-
“አሁን ፍጻሜሽ ደርሷል”የይሖዋ ንጹሕ አምልኮ መልሶ ተቋቋመ!
-
-
7. ይሖዋ ለሕዝቅኤል ፀጉሩን ሦስት ቦታ እንዲከፋፍለውና በእያንዳንዱ ክፍል ላይ የተለያየ ነገር እንዲያደርግ የነገረው ለምን ነበር?
7 ይሖዋ ለሕዝቅኤል የተላጨውን ፀጉሩን ሦስት ቦታ እንዲከፋፍለውና በእያንዳንዱ ክፍል ላይ የተለያየ ነገር እንዲያደርግ የነገረው ለምን ነበር? (ሕዝቅኤል 5:7-12ን አንብብ።) ሕዝቅኤል ከኢየሩሳሌም ነዋሪዎች አንዳንዶቹ በከተማዋ ውስጥ እንደሚሞቱ ለማሳየት የፀጉሩን አንድ ክፍል “በከተማዋ ውስጥ” አቃጠለ። ሌሎቹ የኢየሩሳሌም ነዋሪዎች ከከተማዋ ውጭ እንደሚገደሉ ለማመልከት ደግሞ የፀጉሩን ሌላ ክፍል “በከተማዋ ዙሪያ” በሰይፍ መታ። ከዚያም የቀሩት የኢየሩሳሌም ነዋሪዎች ወደተለያዩ ብሔራት እንደሚበተኑ ለማሳየት የመጨረሻውን የፀጉሩን ክፍል ለነፋስ በተነው፤ እነዚህ ሰዎች በሚበተኑበት ቦታ ሁሉ ‘ሰይፍ ያሳድዳቸዋል።’ ይህም ከጥፋቱ በሕይወት የተረፉት ሰዎች የትም ቦታ ቢሄዱ ሰላም እንደማያገኙ ያመለክታል።
-
-
“የራስህን ፀጉርና ጢምህን ተላጭ”የይሖዋ ንጹሕ አምልኮ መልሶ ተቋቋመ!
-
-
‘አቃጥለው’
አንዳንዶች በከተማዋ ውስጥ ይሞታሉ
‘ምታው’
አንዳንዶች ከከተማዋ ውጭ ይገደላሉ
‘በትነው’
አንዳንዶች ከጥፋቱ ያመልጣሉ፤ ግን ሰላም አያገኙም
-
-
“አሁን ፍጻሜሽ ደርሷል”የይሖዋ ንጹሕ አምልኮ መልሶ ተቋቋመ!
-
-
10 የአምላክ ቃል ወደፊት የሃይማኖት ተቋማት በሚጠፉበት ወቅት በርካታ የሐሰት ሃይማኖት ተከታዮች በሕይወት እንደሚተርፉ ይጠቁማል። በዚያን ጊዜ መሸሸጊያ ለማግኘት እንደሚራወጡት የተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች ሁሉ እነዚህ ሰዎችም በፍርሃት ተውጠው የሚደበቁበት ቦታ ለማግኘት ጥረት ያደርጋሉ። (ዘካ. 13:4-6፤ ራእይ 6:15-17) የእነዚህ ሰዎች ሁኔታ ከጥፋት ከተረፉ በኋላ ‘ለነፋስ የተበተኑትን’ የጥንቷ ኢየሩሳሌም ነዋሪዎች ያስታውሰናል። በአንቀጽ 7 ላይ እንደተመለከትነው የጥንቷ ኢየሩሳሌም ነዋሪዎች ለጊዜው ሕይወታቸው ቢተርፍም ይሖዋ “እነሱን ለማሳደድ ሰይፍ” መዞባቸዋል። (ሕዝ. 5:2) በተመሳሳይም በሐሰት ሃይማኖት ላይ ከሚደርሰው ጥቃት የሚተርፉት ሰዎች የትም ቦታ ሄደው ለመሸሸግ ቢሞክሩ ከይሖዋ ሰይፍ ማምለጥ አይችሉም። ከሌሎቹ ፍየል መሰል ሰዎች ጋር አብረው በአርማጌዶን ይጠፋሉ።—ሕዝ. 7:4፤ ማቴ. 25:33, 41, 46፤ ራእይ 19:15, 18
ምሥራቹን መናገራችንን ስለምናቆም እንደ “ዱዳ” እንሆናለን
-