-
“አሁን ፍጻሜሽ ደርሷል”የይሖዋ ንጹሕ አምልኮ መልሶ ተቋቋመ!
-
-
6. (ሀ) ሕዝቅኤል በአንድ ጊዜ የትኞቹን ሁለት ገጸ ባሕርያት ወክሎ ተጫውቷል? (ለ) ይሖዋ ለሕዝቅኤል ‘ፀጉሩን መዝኖ እንዲከፋፍል’ የሰጠው ትእዛዝ ምን ያመለክታል?
6 የኢየሩሳሌምና የነዋሪዎቿ መጥፋት። በዚህኛው ትንቢታዊ ድራማ ላይ ሕዝቅኤል በአንድ ጊዜ ሁለት ገጸ ባሕርያትን ወክሎ ይጫወታል። በመጀመሪያ ሕዝቅኤል ይሖዋ የሚያደርገውን ነገር በድራማ መልክ ያሳያል። ይሖዋ ሕዝቅኤልን “እንደ ፀጉር አስተካካይ ምላጭ የምትጠቀምበት ስለታም ሰይፍ ውሰድ” አለው። (ሕዝቅኤል 5:1, 2ን አንብብ።) ሰይፉን የጨበጠው የሕዝቅኤል እጅ የይሖዋን እጅ፣ ማለትም በባቢሎን ሠራዊት አማካኝነት የሚፈጸመውን ፍርዱን ያመለክታል። ቀጥሎ ደግሞ ሕዝቅኤል አይሁዳውያን የሚደርስባቸውን ነገር በድራማ መልክ ያሳያል። ይሖዋ ለሕዝቅኤል “የራስህን ፀጉርና ጢምህን ተላጭ” ብሎታል። የሕዝቅኤል ራስ መላጨት አይሁዳውያን ጥቃት እንደሚሰነዘርባቸውና ሙሉ በሙሉ እንደሚጠፉ የሚያመለክት ነው። ከዚህም ሌላ “ሚዛን ወስደህ ፀጉሩን መዝነውና ከፋፍለው” መባሉ በኢየሩሳሌም ላይ የሚፈጸመው የይሖዋ ፍርድ በታሰበበትና ሥር ነቀል በሆነ መንገድ የሚፈጸም እንጂ በዘፈቀደ የሚከናወን አለመሆኑን ያመለክታል።
-
-
“የራስህን ፀጉርና ጢምህን ተላጭ”የይሖዋ ንጹሕ አምልኮ መልሶ ተቋቋመ!
-
-
“ተላጭ”
አይሁዳውያን ጥቃት ይሰነዘርባቸዋል እንዲሁም ተጠራርገው ይጠፋሉ
“መዝነውና ከፋፍለው”
የይሖዋ ፍርድ በታሰበበትና ሥር ነቀል በሆነ መንገድ የሚፈጸም ይሆናል
-