-
“አሁን ፍጻሜሽ ደርሷል”የይሖዋ ንጹሕ አምልኮ መልሶ ተቋቋመ!
-
-
8. (ሀ) የሕዝቅኤል ትንቢታዊ ድራማ ምን የተስፋ ጭላንጭል ይዟል? (ለ) ስለ ‘ጥቂት ፀጉሮች’ የተነገረው ትንቢት ፍጻሜውን ያገኘው እንዴት ነበር?
8 ይሁን እንጂ የሕዝቅኤል ትንቢታዊ ድራማ የተስፋ ጭላንጭልም የያዘ ነው። ይሖዋ ሕዝቅኤልን “ከፀጉሮቹ ላይ ጥቂት ወስደህ በልብስህ እጥፋት ቋጥራቸው” ብሎታል። (ሕዝ. 5:3) ይህ ትእዛዝ በብሔራት መካከል ከሚበተኑት አይሁዳውያን መካከል ጥቂቶች በሕይወት እንደሚተርፉ ያመለክታል። ከእነዚህ ‘ጥቂት ፀጉሮች’ ውስጥ አንዳንዶቹ ለ70 ዓመት የሚቆየው የባቢሎን ግዞት ሲያበቃ ወደ ኢየሩሳሌም ከሚመለሱት ግዞተኞች መካከል ይሆናሉ። (ሕዝ. 6:8, 9፤ 11:17) ታዲያ ይህ ትንቢት ፍጻሜውን አግኝቷል? በሚገባ! የባቢሎን ግዞት ካበቃ ከዓመታት በኋላ ነቢዩ ሐጌ ከተበተኑት አይሁዳውያን መካከል አንዳንዶቹ ወደ ኢየሩሳሌም እንደተመለሱ ዘግቧል። “የቀድሞውን ቤት [የሰለሞንን ቤተ መቅደስ] ያዩ ሽማግሌዎች” የተባሉት እነዚህ አይሁዳውያን ናቸው። (ዕዝራ 3:12፤ ሐጌ 2:1-3) ይሖዋ አስቀድሞ በገባው ቃል መሠረት ንጹሕ አምልኮ ሙሉ በሙሉ እንዳይጠፋ አድርጓል። በዚህ መጽሐፍ ምዕራፍ 9 ላይ ንጹሕ አምልኮ መልሶ ስለተቋቋመበት መንገድ የሚገልጽ ተጨማሪ ማብራሪያ እናገኛለን።—ሕዝ. 11:17-20
-
-
“የራስህን ፀጉርና ጢምህን ተላጭ”የይሖዋ ንጹሕ አምልኮ መልሶ ተቋቋመ!
-
-
“ቋጥራቸው”
አንዳንድ ግዞተኞች ወደ ኢየሩሳሌም ይመለሳሉ፤ ንጹሕ አምልኮም ሙሉ በሙሉ አይጠፋም
-