የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ‘ምድሪቱን ርስት አድርጋችሁ ተከፋፈሉ’
    የይሖዋ ንጹሕ አምልኮ መልሶ ተቋቋመ!
    • “ይህች ምድር ርስት ሆና ተሰጥታችኋለች”

      5, 6. (ሀ) ለነገዶቹ የሚከፋፈለው ክልል የትኛው ነው? (በመግቢያው ላይ ያለውን ሥዕል ተመልከት።) (ለ) ስለ ርስት ክፍፍል የሚገልጸው ራእይ ዓላማ ምንድን ነው?

      5 ሕዝቅኤል 47:14⁠ን አንብብ። ይሖዋ በራእይ አማካኝነት ሕዝቅኤል ትኩረቱን “እንደ ኤደን የአትክልት ሥፍራ” በምትሆነው ምድር ላይ እንዲያሳርፍ አደረገ። (ሕዝ. 36:35) ከዚያም ይሖዋ “ለ12ቱ የእስራኤል ነገዶች ርስት አድርጋችሁ የምታከፋፍሏት ክልል ይህች ናት” አለው። (ሕዝ. 47:13) ለነገዶቹ የሚከፋፈለው “ክልል” ግዞተኞቹ ተመልሰው የሚኖሩበት የእስራኤል ምድር ነው። ቀጥሎም በሕዝቅኤል 47:15-21 ላይ ተመዝግቦ እንደሚገኘው ይሖዋ የምድሪቱን ውጫዊ ወሰኖች በዝርዝር ገለጸ።

      6 ስለ ርስት ክፍፍል የሚገልጸው የዚህ ራእይ ዓላማ ምንድን ነው? የወሰኖቹ ልክ በዝርዝር መገለጹ ሕዝቅኤልና ግዞተኛ ወገኖቹ የሚወዷት አገራቸው ተመልሳ እንደምትቋቋም እርግጠኛ እንዲሆኑ አድርጓቸዋል። ይሖዋ እንዲህ ያለውን ዝርዝር መግለጫ በመጠቀም የሰጣቸው ዋስትና ግዞተኞቹን ምን ያህል አስደስቷቸው እንደሚሆን መገመት እንችላለን። ታዲያ የጥንቶቹ የአምላክ ሕዝቦች በእርግጥ በምድሪቱ ላይ ርስት ተሰጥቷቸዋል? አዎ፣ ተሰጥቷቸዋል።

      አንድ ወንዝ ወደ ባሕር ሲፈስ፤ በዙሪያው ለሕዝቡ የሚከፋፈለው መሬት አለ።

      7. (ሀ) በ537 ዓ.ዓ. የትኛው ክንውን መፈጸም ጀመረ? ይህስ ምን ያስታውሰናል? (ለ) በመጀመሪያ የትኛውን ጥያቄ እንመለከታለን?

      7 ሕዝቅኤል ራእዩን ካየ ከ56 ዓመት ገደማ በኋላ በ537 ዓ.ዓ. በሺዎች የሚቆጠሩ ግዞተኞች ወደ እስራኤል ምድር ተመልሰው ምድሪቱን መውረስ ጀመሩ። ጥንት የተፈጸመው ይህ አስደናቂ ክንውን በዘመናችን በአምላክ ሕዝቦች መካከል የተፈጸመውን ተመሳሳይ ክንውን ያስታውሰናል። በዘመናችን ያሉ የአምላክ ሕዝቦችም ርስት ተሰጥቷቸዋል ሊባል ይችላል። እንዴት? ይሖዋ አገልጋዮቹ ወደ አንድ መንፈሳዊ “ምድር” እንዲገቡና ርስታቸው አድርገው እንዲወርሱት ፈቅዶላቸዋል። በመሆኑም በጥንት ዘመን የነበረችው ተስፋይቱ ምድር መልሳ እንደምትቋቋም የሚገልጸው ትንቢት፣ በዘመናችን የአምላክ ሕዝቦች የሚኖሩበት መንፈሳዊ “ምድር” መልሶ ስለተቋቋመበት ሁኔታ ጥሩ ትምህርት ይሰጠናል። ይሁን እንጂ የምናገኘውን ትምህርት ከመመርመራችን በፊት “በዛሬው ጊዜ መንፈሳዊ ‘ምድር’ አለ የሚል መደምደሚያ ላይ የደረስነው ለምንድን ነው?” ለሚለው ጥያቄ መልስ ለማግኘት እንሞክር።

      8. (ሀ) ይሖዋ የሥጋዊ እስራኤላውያንን ብሔር በየትኛው ብሔር ተክቶታል? (ለ) መንፈሳዊው “ምድር” ወይም መንፈሳዊው ገነት ምንድን ነው? (ሐ) መንፈሳዊው ገነት ወደ ሕልውና የመጣው መቼ ነው? በዚያ የሚኖሩትስ እነማን ናቸው?

      8 ይሖዋ ቀደም ሲል ለሕዝቅኤል ባሳየው ራእይ ላይ፣ እስራኤል መልሳ እንደምትቋቋም የሚናገሩት ትንቢቶች በላቀ ሁኔታ ፍጻሜያቸውን የሚያገኙት ‘አገልጋዩ ዳዊት’ ማለትም ኢየሱስ ክርስቶስ ንጉሥ ሆኖ መግዛት ከጀመረ በኋላ እንደሆነ አመልክቷል። (ሕዝ. 37:24) ይህ የሆነው በ1914 ዓ.ም. ነው። በዚህ ወቅት የሥጋዊ እስራኤላውያን ብሔር የአምላክ ሕዝብ መሆኑ ቀርቶ በመንፈስ የተቀቡ ክርስቲያኖችን ባቀፈው የመንፈሳዊ እስራኤል ብሔር ከተተካ ብዙ ዘመን አልፏል። (ማቴዎስ 21:43፤ 1 ጴጥሮስ 2:9⁠ን አንብብ።) ይሁን እንጂ ይሖዋ የሥጋዊ እስራኤላውያንን ብሔር በመንፈሳዊ ብሔር በመተካት ብቻ አልተወሰነም፤ ግዑዙን የእስራኤል አገርም በመንፈሳዊ “ምድር” ማለትም በመንፈሳዊው ገነት ተክቶታል። (ኢሳ. 66:8) በዚህ መጽሐፍ ምዕራፍ 17 ላይ እንደተመለከትነው መንፈሳዊው ገነት ቅቡዓን ክርስቲያኖች ከ1919 ጀምሮ ይሖዋን ሲያመልኩ የቆዩበትን ከስጋት ነፃ የሆነ መንፈሳዊ ሁኔታ ወይም የእንቅስቃሴ ቀጠና ያመለክታል። (“በ1919 ነው የምንለው ለምንድን ነው?” የሚለውን ሣጥን 9ለን ተመልከት።) ከጊዜ በኋላ፣ ምድራዊ ተስፋ ያላቸው ‘ሌሎች በጎችም’ በዚህ መንፈሳዊ ገነት ውስጥ መኖር ጀምረዋል። (ዮሐ. 10:16) መንፈሳዊው ገነት በዛሬው ጊዜም በማደግና በመስፋፋት ላይ ቢሆንም ይህ ገነት የሚያስገኛቸውን በረከቶች ሙሉ በሙሉ ማጣጣም የሚቻለው ገና ከአርማጌዶን በኋላ ነው።

  • ‘ምድሪቱን ርስት አድርጋችሁ ተከፋፈሉ’
    የይሖዋ ንጹሕ አምልኮ መልሶ ተቋቋመ!
    • 13 አንደኛ፣ የምድሪቱ አከፋፈል። ሙሴ ብዙ ሕዝብ ላላቸው ነገዶች በዛ ያለ ርስት፣ አነስተኛ የሕዝብ ቁጥር ላላቸው ነገዶች ደግሞ አነስ ያለ ርስት እንዲሰጥ ተነግሮት ነበር። (ዘኁ. 26:52-54) ሆኖም ሕዝቅኤል ባየው ራእይ ላይ፣ ይሖዋ ለሁሉም ነገዶች “እኩል ድርሻ [“እያንዳንዱም እንደ ወንድሙ” ግርጌ]” እንዲከፋፈል መመሪያ ሰጥቷል። (ሕዝ. 47:14) በመሆኑም የ12ቱም ነገዶች ርስት ከሰሜን ወሰኑ እስከ ደቡብ ወሰኑ ድረስ ያለው ርቀት እኩል መሆን ነበረበት። የየትኛውም ነገድ አባል የሆኑ እስራኤላውያን፣ ለምለም የሆነችው ተስፋይቱ ምድር ከምታስገኘው የተትረፈረፈ ምርት በእኩል መጠን ተጠቃሚዎች ይሆናሉ።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ