የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ‘በምድራችን’ ላይ የወረደው የይሖዋ በረከት
    መጠበቂያ ግንብ—1999 | መጋቢት 1
    • 13. በዘመናችን ምን ፈውስ ተከናውኗል?

      13 ራእያዊው ወንዝ በድን ወደ ሆነው ሙት ባሕር ገብቶ በዚያ የሚያገኘውን ሁሉ ይፈውሳል። ይህ ባሕር በመንፈሳዊ በድን የሆነን አካባቢ ያመለክታል። ይሁን እንጂ “ወንዙም በመጣበት ስፍራ ሁሉ” ሕይወት ይርመሰመሳል። (ሕዝቅኤል 47:​9) በመጨረሻውም ቀን የሕይወት ውኃ ሊደርስ በቻለባቸው ሥፍራዎች የሚኖሩ ሰዎች መንፈሳዊ ሕይወት አግኝተዋል። በዚህ መንገድ ነፍስ ለመዝራት የመጀመሪያ የሆኑት በ1919 የነበሩት ቅቡዓን ቀሪዎች ናቸው። እንቅስቃሴ አልባ ከሆነው የበድንነት ሁኔታቸው ነቅተው መንፈሳዊ ሕይወት አግኝተዋል። (ሕዝቅኤል 37:​1-14፤ ራእይ 11:​3, 7-12) ይህ ወሳኝ የሆነ ውኃ ከዚያ ወዲህ በመንፈሳዊ በድን ወደሆኑ ሌሎች ሰዎች ተዳርሶ ሕይወት ሊዘሩ ስለቻሉ ቁጥራቸው በጣም እየጨመረ የመጣ ይሖዋን የሚወዱና የሚያገለግሉ እጅግ ብዙ ሰዎች ሊገኙ ችለዋል። በቅርቡ ደግሞ ይህ ዝግጅት ከሙታን ለሚነሱ ብዙ ሰዎች ይዘረጋል።

  • ‘በምድራችን’ ላይ የወረደው የይሖዋ በረከት
    መጠበቂያ ግንብ—1999 | መጋቢት 1
    • 18 በሺህ ዓመቱ ግዛት ማንኛውም አካላዊ፣ አእምሮአዊና ስሜታዊ ሕመም ይፈወሳል። አሕዛብ በምሳሌያዊው ዛፍ መፈወሳቸው የሚያመለክተው ይህንን ነው። በክርስቶስና በ144,000ዎቹ በኩል ላገኘናቸው ዝግጅቶች ምሥጋና ይድረስና “በዚያ የሚቀመጥ:- ታምሜያለሁ አይልም።” (ኢሳይያስ 33:​24) ይህ ወንዙ ከፍተኛ መስፋፋት የሚያደርግበት ወቅት ይሆናል። ከዚህ ንጹሕ የሕይወት ውኃ ለሚጠጡት በሚልዮን፣ ምናልባትም በቢልዮን የሚቆጠሩ ከሙታን የሚነሱ ሰዎች በቂ እንዲሆን የበለጠ ጥልቀትና ስፋት ማግኘት ይኖርበታል። በሕዝቅኤል ራእይ ውስጥ ወንዙ ሙት ባሕርን ሲፈውስ ውኃው የደረሰበት አካባቢ ሁሉ ነፍስ ዘርቷል። ስለዚህ በገነት ውስጥ የሚኖሩ ወንዶችና ሴቶች በሙሉ በተዘረጋላቸው ቤዛዊ ጥቅሞች ካመኑ ከወረሱት አዳማዊ ሞት ተፈውሰው ሙሉ በሙሉ ሕያዋን ይሆናሉ። ራእይ 20:​12 በዚያ ዘመን ከሙታን ለሚነሱት ጭምር የሚጠቅም ተጨማሪ እውቀትና ማስተዋል የሚሰጡ “ጥቅልሎች” እንደሚከፈቱ ይተነብያል። የሚያሳዝነው ግን በዚህ በገነት እንኳን ለመፈወስ እምቢተኛ የሚሆኑ አንዳንድ ሰዎች ይኖራሉ። ‘ጨው ሆነው እንዲቀሩ’ የሚደረጉት ማለትም ለዘላለም ጥፋት የሚዳረጉት እነዚህ ዓመፀኞች ናቸው።​—⁠ራእይ 20:​15

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ