የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • “ከተማዋ ‘ይሖዋ በዚያ አለ’ ተብላ ትጠራለች”
    የይሖዋ ንጹሕ አምልኮ መልሶ ተቋቋመ!
    • 4. ለይሖዋ መዋጮ ሆኖ ስለሚሰጠው መሬት ከሚገልጸው ዘገባ ምን ትምህርት እናገኛለን?

      4 ለይሖዋ መዋጮ ሆኖ ስለሚሰጠው መሬት ከሚገልጸው ዘገባ ምን ትምህርት እናገኛለን? ይሖዋ በመጀመሪያ መዋጮ ሆኖ የሚሰጠውን መሬት ከለየ በኋላ ለየነገዶቹ የሚከፋፈለውን መሬት በመመደብ ቅድሚያ ሊሰጥ የሚገባው ለዚህ መንፈሳዊ ማዕከል እንደሆነ አመልክቷል። (ሕዝ. 45:1) መሬቱ በዚህ ቅደም ተከተል መከፋፈሉ፣ በግዞት የነበሩትን እስራኤላውያን በሕይወታቸው ውስጥ ቀዳሚውን ቦታ መስጠት ያለባቸው ለይሖዋ አምልኮ እንደሆነ አስተምሯቸው እንደሚሆን ጥርጥር የለውም። ዛሬም በተመሳሳይ የአምላክን ቃል ማጥናትን፣ በክርስቲያናዊ ስብሰባዎች ላይ መገኘትንና በስብከቱ ሥራ መካፈልን ለመሳሰሉት መንፈሳዊ እንቅስቃሴዎች ቅድሚያ መስጠት እንደሚገባን እንገነዘባለን። ቅድሚያ ሊሰጠው የሚገባውን ነገር በማስቀደም ረገድ ይሖዋ የተወውን ምሳሌ የምንከተል ከሆነ የዕለት ተዕለት ሕይወታችን ለእሱ በምናቀርበው አምልኮ ላይ ያተኮረ ይሆናል።

  • “መዋጮ አድርጋችሁ ለመስጠት የምትለዩት መሬት”
    የይሖዋ ንጹሕ አምልኮ መልሶ ተቋቋመ!
    • መ. “መዋጮ ሆኖ የተሰጠ ቅዱስ ስፍራ”

      ይህ ቦታ “ቅዱስ ድርሻ” ተብሎም ተጠርቷል። የላይኛው ክፍል ‘ለሌዋውያን’ የተመደበ “የተቀደሰ” ድርሻ ነው። መካከለኛው ክፍል “ለካህናቱ መዋጮ ሆኖ የሚሰጥ ቅዱስ ስፍራ” ነው። “ለቤቶቻቸው እንዲሁም ለመቅደሱ የሚሆን” ቦታ ነው።

      ሕዝ. 45:1-5፤ 48:9-14

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ