የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ከአንበሶች መንጋጋ ዳነ!
    የዳንኤልን ትንቢት በትኩረት ተከታተል!
    • 7. የመንግሥቱ አለቆችና መሳፍንቱ ለንጉሡ ምን ሐሳብ አቀረቡ? ይህንንስ ያደረጉት እንዴት ነበር?

      7 የመንግሥቱ አለቆችና መሳፍንት አንድ ላይ ‘ስብስብ ብለው’ ዳርዮስ ዘንድ ገቡ። እዚህ ላይ የተሠራበት የአረማይክ አገላለጽ ድብልቅልቅ ያለ ውካታን የሚያመለክት ነው። እነዚህ ሰዎች ወደ ዳርዮስ የቀረቡት እጅግ አንገብጋቢ ጉዳይ እንዳላቸው አድርገው ነው። እነርሱ ያመኑበትና አፋጣኝ እርምጃ የሚያሻው ነገር እንደሆነ አድርገው ቢያቀርቡት ዳርዮስ ሐሳባቸውን ለመቀበል ብዙም እንደማያንገራግር አስበው ሊሆን ይችላል። በመሆኑም በቀጥታ ወደ ፍሬ ጉዳያቸው በመሄድ እንዲህ አሉ:- “የመንግሥቱ አለቆች ሁሉ ሹማምቶችና መሳፍንት አማካሪዎችና አዛዦች:- ንጉሥ ሆይ፣ ከአንተ በቀር ማንም እስከ ሠላሳ ቀን ድረስ ልመና ከአምላክ ወይም ከሰው ቢለምን፣ በአንበሶች ጒድጓድ ውስጥ ይጣል የሚል የንጉሥ ሕግና ብርቱ ትእዛዝ ይወጣ ዘንድ ተማከሩ።”a—ዳንኤል 6:6, 7

      8. (ሀ) ዳርዮስ የቀረበው የሕግ ረቂቅ ጥሩ እንደሚሆን የተሰማው ለምን ሊሆን ይችላል? (ለ) የመንግሥቱ አለቆችና የመሳፍንቱ እውነተኛ ዓላማ ግን ምን ነበር?

      8 የመሶጴጣሚያ ነገሥታት እንደ መለኮት መታየታቸውና መመለካቸው የተለመደ ነገር እንደነበር ታሪካዊ መዛግብትም ይመሠክራሉ። በመሆኑም ዳርዮስ በዚህ ሐሳብ ተደልሎ እንደነበር ምንም ጥርጥር የለውም። ደግሞም ሐሳቡ ጠቃሚ ሊሆን የሚችልበት ጎን ታይቶት ይሆናል። በባቢሎን ለሚኖሩት ሰዎች ዳርዮስ የባዕድ አገር ሰውና መጤ መሆኑን አትዘንጋ። ይህ አዲስ ሕግ እንደ ንጉሥ አድርገው እንዲቀበሉትና በባቢሎን ያሉት በጣም ብዙ ነዋሪዎችም ለአዲሱ አገዛዝ ታማኝነታቸውንና ድጋፋቸውን እንዲገልጹ የሚያበረታታ ሊሆን ይችላል። የመንግሥቱ አለቆችና መሳፍንቱ ግን ይህንን ነገር ሲወጥኑ ያሳሰባቸው የንጉሡ ጥቅም አልነበረም። እውነተኛው ዓላማቸው ዳንኤልን ወጥመድ ውስጥ ማስገባት ነበር። ምክንያቱም ዳንኤል በቤቱ አናት ላይ ወዳለው እልፍኝ ገብቶ መስኮቶችን ከፍቶ በቀን ሦስት ጊዜ ወደ አምላኩ የመጸለይ ልማድ እንደነበረው ያውቃሉ።

      9. አዲሱ ሕግ አይሁዳውያን ላልሆኑ ለአብዛኛዎቹ ሰዎች እምብዛም ችግር የማይፈጥርባቸው ለምንድን ነበር?

      9 በጸሎት ላይ የተደረገው ይህ እገዳ በባቢሎን በነበሩት ሃይማኖታዊ ወገኖች ሁሉ ላይ ችግር የሚፈጥር ነበርን? በተለይ እገዳው የሚቆየው ለሠላሳ ቀናት ብቻ ስለነበር እንደዚያ ማለት ላይሆን ይችላል። ከዚህም በላይ ለጊዜውም ቢሆን ለሰው አምልኮ መስጠትን አቋምን እንደማላላት የሚቆጥሩት አይሁዳዊ ያልሆኑ ሰዎች እጅግ ጥቂት ናቸው። አንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ምሁር እንዲህ ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል:- “ከማንኛውም ብሔር ይበልጥ ጣዖት አምላኪ ለሆኑት ሰዎች የነገሥታት አምልኮ ያን ያህል እንግዳ የሆነ ነገር የሚጠይቅባቸው አልነበረም። በመሆኑም ባቢሎናውያን ለጣዖት አምላክ የሚገባውን ክብር ለድል አድራጊው ለሜዶናዊው ዳርዮስ እንዲሰጡ ሲጠየቁ ጥያቄውን በእሺታ ተቀብለውታል። እንዲህ ያለውን ጥያቄ ሳይቀበሉ የቀሩት አይሁዳውያኑ ብቻ ናቸው።”

  • ከአንበሶች መንጋጋ ዳነ!
    የዳንኤልን ትንቢት በትኩረት ተከታተል!
    • a የምሥራቃውያን ገዥዎች ብዙውን ጊዜ አራዊት ያሉባቸው መናፈሻዎች እንደነበሯቸው የሚገልጹ ተቀርጸው የተገኙ ጥንታዊ ጽሑፎች በባቢሎን ‘የአንበሶች ጉድጓድ’ መኖሩን የሚደግፉ ማስረጃዎች ናቸው።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ