የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • የልዑላንን ልዑል ሊገዳደር የሚችል ማን ነው?
    የዳንኤልን ትንቢት በትኩረት ተከታተል!
    • 21. ሰባተኛው የዓለም ኃይል ወና ሊያስቀረው የፈለገውን ‘ቅዱስ ስፍራ’ የያዙት እነማን ናቸው?

      21 ዛሬ ያሉት የ144,000ዎቹ ቀሪዎች ‘የሰማያዊቷ ኢየሩሳሌም’ ማለትም የከተማ መሰሏ የአምላክ መንግሥትና የቤተ መቅደስ ዝግጅቷ ምድራዊ ወኪሎች ናቸው። (ዕብራውያን 12:22, 28፤ 13:14) ከዚህ አንጻር ሲታይ ቅዱሳኑ ሰባተኛው የዓለም ኃይል ሊረግጠውና ወና ሊያስቀረው የሚፈልገውን ‘ቅዱስ ስፍራ’ ይዘዋል። (ዳንኤል 8:13) ዳንኤል ይህ ቅዱስ ስፍራ “የመቅደሱ [የይሖዋ መቅደስ] ቋሚ ስፍራ” መሆኑንም በመግለጽ እንዲህ ብሏል:- “እርሱም [ይሖዋ] የዘወትሩ መሥዋዕት ቀረበት፤ የመቅደሱም ቋሚ ስፍራ ተጣለ። ከዚያም ከኃጢአት የተነሣ ሠራዊት ከዘወትሩ መሥዋዕት ጋር አልፎ ተሰጠ፤ እርሱም እውነትን ወደ ምድሩ ጣለ፣ አደረገም ተከናወነም።” (ዳንኤል 8:11, 12 NW) ይህ ነገር ፍጻሜውን ያገኘው እንዴት ነው?

      22. በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት ሰባተኛው የዓለም ኃይል ጉልህ “ኃጢአት” የፈጸመው እንዴት ነው?

      22 የይሖዋ ምሥክሮች በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት የነበሩበት ሁኔታ ምን ይመስላል? ከባድ ስደት ደርሶባቸዋል! ስደቱ የጀመረው በናዚና በፋሽስት አገሮች ነበር። ይሁን እንጂ ብዙም ሳይቆይ ‘ትንሹ ቀንድ ኃያልነቱ ገንኖበት በነበረው የግዛት ክልል’ ሁሉ ‘እውነት ወደ ምድር ተጣለ።’ የመንግሥቱ አዋጅ ነጋሪዎች “ሠራዊት” እንዲሁም ‘ምሥራቹን’ የመስበክ ሥራቸው በብሪታንያ የኮመንዌልዝ አገሮች በሙሉ ለማለት ይቻላል ታግዶ ነበር። (ማርቆስ 13:10) እነዚህ ብሔራት ዜጎቻቸውን ለብሔራዊ ግዳጅ ሲመለምሉ የይሖዋ ምሥክሮች እንደ ሃይማኖታዊ አገልግሎት ሰጭዎች ታይተው ከግዴታ ነፃ እንዲሆኑ ለማድረግ ፈቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተዋል። ይህም ምሥክሮቹ የአምላክ አገልጋዮች እንዲሆኑ ለተሰጣቸው ሥራ ብሔራቱ ምንም አክብሮት እንደሌላቸው የሚያሳይ ነበር። በዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ የነበሩት የይሖዋ የታመኑ አገልጋዮች የሕዝብ ዓመፅና የተለያዩ ውርደት ደርሶባቸዋል። ሰባተኛው የዓለም ኃይል ሕዝቦቹ ለይሖዋ ዘወትር የሚያቀርቡትንና እንደ ‘ዘወትር መሥዋዕት’ የሚታየውን የምሥጋና መሥዋዕት ማለትም “የከንፈሮችን ፍሬ” ለማስቀረት የሞከረ ያህል ነበር። (ዕብራውያን 13:15) በዚህ መንገድ ይህ የዓለም ኃይል ለልዑሉ አምላክ የሚገባውን “የመቅደሱን ቋሚ ስፍራ” በመውረር “ኃጢአት” ሠርቷል።

      23. (ሀ) በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት የአንግሎ አሜሪካ የዓለም ኃይል ‘የልዑላንን ልዑል’ የተገዳደረው እንዴት ነው? (ለ) ‘የልዑላን ልዑል’ የተባለው ማን ነው?

      23 ትንሹ ቀንድ በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት ‘በቅዱሳኑ’ ላይ ስደት በማስነሣት ‘እስከ ሠራዊት አለቃ ድረስ ራሱን ከፍ አድርጓል።’ ወይም መልአኩ ገብርኤል እንዳለው ‘የልዑላንን ልዑል’ ተገዳድሯል። (ዳንኤል 8:11, 25 የ1980 ትርጉም) ‘የልዑላን ልዑል’ የሚለው ማዕረግ የሚያገለግለው ለይሖዋ አምላክ ብቻ ነው። “ልዑል” ተብሎ የተተረጎመው ሳር የሚለው የዕብራይስጥ ቃል “የበላይ መሆን” የሚል ትርጉም ካለው ግሥ ጋር የሚዛመድ ነው። ቃሉ የንጉሥን ልጅ ወይም የንጉሣዊ ቤተሰብ አባል የሆነን ሰው ከማመልከቱም ሌላ አንድን አዛዥ ወይም አለቃ ሊያመለክት ይችላል። የዳንኤል መጽሐፍ እንደ ሚካኤል ስላሉ ሌሎች መላእክታዊ አለቆችም ይጠቅሳል። አምላክ የእነዚህ ሁሉ ልዑላን ልዑል ነው። (ዳንኤል 10:13, 21፤ ከ⁠መዝሙር 83:18 ጋር አወዳድር።) በእርግጥ የልዑላን ልዑል የሆነውን ይሖዋን ሊገዳደር የሚችል ይኖራል ብለን ልናስብ እንችላለንን?

      ወደ ትክክለኛ ሁኔታው የተመለሰ “ቅዱስ ስፍራ”

      24. ዳንኤል 8:14 ምን ማረጋገጫ ይሰጠናል?

      24 ሌላው ቀርቶ እንደ አንግሎ አሜሪካ የዓለም ኃይል ያለ ‘አስፈሪ’ ንጉሥም እንኳ ቢሆን የልዑላን ልዑል የሆነውን ይሖዋን ሊገዳደር የሚችል አይኖርም! ይህ ንጉሥ የአምላክን መቅደስ ወና ለማስቀረት ቢሞክርም አይሳካለትም። መልእክተኛው መልአክ እንዳለው “ከሁለት ሺህ ሦስት መቶ ማታና ጠዋት በኋላ ቅዱሱ ስፍራ ወደ ትክክለኛው ሁኔታ ይመለሳል።”—ዳንኤል 8:13, 14፤ ዘ ኒው ኢንግሊሽ ባይብል

  • የልዑላንን ልዑል ሊገዳደር የሚችል ማን ነው?
    የዳንኤልን ትንቢት በትኩረት ተከታተል!
    • 27. ስደት በሞላባቸው የሁለተኛው የዓለም ጦርነት ዓመታት ወቅት ‘የዘወትር መሥዋዕቱ’ ተስተጓጉሎ እንደነበር የሚያሳይ ምን ማስረጃ አለ?

      27 እነዚህ 2,300 ቀናት በሂደት ላይ በነበሩበት ወቅት ማለትም በ1939 የጀመረው ሁለተኛው የዓለም ጦርነት ሲካሄድ በአምላክ መቅደስ የሚቀርበው ‘የዘወትሩ መሥዋዕት’ በስደት ምክንያት በእጅጉ ተስተጓጉሎ ነበር። በ1938 የመጠበቂያ ግንብ ማኅበር በዓለም ዙሪያ የይሖዋ ምሥክሮችን ሥራ በበላይነት የሚከታተሉ 39 ቅርንጫፍ ቢሮዎች የነበሩት ሲሆን በ1943 ግን 21 ብቻ ሆነው ነበር። በዚህ መሃል የነበረው የአስፋፊዎች ጭማሪም እጅግ አነስተኛ ነበር።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ