-
“ጅረቱ በሚፈስበት ቦታ ያለው ነገር ሁሉ በሕይወት ይኖራል”የይሖዋ ንጹሕ አምልኮ መልሶ ተቋቋመ!
-
-
7. በወንዙ ዳርና ዳር ስለበቀሉት ዛፎች የሚናገረው መግለጫ ለግዞተኞቹ አይሁዳውያን ምን ዋስትና ሰጥቷቸዋል?
7 ለመብልና ለመድኃኒት የሚሆኑ ዛፎች። በወንዙ ዳርና ዳር ስላሉት ዛፎችስ ምን ማለት ይቻላል? እነዚህ ዛፎች ለራእዩ ውበት ከመስጠት ባለፈ የሚያስተላልፉት መልእክትም አለ። ሕዝቅኤልና ወገኖቹ እነዚህ ዛፎች በየወሩ ስለሚሰጡት ጣፋጭ ፍሬ ማሰባቸው ብቻ እንኳ እንደሚያስደስታቸው የታወቀ ነው። ይህ አስደሳች መግለጫ ይሖዋ በመንፈሳዊ እንደሚመግባቸው ተጨማሪ ዋስትና ሰጥቷቸዋል። ከዚህም ሌላ የዛፎቹ ቅጠል “ለመድኃኒት” እንደሚሆን ልብ በል። (ሕዝ. 47:12) ይሖዋ ከግዞት የሚመለሱት አይሁዳውያን ከሁሉ ይበልጥ የሚያስፈልጋቸው መንፈሳዊ ፈውስ እንደሆነ ያውቃል፤ በመሆኑም በመንፈሳዊ ሁኔታ እንደሚፈውሳቸው ተስፋ ሰጥቷቸዋል። ይህ ተስፋ የሚፈጸመው እንዴት እንደሆነ ንጹሕ አምልኮ መልሶ እንደሚቋቋም በሚገልጹ ሌሎች ትንቢቶች ላይ ተብራርቷል፤ በዚህ መጽሐፍ ምዕራፍ 9 ላይ ይህን ሐሳብ ተመልክተን ነበር።
-
-
ቀስ እያለ የሚፈሰው ውኃ ትልቅ ወንዝ ሆነ!የይሖዋ ንጹሕ አምልኮ መልሶ ተቋቋመ!
-
-
ለመብልና ለመድኃኒት የሚሆኑ ዛፎች
በጥንት ዘመን፦ ይሖዋ ከግዞት የተመለሱ ታማኝ ሕዝቦቹን በመንፈሳዊ መግቧቸዋል፤ እንዲሁም ለረጅም ዘመናት ሲያሠቃያቸው ከቆየው መንፈሳዊ ሕመም ፈውሷቸዋል
በዘመናችን፦ በተትረፈረፈ ሁኔታ የሚቀርበው መንፈሳዊ ምግብ ብዙ ሰዎች በዛሬው ጊዜ ያለውን ዓለም ቀስፎ የያዘውን መንፈሳዊ ሕመምና ረሃብ እንዲቋቋሙ አስችሏቸዋል
ወደፊት፦ ክርስቶስና አብረውት የሚገዙት 144,000 ቅቡዓን፣ ታዛዥ የሰው ልጆች ወደ ፍጽምና እንዲደርሱ እንዲሁም ለዘላለም ጤናማና ጠንካራ ሆነው እንዲኖሩ ይረዷቸዋል!
-