የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • “ጅረቱ በሚፈስበት ቦታ ያለው ነገር ሁሉ በሕይወት ይኖራል”
    የይሖዋ ንጹሕ አምልኮ መልሶ ተቋቋመ!
    • 1, 2. በሕዝቅኤል 47:1-12 ላይ እንደተገለጸው ሕዝቅኤል ምን ተመለከተ? (በመግቢያው ላይ ያለውን ሥዕል ተመልከት።)

      ሕዝቅኤል ስለ ቤተ መቅደሱ ባየው ራእይ ላይ ሌላ አስደናቂ ነገር ተመለከተ፦ አንድ ጅረት ከቤተ መቅደሱ ወጥቶ ይፈስሳል። ሕዝቅኤል ይህን ኩልል ያለ ውኃ ተከትሎ ሲሄድ በዓይነ ሕሊናህ ይታይህ። (ሕዝቅኤል 47:1-12⁠ን አንብብ።) ውኃው የሚመነጨው ከመቅደሱ ደፍ ሥር ነው፤ ከዚያም ቀስ ብሎ እየፈሰሰ በምሥራቁ በር አቅራቢያ ከቤተ መቅደሱ ግቢ ይወጣል። ሕዝቅኤልን የሚያስጎበኘው መልአክ ሕዝቅኤልን እየመራ ከቤተ መቅደሱ ውጭ ወሰደው፤ በሚሄዱበት ጊዜም ርቀቱን ይለካ ነበር። መልአኩ ሕዝቅኤልን በተደጋጋሚ በውኃው መካከል እንዲያልፍ አደረገው። ነቢዩም የውኃው ጥልቀት በፍጥነት እየጨመረ እንደሄደ አስተዋለ፤ ብዙም ሳይቆይ ውኃው በዋና ካልሆነ በስተቀር በእግር ሊሻገሩት የማይቻል ትልቅ ወንዝ ሆነ!

  • “ጅረቱ በሚፈስበት ቦታ ያለው ነገር ሁሉ በሕይወት ይኖራል”
    የይሖዋ ንጹሕ አምልኮ መልሶ ተቋቋመ!
    • 5. በራእዩ ላይ የታየው ወንዝ ምንጊዜም ለሁሉም የሚበቃ በረከት እንደሚኖር የሚያረጋግጠው እንዴት ነው?

      5 ይሁንና ምንጊዜም ለሁሉም የሚበቃ በረከት ይኖራል? ራእዩ፣ ቀስ እያለ የሚፈሰው ውኃ በአስደናቂ ሁኔታ እየጨመረ ሄዶ ሁለት ኪሎ ሜትር በማይሞላ ርቀት ውስጥ ትልቅ ወንዝ እንደሚሆን ስለሚገልጽ በዚህ ረገድ የሚያሳስብ ነገር አይኖርም። (ሕዝ. 47:3-5) አይሁዳውያን ወደ ትውልድ አገራቸው ከተመለሱ በኋላ የሕዝቡ ቁጥር እያደገ ይሄድ ይሆናል፤ ያም ቢሆን የይሖዋ በረከት እየጨመረ ስለሚሄድ የሁሉንም ፍላጎት ማሟላት ይችላል። በራእዩ ላይ የታየው ወንዝ የተትረፈረፈ በረከት እንደሚኖር ያመለክታል።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ