኤላውያን ከአንድ ብሔር ማለትም ከባቢሎን ሳይሆን ከተለያዩ ብሔራት እንዲያውም “ከየአቅጣጫው” እንደሚመጡ ተገልጿል።
-