የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ‘አራት ፊት ያላቸው አራቱ ሕያዋን ፍጥረታት’ ምን ያመለክታሉ?
    የይሖዋ ንጹሕ አምልኮ መልሶ ተቋቋመ!
    • 15. ሕዝቅኤል፣ ባየው የመጀመሪያ ራእይ አማካኝነት ምን የሚያጽናና እውነት ተምሯል?

      15 ሕዝቅኤል፣ ባየው የመጀመሪያ ራእይ አማካኝነት ከይሖዋ ጋር ስላለው ዝምድና አንድ ወሳኝና የሚያጽናና እውነት ተምሯል። ይህ እውነት ምንድን ነው? በሕዝቅኤል መጽሐፍ የመክፈቻ ቃላት ላይ ይህ እውነት ተገልጿል። ሕዝቅኤል “በከለዳውያን ምድር” እንደነበረ ከገለጸ በኋላ “በዚያም የይሖዋ ኃይል በእሱ ላይ [እንደወረደ]” ተናግሯል። (ሕዝ. 1:3) ሕዝቅኤል ራእዩን ያየው በኢየሩሳሌም ሳይሆን እዚያው ባቢሎን እያለ መሆኑን እንደገለጸ ልብ በል።c ታዲያ ይህ ለሕዝቅኤል ምን አስገንዝቦታል? ሕዝቅኤል ከኢየሩሳሌምና ከቤተ መቅደሱ ርቆ የሚኖር ምስኪን ግዞተኛ ቢሆንም ከይሖዋና ከአምልኮው ግን አልተነጠለም። ይሖዋ በባቢሎን ለሕዝቅኤል መገለጡ ሕዝቅኤል የሚያቀርበው ንጹሕ አምልኮ በሚኖርበት ቦታ ወይም በኑሮ ሁኔታው ላይ የተመካ እንዳልሆነ ያሳያል። ዋናው ነገር የሕዝቅኤል የልብ ሁኔታና ይሖዋን ለማገልገል ያለው ፍላጎት ነው።

  • ‘አራት ፊት ያላቸው አራቱ ሕያዋን ፍጥረታት’ ምን ያመለክታሉ?
    የይሖዋ ንጹሕ አምልኮ መልሶ ተቋቋመ!
    • c አንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ተንታኝ እንደተናገሩት “በዚያም” የሚለው ቃል ‘ሁኔታው ሕዝቅኤልን ምን ያህል እንዳስደነቀው በግልጽ ያሳያል። አምላክ በዚያ በባቢሎንም አለ! ይህ ምንኛ የሚያጽናና ነው!’

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ