የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • “ጅረቱ በሚፈስበት ቦታ ያለው ነገር ሁሉ በሕይወት ይኖራል”
    የይሖዋ ንጹሕ አምልኮ መልሶ ተቋቋመ!
    • 10, 11. (ሀ) በዛሬው ጊዜ እንደ ወንዝ እየፈሰሱልን ያሉት የትኞቹ በረከቶች ናቸው? (ለ) የይሖዋ በረከት ቁጥራቸው እያደገ የሄደውን ሰዎች ፍላጎት ማርካት በሚያስችል መጠን እየፈሰሰ ያለው እንዴት ነው?

      10 በረከት የሚያስገኝ ወንዝ። ከይሖዋ ቤት ስለሚፈሰው ውኃ የሚገልጸው ዘገባ በዘመናችን የትኞቹን በረከቶች ያስታውሰናል? በመንፈሳዊ እንድንመገብና መንፈሳዊ ጤንነታችን እንዲጠበቅ አስተዋጽኦ የሚያደርጉትን ነገሮች በሙሉ ያስታውሰናል። ከእነዚህ መካከል በዋነኝነት የሚጠቀሰው ለኃጢአታችን ይቅርታ እንድናገኝና እንድንነጻ የሚያስችለን የክርስቶስ ቤዛዊ መሥዋዕት ነው። በአምላክ ቃል ውስጥ የሚገኘው ንጹሕ እውነትም ሕይወት ሰጪ በሆነና በሚያነጻ ውኃ ተመስሏል። (ኤፌ. 5:25-27) እነዚህ በረከቶች በዘመናችን የፈሰሱት እንዴት ነው?

  • ቀስ እያለ የሚፈሰው ውኃ ትልቅ ወንዝ ሆነ!
    የይሖዋ ንጹሕ አምልኮ መልሶ ተቋቋመ!
    • ቀስ እያለ የሚፈሰው ውኃ ትልቅ ወንዝ ሆነ!

      ሕዝቅኤል ከይሖዋ ቤተ መቅደስ ወጥቶ ቀስ እያለ የሚፈስ ውኃ በአስደናቂ ሁኔታ እየጨመረ ሄዶ ሁለት ኪሎ ሜትር በማይሞላ ርቀት ውስጥ ትልቅ ወንዝ ሲሆን ተመለከተ። በወንዙ ዳርና ዳር ለመብልና ለመድኃኒት የሚሆኑ ዛፎች አሉ። የዚህ ሁሉ ትርጉም ምንድን ነው?

      ከቤተ መቅደሱ ወጥቶ የሚፈሰው ውኃ ትልቅ ወንዝ ሆነ። ውኃው ሲፈስ ያለውን ጥልቀት የሚያሳዩ ምልክቶች። 1,000 ክንድ፦ እስከ ቁርጭምጭሚት። 2,000 ክንድ፦ እስከ ጉልበት። 3,000 ክንድ፦ እስከ ወገብ። 4,000 ክንድ፦ በእግር መሻገር የማይቻል።

      በረከት የሚያስገኝ ወንዝ

      በጥንት ዘመን፦ ግዞተኞቹ ወደ ትውልድ አገራቸው ከተመለሱ በኋላ በቤተ መቅደሱ የሚከናወነውን ንጹሕ አምልኮ መልሶ በማቋቋሙ ሥራ ሲካፈሉ የይሖዋ በረከት ይፈስላቸው ነበር

      በዘመናችን፦ በ1919 ንጹሕ አምልኮ መልሶ ሲቋቋም ከዚያ በፊት ታይቶ በማይታወቅ መጠን ለአምላክ ታማኝ አገልጋዮች መንፈሳዊ በረከት የሚፈስበት መንገድ ተከፈተ

      ወደፊት፦ ከአርማጌዶን በኋላ የይሖዋ በረከት መንፈሳዊም ሆነ አካላዊ ጥቅም ያስገኛል

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ