የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • “ጎግ ሆይ፣ እኔ በአንተ ላይ ተነስቻለሁ”
    የይሖዋ ንጹሕ አምልኮ መልሶ ተቋቋመ!
    • “ምድር” የተባለው ምንድን ነው?

      11. የሕዝቅኤል ትንቢት ጎግ የሚወረውን “ምድር” በተመለከተ ምን መግለጫ ይሰጣል?

      11 በአንቀጽ 3 ላይ እንደተመለከትነው የማጎጉ ጎግ በይሖዋ ዓይን ውድ የሆነን “ምድር” በመውረር የይሖዋን ታላቅ ቁጣ ይቀሰቅሳል። ይህ “ምድር” ምንን ያመለክታል? እስቲ መለስ ብለን የሕዝቅኤልን ትንቢት እንመልከት። (ሕዝቅኤል 38:8-12⁠ን አንብብ።) ትንቢቱ ጎግ “ከብሔራት ሁሉ መካከል ዳግመኛ የተሰበሰበውን” እና “የተመለሰውን ሕዝብ ምድር” እንደሚወር ይናገራል። በተጨማሪም ትንቢቱ በዚህ “ምድር” ላይ የሚኖሩትን የይሖዋ አምላኪዎች በተመለከተ ምን እንደሚል ልብ በል፦ “ያለስጋት ተቀምጠዋል”፤ “የሚኖሩት ቅጥር፣ መቀርቀሪያና በር በሌላቸው ሰፈሮች ነው”፤ እንዲሁም “ሀብትና ንብረት” አከማችተዋል። በዓለም ዙሪያ የሚገኙ የይሖዋ አምላኪዎች የሚኖሩት እንዲህ ባለው “ምድር” ላይ ነው። የዚህን “ምድር” ምንነት ለይተን ማወቅ የምንችለው እንዴት ነው?

      12. በጥንት ዘመን በእስራኤል ምድር ንጹሕ አምልኮ መልሶ በተቋቋመበት ወቅት የትኛው ትንቢት ፍጻሜውን አግኝቷል?

      12 የአምላክ የተመረጡ ሕዝቦች ለበርካታ መቶ ዓመታት ይኖሩበት፣ ይሠሩበትና ያመልኩበት በነበረው በጥንቱ እስራኤል ንጹሕ አምልኮ መልሶ በተቋቋመበት ወቅት የተፈጸመውን ነገር መመልከታችን ጠቃሚ ይሆናል። ይሖዋ፣ እስራኤላውያን ታማኝነታቸውን ባጓደሉበት ወቅት ምድራቸው እንደምትጠፋና ባድማ እንደምትሆን በሕዝቅኤል በኩል ተንብዮ ነበር። (ሕዝ. 33:27-29) በተጨማሪም ይሖዋ ንስሐ የገቡ እስራኤላውያን ቀሪዎች ከባቢሎን ግዞት እንደሚመለሱና በምድሪቱ ላይ ንጹሕ አምልኮን መልሰው እንደሚያቋቁሙ ተንብዮአል። ያን ጊዜ ይሖዋ በእስራኤል ምድር ላይ በረከቱን ስለሚያፈስ ምድሪቱ ተለውጣ “እንደ ኤደን የአትክልት ስፍራ” ውብ ትሆናለች። (ሕዝ. 36:34-36) ይህ ትንቢት ግዞተኞቹ አይሁዳውያን በትውልድ አገራቸው ንጹሕ አምልኮን መልሰው ለማቋቋም ወደ ኢየሩሳሌም ከተመለሱበት ከ537 ዓ.ዓ. ጀምሮ ፍጻሜውን አግኝቷል።

      13, 14. (ሀ) የአምላክ ሕዝቦች የሚኖሩበት “ምድር” ምንድን ነው? (ለ) ይህ “ምድር” በይሖዋ ዓይን ውድ የሆነው ለምንድን ነው?

      13 በዘመናችን ያሉ የአምላክ ሕዝቦችም ንጹሕ አምልኮ መልሶ ሲቋቋም መመልከት ችለዋል። በዚህ መጽሐፍ ምዕራፍ 9 ላይ እንደተመለከትነው፣ ለረጅም ዘመን በታላቂቱ ባቢሎን ግዞት ሥር የቆዩት የአምላክ ሕዝቦች በ1919 ነፃ ወጥተዋል። በዚያ ዓመት ይሖዋ ሕዝቦቹን ወደ አንድ “ምድር” አምጥቷቸዋል። ይህ “ምድር” መንፈሳዊውን ገነት፣ ማለትም እውነተኛውን አምላክ የምናመልክበትን ከስጋት ነፃ የሆነና በመንፈሳዊ የበለጸገ ሁኔታ ወይም የእንቅስቃሴ ቀጠና ያመለክታል። በዚህ “ምድር” ላይ አእምሯችንና ልባችን ሰላም አግኝቶ ያለስጋት በአንድነት እንኖራለን። (ምሳሌ 1:33) የተትረፈረፈ መንፈሳዊ ምግብ እናገኛለን፤ እንዲሁም እውነተኛ እርካታ በሚያስገኘው የአምላክን መንግሥት የማወጁ ሥራ እንካፈላለን። በእርግጥም “የይሖዋ በረከት ባለጸጋ ታደርጋለች፤ እሱም ከበረከቱ ጋር ሥቃይን አይጨምርም” የሚለው ምሳሌ እውነት እንደሆነ መመልከት ችለናል። (ምሳሌ 10:22) በየትኛውም የዓለም ክፍል ብንገኝ፣ ንጹሕ አምልኮን በቃልና በተግባር እስከደገፍን ድረስ የምንኖረው በዚህ “ምድር” ማለትም በመንፈሳዊው ገነት ውስጥ ነው።

      14 ይህ መንፈሳዊ ገነት በይሖዋ ዓይን በጣም ውድ ነው። ለምን? ምክንያቱም የዚህ “ምድር” ነዋሪዎች ይሖዋ ወደ ንጹሕ አምልኮ የሳባቸው ‘በብሔራት ሁሉ መካከል ያሉ ውድ ነገሮች’ ናቸው። (ሐጌ 2:7 ግርጌ፤ ዮሐ. 6:44) እነዚህ ሰዎች ግሩም የሆኑትን የአምላክ ባሕርያት የሚያንጸባርቀውን አዲስ ስብዕና ለመልበስ ልባዊ ጥረት ያደርጋሉ። (ኤፌ. 4:23, 24፤ 5:1, 2) ከንጹሕ አምልኮ ጎን የቆሙ እንደመሆናቸው መጠን አምላክን በሚያስከብርና ለእሱ ያላቸውን ፍቅር በሚያሳይ መንገድ አቅማቸው በፈቀደ መጠን በቅዱስ አገልግሎት ይካፈላሉ። (ሮም 12:1, 2፤ 1 ዮሐ. 5:3) ይሖዋ፣ አገልጋዮቹ መንፈሳዊውን ገነት ለማስዋብ የሚያደርጉትን ጥረት ሲመለከት ልቡ ምን ያህል በደስታ እንደሚሞላ መገመት እንችላለን። በሕይወትህ ውስጥ ለንጹሕ አምልኮ ቅድሚያ በመስጠት መንፈሳዊውን ገነት ማስዋብ ብቻ ሳይሆን የይሖዋን ልብ ደስ ማሰኘት ትችላለህ፤ ይህ እንዴት ያለ ታላቅ መብት ነው!—ምሳሌ 27:11

      ፎቶግራፎች፦ የይሖዋ አገልጋዮች። 1. ወንድሞችና እህቶች በስብሰባ አዳራሽ ውስጥ ሲጨዋወቱ። 2. ወንድሞችና እህቶች የስብሰባ አዳራሹን ሲንከባከቡ። 3. አንድ ወንድም እስር ቤት ውስጥ ሆኖ ሲጸልይ። 4. አንድ ባልና ሚስት በጣም የታመመችን አንዲት  እህት ሆስፒታል ሄደው ሲጠይቁ።

      በየትኛውም የዓለም ክፍል ብንገኝ፣ ንጹሕ አምልኮን እስከደገፍን ድረስ የምንኖረው በመንፈሳዊው ገነት ውስጥ ነው (አንቀጽ 13, 14⁠ን ተመልከት)

  • “ጎግ ሆይ፣ እኔ በአንተ ላይ ተነስቻለሁ”
    የይሖዋ ንጹሕ አምልኮ መልሶ ተቋቋመ!
    • 16 የማጎጉ ጎግ መንፈሳዊውን ገነት የሚወረው መቼ ነው? ትንቢቱ “በመጨረሻዎቹ ዓመታት . . . የተመለሰውን ሕዝብ ምድር ትወራለህ” ይላል። (ሕዝ. 38:8) ይህ ትንቢት ጎግ ይህን “ምድር” የሚወረው በዚህ ሥርዓት መጨረሻ አካባቢ እንደሆነ ይጠቁማል። ታላቁ መከራ የሚጀምረው በዓለም ላይ ያሉትን የሐሰት ሃይማኖቶች በሙሉ የምታመለክተው ታላቂቱ ባቢሎን ስትጠፋ እንደሆነ አስታውስ። የሐሰት ሃይማኖት ተቋማት ከጠፉ በኋላ እና አርማጌዶን ከመጀመሩ በፊት ጎግ ከእውነተኛው አምልኮ ጎን በቆሙ ሰዎች ላይ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ መጠነ ሰፊ ጥቃት ይሰነዝራል።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ