-
“የቤተ መቅደሱ ሕግ ይህ ነው”የይሖዋ ንጹሕ አምልኮ መልሶ ተቋቋመ!
-
-
በዘመናችን ከሕዝቅኤል ራእይ የምናገኘው ትምህርት
13, 14. (ሀ) ሕዝቅኤል ስለ ቤተ መቅደሱ ያየው ራእይ በእኛም ዘመን ፍጻሜውን እንደሚያገኝ እንዴት እናውቃለን? (ለ) ራእዩ በየትኞቹ ሁለት መንገዶች ይጠቅመናል? (“የተለያዩ ቤተ መቅደሶች፣ የተለያዩ ትምህርቶች” የሚለውን ሣጥን 13ሀንም ተመልከት።)
13 ሕዝቅኤል ስለ ቤተ መቅደሱ ያየው ራእይ ለእኛስ የያዘው ትምህርት አለ? አዎ! ሕዝቅኤል በራእይ ባየው “በአንድ ትልቅ ተራራ” ላይ የሚገኝ ቤተ መቅደስና ኢሳይያስ “የይሖዋ ቤት ተራራ ከተራሮች አናት በላይ ጸንቶ [እንደሚቆም]” በተናገረው ትንቢት መካከል ተመሳሳይነት እንዳለ አስታውስ። ኢሳይያስ ትንቢቱ ፍጻሜውን የሚያገኘው “በዘመኑ መጨረሻ” ወይም “በመጨረሻዎቹ ቀኖች” እንደሆነ በግልጽ ተናግሯል። (ሕዝ. 40:2፤ ኢሳ. 2:2-4 ግርጌ፤ ሚክያስ 4:1-4ንም ተመልከት።) እነዚህ ትንቢቶች ፍጻሜያቸውን የሚያገኙት በመጨረሻዎቹ ቀኖች ውስጥ ማለትም ንጹሕ አምልኮ መልሶ ከተቋቋመበትና በትልቅ ተራራ ላይ የተቀመጠ ያህል ከፍ ከፍ ከተደረገበት ከ1919 ጀምሮ ባለው ጊዜ ነው።b
14 ስለዚህ የሕዝቅኤል ራእይ በዛሬው ጊዜ ከምናቀርበው ንጹሕ አምልኮ ጋር በተያያዘም እንደሚሠራ በእርግጠኝነት መናገር እንችላለን። ይህ ራእይ በጥንት ዘመን የነበሩትን አይሁዳውያን ግዞተኞች እንደጠቀማቸው ሁሉ እኛንም በሁለት መንገዶች ይጠቅመናል። (1) ይሖዋ ለንጹሕ አምልኮ ያወጣውን መሥፈርት እንዴት ማክበር እንደምንችል ያስተምረናል። (2) ንጹሕ አምልኮ መልሶ እንደሚቋቋምና የይሖዋን በረከት እንደምናገኝ ዋስትና ይሰጠናል።
-
-
ሕዝቅኤል ስለ ቤተ መቅደሱ ካየው ራእይ የምናገኛቸው ትምህርቶችየይሖዋ ንጹሕ አምልኮ መልሶ ተቋቋመ!
-
-
ንጹሕ አምልኮ ከፍ ከፍ ተደረገ፤ ጥበቃም ተደረገለት
በራእይ የታየው ቤተ መቅደስ የሚገኘው “ትልቅ ተራራ” (1) ላይ ነው። እኛስ ንጹሕ አምልኮን በሕይወታችን ውስጥ በማስቀደም ከፍ ከፍ እንዲል እያደረግነው ነው?
-