የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • የመጽሐፍ ቅዱስ መጽሐፍ ቁጥር 16—ነህምያ
    “ቅዱሳት መጻሕፍት ሁሉ” ትክክለኛና ጠቃሚ ናቸው፣ ጥራዝ 14
    • 4 የነህምያ መጽሐፍ ከቀሩት በመንፈስ አነሳሽነት የተጻፉ ቅዱሳን ጽሑፎች ጋር ሙሉ በሙሉ ስለሚስማማ የቅዱሳን ጽሑፎች ክፍል መሆኑ አያጠያይቅም። ስለ ሕጉ በተዘዋዋሪ መንገድ ያወሳባቸው በርካታ ቦታዎች ያሉ ሲሆን ከእነዚህም መካከል ከባዕድ አገር ሰዎች ጋር ትዳር መመሥረትን (ዘዳ. 7:3፤ ነህ. 10:30)፣ ብድርን (ዘሌ. 25:35-38፤ ዘዳ. 15:7-11፤ ነህ. 5:2-11) እንዲሁም የዳስ በዓልን (ዘዳ. 31:10-13፤ ነህ. 8:14-18) ስለመሳሰሉት ጉዳዮች የጠቀሳቸው ነጥቦች ይገኙበታል። ከዚህም በላይ መጽሐፉ ኢየሩሳሌም ተቃውሞ ባለበትና “በመከራ ጊዜ” እንደምትሠራ የሚገልጸው የዳንኤል ትንቢት ፍጻሜ ማግኘት የሚጀምርበትን ጊዜ ይጠቁማል።—ዳን. 9:25

      5 ነህምያ የከተማዋን ቅጥር ለመገንባት ወደ ኢየሩሳሌም ስለተጓዘበት ዓመት ይኸውም ስለ 455 ከክርስቶስ ልደት በፊትስ ምን ማለት ይቻላል? ከግሪክ፣ ከፋርስ እና ከባቢሎን የተገኙ አስተማማኝ የታሪክ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት አርጤክስስ ወደ ዙፋን የወጣው (accession year) በ475 ከክርስቶስ ልደት በፊት ሲሆን የግዛት ዘመኑ (regnal year) መቆጠር የጀምረው ደግሞ በ474 ከክርስቶስ ልደት በፊት ነው።a በዚህ መሠረት 20ኛው የግዛት ዘመኑ 455 ከክርስቶስ ልደት በፊት ይሆናል ማለት ነው። ነህምያ 2:1-8 እንደሚጠቁመው የንጉሡ ጠጅ አሳላፊ የሆነው ነህምያ ኢየሩሳሌምን፣ ቅጥሯንና በሮቿን ለማደስና መልሶ ለመገንባት ከንጉሡ ፈቃድ ያገኘው በዚህ ዓመት የፀደይ ወቅት ማለትም በአይሁዳውያኑ አቆጣጠር በኒሳን ወር ነበር። የዳንኤል ትንቢት “ኢየሩሳሌምን ለማደስና ለመጠገን ዐዋጁ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ፣ ገዥው መሲሕ እስከሚመጣበት ጊዜ ድረስ” 69 የዓመታት ሳምንታት ወይም 483 ዓመታት እንደሚያልፉ የተናገረ ሲሆን ኢየሱስ በ29 ከክርስቶስ ልደት በኋላ ሲቀባ ይህ ትንቢት በአስገራሚ ሁኔታ ፍጻሜውን አግኝቷል። ይህ ዓመት ከዓለም የታሪክ ማስረጃዎችም ሆነ ከመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ ጋር ይስማማል።b (ዳን. 9:24-27፤ ሉቃስ 3:1-3, 23) በእርግጥም የነህምያ መጽሐፍና የሉቃስ ወንጌል ይሖዋ አምላክ የእውነተኛ ትንቢት ምንጭና አስፈጻሚ መሆኑን በማሳየት ረገድ ከዳንኤል መጽሐፍ ጋር አስገራሚ በሆነ መንገድ የተሳሰሩ ናቸው! የነህምያ መጽሐፍ በመንፈስ አነሳሽነት የተጻፉት ቅዱሳን ጽሑፎች ክፍል መሆኑ አጠያያቂ አይደለም።

  • ጥናት ቁጥር 3​—በጊዜ ሂደት ውስጥ የተለያዩ ክስተቶች የተፈጸሙበትን ዘመን ማስላት
    “ቅዱሳት መጻሕፍት ሁሉ” ትክክለኛና ጠቃሚ ናቸው፣ ጥራዝ 12
    • [በገጽ 28 ላይ የሚገኝ ሠንጠረዥ]

      ታሪካዊ ክንውኖች የተፈጸሙባቸውን ዘመናት የሚያሳይ ሰንጠረዥ

      ገ. የሚለው “ገደማ” ማለት ነው።

      ጊዜ ክንውን ጥቅስ

      4026 ዓ.ዓ. አዳም ተፈጠረ ዘፍ 2:7

      ከ4026 ዓ.ዓ. የኤደን ቃል ኪዳን፣ ዘፍ 3:15

      በኋላ የመጀመሪያው ትንቢት

      ከ3896 ዓ.ዓ. ቃየን አቤልን ገደለው ዘፍ 4:8

      በፊት

      3896 ዓ.ዓ. ሴት ተወለደ ዘፍ 5:3

      3404 ዓ.ዓ. ጻድቁ ሄኖክ ተወለደ ዘፍ 5:18

      3339 ዓ.ዓ. ማቱሳላ ተወለደ ዘፍ 5:21

      3152 ዓ.ዓ. ላሜህ ተወለደ ዘፍ 5:25

      3096 ዓ.ዓ. አዳም ሞተ ዘፍ 5:5

      3039 ዓ.ዓ. ሄኖክ ተወሰደ፤ ትንቢት ዘፍ 5:23, 24፤ ይሁዳ 14

      የሚናገርበት ዘመን አበቃ

      2970 ዓ.ዓ. ኖኅ ተወለደ ዘፍ 5:28, 29

      2490 ዓ.ዓ. አምላክ የሰውን ዘር በተመለከተ ዘፍ 6:3

      ውሳኔ አስተላለፈ

      2470 ዓ.ዓ. ያፌት ተወለደ ዘፍ 5:32፤ 9:24፤ 10:21

      2468 ዓ.ዓ. ሴም ተወለደ ዘፍ 7:11፤ 11:10

      2370 ዓ.ዓ. ማቱሳላ ሞተ ዘፍ 5:27

      የጥፋት ውኃ ወረደ ዘፍ 7:6, 11

      (በመፀው ወቅት)

      2369 ዓ.ዓ. ከጥፋት ውኃ በኋላ የተደረገው ቃል ኪዳን ዘፍ 8:13፤ 9:16

      2368 ዓ.ዓ. አርፋክስድ ተወለደ ዘፍ 11:10

      ከ2269 ዓ.ዓ. በኋላ የባቤል ግንብ ግንባታ ዘፍ 11:4

      2020 ዓ.ዓ. ኖኅ ሞተ ዘፍ 9:28, 29

      2018 ዓ.ዓ. አብርሃም ተወለደ ዘፍ 11:26, 32፤ 12:4

      1943 ዓ.ዓ. አብርሃም ወደ ከነአን ሲጓዝ ኤፍራጥስን ዘፍ 12:4, 7፤ ዘፀ 12:40፤

      ተሻገረ፤ የአብርሃም ቃል ኪዳን ጸና፤ ገላ 3:17

      እስከ ሕጉ ቃል ኪዳን ድረስ ያለው

      የ430 ዓመት ጊዜ ጀመረ

      ከ1933 ዓ.ዓ. በፊት አብርሃም ሎጥን አዳነው፤ ዘፍ 14:16, 18፤ 16:3

      አብርሃም ከመልከጼዴቅ ጋር ተገናኘ

      1932 ዓ.ዓ. እስማኤል ተወለደ ዘፍ 16:15, 16

      1919 ዓ.ዓ. የግርዘት ቃል ኪዳን ተደረገ ዘፍ 17:1, 10, 24

      ሰዶምና ገሞራ ተፈረደባቸው ዘፍ 19:24

      1918 ዓ.ዓ. ሕጋዊ ወራሽ የሆነው ይስሐቅ ተወለደ፤ ዘፍ 21:2, 5፤ ሥራ 13:17-20

      “450 ዓመት ያህል” የተባለው ጊዜ ጀመረ

      1913 ዓ.ዓ. ይስሐቅ ጡት ጣለ፤ እስማኤል ተሰደደ፤ ዘፍ 21:8፤ 15:13፤ ሥራ 7:6

      የ400 ዓመት የመከራ ጊዜ ጀመረ

      1881 ዓ.ዓ. ሣራ ሞተች ዘፍ 17:17፤ 23:1

      1878 ዓ.ዓ. ይስሐቅና ርብቃ ተጋቡ ዘፍ 25:20

      1868 ዓ.ዓ. ሴም ሞተ ዘፍ 11:11

      1858 ዓ.ዓ. ኤሳውና ያዕቆብ ተወለዱ ዘፍ 25:26

      1843 ዓ.ዓ. አብርሃም ሞተ ዘፍ 25:7

      1818 ዓ.ዓ. ኤሳው የመጀመሪያዎቹን ሁለት ሚስቶቹን አገባ ዘፍ 26:34

      1795 ዓ.ዓ. እስማኤል ሞተ ዘፍ 25:17

      1781 ዓ.ዓ. ያዕቆብ ወደ ካራን ሸሸ፤ ዘፍ 28:2, 13, 19

      በቤቴል ያየው ራእይ

      1774 ዓ.ዓ. ያዕቆብ ሊያን እና ራሔልን አገባ ዘፍ 29:23-30

      1767 ዓ.ዓ. ዮሴፍ ተወለደ ዘፍ 30:23, 24

      1761 ዓ.ዓ. ያዕቆብ ከካራን ወደ ከነአን ተመልሶ ሄደ ዘፍ 31:18, 41

      1761 ዓ.ዓ. ገ. ያዕቆብ ከመልአክ ጋር ታገለ፤ ዘፍ 32:24-28

      እስራኤል ተብሎ ተጠራ

      1750 ዓ.ዓ. የዮሴፍ ወንድሞች፣ ዮሴፍን ለባርነት ሸጡት ዘፍ 37:2, 28

      1738 ዓ.ዓ. ይስሐቅ ሞተ ዘፍ 35:28, 29

      1737 ዓ.ዓ. ዮሴፍ የግብፅ ጠቅላይ ሚኒስትር ተደረገ ዘፍ 41:40, 46

      1728 ዓ.ዓ. ያዕቆብ ከመላ ቤተሰቡ ጋር

      ወደ ግብፅ ሄደ ዘፍ 45:6፤ 46:26፤ 47:9

      1711 ዓ.ዓ. ያዕቆብ ሞተ ዘፍ 47:28

      1657 ዓ.ዓ. ዮሴፍ ሞተ ዘፍ 50:26

      ከ1613 ዓ.ዓ. በፊት ኢዮብ መከራ ደረሰበት ኢዮብ 1:8፤ 42:16

      ከ1600 ዓ.ዓ. በኋላ ግብፅ የመጀመሪያው የዓለም ኃያል ዘፀ 1:8

      መንግሥት ሆነች

      1593 ዓ.ዓ. ሙሴ ተወለደ ዘፀ 2:2, 10

      1553 ዓ.ዓ. ሙሴ የማዳን እርምጃ ወሰደ፤ ዘፀ 2:11, 14, 15፤

      ወደ ምድያም ምድር ሸሸ ሥራ 7:23

      1514 ዓ.ዓ. ገ. ሙሴ በእሳት የተያያዘ ቁጥቋጦ አየ ዘፀ 3:2

      1513 ዓ.ዓ. ፋሲካ፤ እስራኤላውያን ግብፅን ለቀው ወጡ፤ ዘፀ 12:12፤

      ይሖዋ በቀይ ባሕር አዳናቸው የግብፅ መንግሥት ዘፀ 14:27, 29, 30፤

      ኃይል ተዳከመ፤ የ400 ዓመቱ የመከራ ጊዜ አበቃ ዘፍ 15:13, 14

      በሲና ተራራ (ኮሬብ) የሕጉ ቃል ኪዳን ተደረገ ዘፀ 24:6-8

      የአብርሃም ቃል ኪዳን ከጸናበት ጊዜ አንስቶ ገላ 3:17፤ ዘፀ 12:40

      የነበረው የ430 ዓመት ጊዜ አበቃ

      ሙሴ በምድረ በዳ የዘፍጥረት መጽሐፍን አጠናቀረ፤ ዮሐ 5:46

      መጽሐፍ ቅዱስን የመጻፍ ሥራ ተጀመረ

      1512 ዓ.ዓ. የማደሪያ ድንኳኑ ሥራ ተጠናቀቀ ዘፀ 40:17

      የአሮን የክህነት ሥርዓት ተቋቋመ ዘሌ 8:34-36

      ሙሴ ዘፀአትንና ዘሌዋውያንን ጽፎ አጠናቀቀ ዘሌ 27:34፤ ዘኁ 1:1

      1473 ዓ.ዓ. ገ. ሙሴ የኢዮብ መጽሐፍን ጽፎ አጠናቀቀ ኢዮብ 42:16, 17

      1473 ዓ.ዓ. ሙሴ በሞዓብ ሜዳ እያለ ዘኁልቁን ጽፎ አጠናቀቀ ዘኁ 35:1፤ 36:13

      በሞዓብ ከእስራኤል ጋር የተደረገው ቃል ኪዳን ዘዳ 29:1

      ሙሴ ዘዳግምን ጻፈ ዘዳ 1:1, 3

      ሙሴ በሞዓብ በሚገኘው ነቦ ተራራ ላይ ሞተ ዘዳ 34:1, 5, 7

      እስራኤላውያን በኢያሱ እየተመሩ ወደ ከነአን ገቡ ኢያሱ 4:19

      1467 ዓ.ዓ. እስራኤላውያን፣ የምድሪቱን አብዛኛውን ክፍል ተቆጣጠሩ፤ ኢያሱ 11:23፤

      በሐዋርያት ሥራ 13:17-20 ላይ የተጠቀሰው ኢያሱ 14:7, 10-15

      “450 ዓመት ያህል” የተባለው ጊዜ አበቃ፤

      1450 ዓ.ዓ. ገ. የኢያሱ መጽሐፍ ተጽፎ ተጠናቀቀ ኢያሱ 1:1፤ 24:26

      ኢያሱ ሞተ ኢያሱ 24:29

      1117 ዓ.ዓ. ሳሙኤል ሳኦልን የእስራኤል ንጉሥ አድርጎ ሾመው 1ሳሙ 10:24፤

      ሥራ 13:21

      1107 ዓ.ዓ. ዳዊት በቤተልሔም ተወለደ 1ሳሙ 16:1

      1100 ዓ.ዓ. ገ. ሳሙኤል የመሳፍንት መጽሐፍን ጽፎ አጠናቀቀ መሳ 21:25

      1090 ዓ.ዓ. ገ. ሳሙኤል የሩት መጽሐፍን ጽፎ አጠናቀቀ ሩት 4:18-22

      1078 ዓ.ዓ. ገ. የአንደኛ ሳሙኤል መጽሐፍ ተጽፎ ተጠናቀቀ 1ሳሙ 31:6

      1077 ዓ.ዓ. ዳዊት በኬብሮን የይሁዳ ንጉሥ ሆነ 2ሳሙ 2:4

      1070 ዓ.ዓ. ዳዊት በመላው እስራኤል ላይ ንጉሥ ሆነ፤ 2ሳሙ 5:3-7

      ኢየሩሳሌምን ዋና ከተማው አደረጋት

      ከ1070 ዓ.ዓ. በኋላ ታቦቱ ወደ ኢየሩሳሌም ተወሰደ፤ ይሖዋ 2ሳሙ 6:15፤ 7:12-16

      ከዳዊት ጋር የመንግሥት ቃል ኪዳን አደረገ

      1040 ዓ.ዓ. ገ. ጋድ እና ናታን የሁለተኛ ሳሙኤል መጽሐፍን 2ሳሙ 24:18

      ጽፈው አጠናቀቁ

      1037 ዓ.ዓ. ሰለሞን ዳዊትን ተክቶ የእስራኤል ንጉሥ ሆነ 1ነገ 1:39፤ 2:12

      1034 ዓ.ዓ. ሰለሞን ቤተ መቅደሱን መገንባት ጀመረ 1ነገ 6:1

      1027 ዓ.ዓ. በኢየሩሳሌም የተካሄደው የቤተ መቅደስ ግንባታ ተጠናቀቀ 1ነገ 6:38

      1020 ዓ.ዓ. ገ. ሰለሞን መኃልየ መኃልይን ጽፎ አጠናቀቀ መኃ 1:1

      ከ1000 ዓ.ዓ. በፊት ሰለሞን መክብብ መጽሐፍን ጽፎ አጠናቀቀ መክ. 1:1

      997 ዓ.ዓ. ሮብዓም በሰለሞን ምትክ ነገሠ፤ መንግሥቱ ተከፈለ፤ 1 ነገ. 11:43፤

      ኢዮርብዓም የእስራኤል ንጉሥ ሆኖ መግዛት ጀመረ 1 ነገ. 12:19, 20

      993 ዓ.ዓ. ሺሻቅ ይሁዳን ወርሮ ከቤተ መቅደሱ ውድ ነገሮችን ወሰደ 1 ነገ. 14:25, 26

      980 ዓ.ዓ. አብያም (አብያ) በሮብዓም ምትክ የይሁዳ ንጉሥ ሆነ 1 ነገ. 15:1, 2

      977 ዓ.ዓ. አሳ በአብያም ምትክ የይሁዳ ንጉሥ ሆነ 1 ነገ. 15:9, 10

      976 ዓ.ዓ. ገ. ናዳብ በኢዮርብዓም ምትክ የእስራኤል ንጉሥ ሆነ 1 ነገ. 14:20

      975 ዓ.ዓ. ገ. ባኦስ በናዳብ ምትክ የእስራኤል ንጉሥ ሆነ 1 ነገ. 15:33

      952 ዓ.ዓ. ገ. ኤላ በባኦስ ምትክ የእስራኤል ንጉሥ ሆነ 1 ነገ. 16:8

      951 ዓ.ዓ. ገ. ዚምሪ በኤላ ምትክ የእስራኤል ንጉሥ ሆነ 1 ነገ. 16:15

      ኦምሪ እና ቲብኒ በዚምሪ ምትክ የእስራኤል ነገሥታት ሆኑ 1 ነገ. 16:21

      947 ዓ.ዓ. ገ. ኦምሪ ብቻውን የእስራኤል ንጉሥ ሆኖ መግዛት ጀመረ 1 ነገ. 16:22, 23

      940 ዓ.ዓ. ገ. አክዓብ በኦምሪ ምትክ የእስራኤል ንጉሥ ሆነ 1 ነገ. 16:29

      936 ዓ.ዓ. ኢዮሳፍጥ በአሳ ምትክ የይሁዳ ንጉሥ ሆነ 1 ነገ. 22:41, 42

      919 ዓ.ዓ. ገ. አካዝያስ በአክዓብ ምትክ የእስራኤል ንጉሥ ሆነ 1 ነገ. 22:51, 52

      917 ዓ.ዓ. ገ. ኢዮራም በአካዝያስ ምትክ የእስራኤል ንጉሥ ሆነ 2 ነገ. 3:1

      913 ዓ.ዓ. ኢዮራም ‘የይሁዳ ንጉሥ’ ሆኖ ከኢዮሳፍጥ ጋር 2 ነገ. 8:16, 17

      መግዛት ጀመረ

      906 ዓ.ዓ. ገ. አካዝያስ በኢዮራም ምትክ የይሁዳ ንጉሥ ሆነ 2 ነገ. 8:25, 26

      905 ዓ.ዓ. ገ. ንግሥት ጎቶልያ የንግሥና ሥልጣን በመንጠቅ 2 ነገ. 11:1-3

      በይሁዳ ላይ መግዛት ጀመረች

      ኢዩ በኢዮራም ምትክ የእስራኤል ንጉሥ ሆነ 2 ነገ. 9:24, 27፤ 10:36

      898 ዓ.ዓ. ኢዮዓስ በአካዝያስ ምትክ የይሁዳ ንጉሥ ሆነ 2 ነገ. 12:1

      876 ዓ.ዓ. ኢዮዓካዝ በኢዩ ምትክ የእስራኤል ንጉሥ ሆነ 2 ነገ. 13:1

      859 ዓ.ዓ. ገ. ኢዮዓስ በኢዮዓካዝ ምትክ የእስራኤል ንጉሥ ሆነ 2 ነገ. 13:10

      858 ዓ.ዓ. አሜስያስ በኢዮዓስ ምትክ የይሁዳ ንጉሥ ሆነ 2 ነገ. 14:1, 2

      844 ዓ.ዓ. ገ. ዳግማዊ ኢዮርብዓም በኢዮዓስ ምትክ የእስራኤል ንጉሥ ሆነ 2 ነገ. 14:23

      ዮናስ፣ የዮናስ መጽሐፍን ጽፎ አጠናቀቀ ዮናስ 1:1, 2

      829 ዓ.ዓ. ዖዝያ (አዛርያስ) በአሜስያስ ምትክ የይሁዳ ንጉሥ ሆነ 2 ነገ. 15:1, 2

      820 ዓ.ዓ. ገ. የኢዩኤል መጽሐፍ የተጻፈው በዚህ ጊዜ ሳይሆን አይቀርም ኢዩ. 1:1

      804 ዓ.ዓ. ገ. አሞጽ፣ የአሞጽ መጽሐፍን ጽፎ አጠናቀቀ አሞጽ 1:1

      792 ዓ.ዓ. ገ. ዘካርያስ የእስራኤል ንጉሥ ሆነ (6 ወራት) 2 ነገ. 15:8

      791 ዓ.ዓ. ገ. ሻሉም በዘካርያስ ምትክ የእስራኤል ንጉሥ ሆነ 2 ነገ. 15:13, 17

      መናሄም በሻሉም ምትክ የእስራኤል ንጉሥ ሆነ

      780 ዓ.ዓ. ገ. ፈቃህያህ በመናሄም ምትክ የእስራኤል ንጉሥ ሆነ 2 ነገ. 15:23

      778 ዓ.ዓ. ገ. ፋቁሄ በፈቃህያህ ምትክ የእስራኤል ንጉሥ ሆነ 2 ነገ. 15:27

      778 ዓ.ዓ. ገ. ኢሳይያስ የነቢይነት ተልዕኮውን ማከናወን ጀመረ ኢሳ. 1:1፤ 6:1

      777 ዓ.ዓ. ኢዮዓታም በዖዝያ (አዛርያስ) ምትክ የይሁዳ ንጉሥ ሆነ 2 ነገ. 15:32, 33

      761 ዓ.ዓ. ገ. አካዝ በኢዮዓታም ምትክ የይሁዳ ንጉሥ ሆነ 2 ነገ. 16:1, 2

      758 ዓ.ዓ. ገ. ሆሺአ የእስራኤል ንጉሥ ሆኖ መግዛት ጀመረ 2 ነገ. 15:30

      745 ዓ.ዓ. ሕዝቅያስ በአካዝ ምትክ የይሁዳ ንጉሥ ሆነ 2 ነገ. 18:1, 2

      ከ745 ዓ.ዓ. በኋላ ሆሴዕ፣ የሆሴዕ መጽሐፍን ጽፎ አጠናቀቀ ሆሴዕ 1:1

      740 ዓ.ዓ. አሦር እስራኤልን ድል አደረገ፣ ሰማርያን ተቆጣጠረ 2 ነገ. 17:6, 13, 18

      732 ዓ.ዓ. ሰናክሬም ይሁዳን ወረረ 2 ነገ. 18:13

      ከ732 ዓ.ዓ. በኋላ ኢሳይያስ፣ የኢሳይያስ መጽሐፍን ጽፎ አጠናቀቀ ኢሳ. 1:1

      ከ717 ዓ.ዓ. በፊት ሚክያስ፣ የሚክያስ መጽሐፍን ጽፎ አጠናቀቀ ሚክ. 1:1

      717 ዓ.ዓ. ገ. የምሳሌ መጽሐፍን የማጠናቀሩ ሥራ ተጠናቀቀ ምሳሌ 25:1

      716 ዓ.ዓ. ምናሴ በሕዝቅያስ ምትክ የይሁዳ ንጉሥ ሆነ 2 ነገ. 21:1

      661 ዓ.ዓ. አምዖን በምናሴ ምትክ የይሁዳ ንጉሥ ሆነ 2 ነገ. 21:19

      659 ዓ.ዓ. ኢዮስያስ በአምዖን ምትክ የይሁዳ ንጉሥ ሆነ 2 ነገ. 22:1

      ከ648 ዓ.ዓ. በፊት ሶፎንያስ፣ የሶፎንያስ መጽሐፍን ጽፎ አጠናቀቀ ሶፎ. 1:1

      647 ዓ.ዓ. ኤርምያስ የነቢይነት ተልዕኮውን ተቀበለ ኤር. 1:1, 2, 9, 10

      ከ632 ዓ.ዓ. በፊት ናሆም፣ የናሆም መጽሐፍን ጽፎ አጠናቀቀ ናሆም 1:1

      632 ዓ.ዓ. ነነዌ በከለዳውያን እና በሜዶናውያን እጅ ወደቀች ናሆም 3:7

      ባቢሎን የዓለም ኃያል መንግሥት ሆነች

      628 ዓ.ዓ. ኢዮዓካዝ በኢዮስያስ ምትክ የይሁዳ ንጉሥ ሆነ 2 ነገ. 23:31

      ኢዮዓቄም በኢዮዓካዝ ምትክ የይሁዳ ንጉሥ ሆነ 2 ነገ. 23:36

      628 ዓ.ዓ. ገ. ዕንባቆም፣ የዕንባቆም መጽሐፍን ጽፎ አጠናቀቀ ዕን. 1:1

      625 ዓ.ዓ. ናቡከደነጾር (ዳግማዊ) የባቢሎን ንጉሥ ሆነ፤ ኤር. 25:1

      የግዛት ዘመኑ የሚቆጠረው ከ624 ዓ.ዓ. አንስቶ ነው

      620 ዓ.ዓ. ናቡከደነጾር፣ ኢዮዓቄም እንዲገብርለት አደረገ 2 ነገ. 24:1

      618 ዓ.ዓ. ከኢዮዓቄም በኋላ ዮአኪን የይሁዳ ንጉሥ ሆነ 2 ነገ. 24:6, 8

      617 ዓ.ዓ. ናቡከደነጾር፣ የመጀመሪያዎቹን አይሁዳውያን ምርኮኞች ዳን. 1:1-4፤

      ወደ ባቢሎን አጋዘ

      ሴዴቅያስ የይሁዳ ንጉሥ እንዲሆን ተሾመ 2 ነገ. 24:12-18

      613 ዓ.ዓ. ሕዝቅኤል ነቢይ ሆኖ ማገልገል ጀመረ ሕዝ. 1:1-3

      609 ዓ.ዓ. ናቡከደነጾር፣ ለሦስተኛ ጊዜ በይሁዳ ላይ ዘመተ፤ 2 ነገ. 25:1, 2

      በኢየሩሳሌም ላይ ከበባ ማድረግ ጀመረ

      607 ዓ.ዓ. በአምስተኛው ወር (አብ)፣ ቤተ መቅደሱ ተቃጠለ 2 ነገ. 25:8-10፤

      እንዲሁም ኢየሩሳሌም ጠፋች ኤር. 52:12-14

      በሰባተኛው ወር፣ አይሁዳውያን ይሁዳን ትተው ሄዱ፤ 2 ነገ. 25:25, 26፤

      “የተወሰኑት የአሕዛብ ዘመናት” መቆጠር የሚጀምሩት ሉቃስ 21:24

      ከዚህ ጊዜ አንስቶ ነው

      ኤርምያስ፣ ሰቆቃወ ኤርምያስን ጻፈ የሰቆቃወ

      ኤርምያስ መግቢያ፣ ሰብዓ ሊቃናት

      607 ዓ.ዓ. ገ. አብድዩ፣ የአብድዩ መጽሐፍን ጻፈ አብ. 1

      591 ዓ.ዓ. ገ. ሕዝቅኤል፣ የሕዝቅኤል መጽሐፍን ጽፎ አጠናቀቀ ሕዝ. 40:1፤ 29:17

      580 ዓ.ዓ. የአንደኛ እና የሁለተኛ ነገሥት እንዲሁም ኤር. 52:31፤

      የኤርምያስ መጻሕፍት ተጽፈው ተጠናቀቁ 2 ነገ. 25:27

      539 ዓ.ዓ. ባቢሎን በሜዶናውያን እና በፋርሳውያን እጅ ወደቀች፤ ዳን. 5:30, 31

      ሜዶ ፋርስ አራተኛው የዓለም ኃያል መንግሥት ሆነ

      537 ዓ.ዓ. ፋርሳዊው ቂሮስ፣ አይሁዳውያን ወደ ኢየሩሳሌም እንዲመለሱ 2 ዜና 36:22, 23፤

      ያስተላለፈው አዋጅ ተግባራዊ ሆነ፤ ኢየሩሳሌም ባድማ ሆና

      ያሳለፈቻቸው 70 ዓመታት አበቁ ኤር. 25:12፤ 29:10

      536 ዓ.ዓ. ገ. ዳንኤል፣ የዳንኤል መጽሐፍን ጽፎ አጠናቀቀ ዳን. 10:1

      536 ዓ.ዓ. በዘሩባቤል መሪነት የቤተ መቅደሱ መሠረት ተጣለ ዕዝራ 3:8-10

      522 ዓ.ዓ. ቤተ መቅደሱን የመገንባቱ ሥራ ታገደ ዕዝራ 4:23, 24

      520 ዓ.ዓ. ሐጌ፣ የሐጌ መጽሐፍን ጽፎ አጠናቀቀ ሐጌ 1:1

      518 ዓ.ዓ. ዘካርያስ፣ የዘካርያስ መጽሐፍን ጽፎ አጠናቀቀ ዘካ. 1:1

      515 ዓ.ዓ. ዘሩባቤል የሁለተኛውን ቤተ መቅደስ ግንባታ አጠናቀቀ ዕዝራ 6:14, 15

      475 ዓ.ዓ. ገ. መርዶክዮስ፣ የአስቴር መጽሐፍን ጽፎ አጠናቀቀ አስ. 3:7፤ 9:32

      468 ዓ.ዓ. ዕዝራ እና ካህናቱ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ ዕዝራ 7:7

      460 ዓ.ዓ. ገ. ዕዝራ፣ የአንደኛ እና ሁለተኛ ዜና መዋዕል እንዲሁም ዕዝራ 1:1፤

      የዕዝራ መጻሕፍትን ጽፎ አጠናቀቀ፤ 2 ዜና 36:22

      የመዝሙር መጽሐፍን የማጠናቀሩ ሥራ ተጠናቀቀ

      455 ዓ.ዓ. በነህምያ መሪነት የኢየሩሳሌም ቅጥር ተገነባ፤ ነህ. 1:1፤ 2:1, 11፤

      የ70 ሳምንታት ትንቢት ፍጻሜውን ማግኘት ጀመረ ነህ. 6:15፤ ዳን. 9:24

      ከ443 ዓ.ዓ. በኋላ ነህምያ፣ የነህምያ መጽሐፍን ጽፎ አጠናቀቀ ነህ. 5:14

      ሚልክያስ፣ የሚልክያስ መጽሐፍን ጽፎ አጠናቀቀ ሚል. 1:1

      406 ዓ.ዓ. ኢየሩሳሌምን እንደገና የመገንባቱ ሥራ እንደተጠናቀቀ ዳን. 9:25

      ከሁኔታዎች መረዳት ይቻላል

      332 ዓ.ዓ. አምስተኛው የዓለም ኃያል መንግሥት የሆነው ግሪክ ዳን. 8:21

      ይሁዳን መግዛት ጀመረ

      280 ዓ.ዓ. ገ. ግሪክኛውን ሰብዓ ሊቃናት የማዘጋጀቱ ሥራ ተጀመረ

      165 ዓ.ዓ. ቤተ መቅደሱ በግሪክ የጣዖት አምልኮ ከረከሰ በኋላ ዮሐ. 10:22

      እንደገና ተወሰነ፤ የመታደስ በዓል

      63 ዓ.ዓ. ስድስተኛው የዓለም ኃያል መንግሥት የሆነው ሮም ዮሐ. 19:15፤

      ኢየሩሳሌምን መግዛት ጀመረ ራእይ 17:10

      37 ዓ.ዓ. ገ. ሄሮድስ (በሮም የተሾመ ንጉሥ) የኃይል እርምጃ በመውሰድ

      ኢየሩሳሌምን በቁጥጥሩ ሥር አደረገ

      2 ዓ.ዓ. አጥማቂው ዮሐንስ እና ኢየሱስ ተወለዱ ሉቃስ 1:60፤ 2:7

      29 ዓ.ም. ዮሐንስ እና ኢየሱስ አገልግሎታቸውን ጀመሩ ሉቃስ 3:1, 2, 23

      33 ዓ.ም. ኒሳን 14፣ ኢየሱስ መሥዋዕት በመሆን ለአዲሱ ቃል ኪዳን ሉቃስ 22:20፤ 23:33

      መሠረት ጣለ፤ ተሰቀለ

      ኒሳን 16፣ ኢየሱስ ከሞት ተነሳ ማቴ. 28:1-10

      ሲዋን 6፣ መንፈስ ቅዱስ ፈሰሰ፤ ጴጥሮስ፣ አይሁዳውያን ሥራ 2:1-17, 38

      በጴንጤቆስጤ ዕለት፣ ወደ ክርስቲያን ጉባኤ መግባት የሚችሉበት መንገድ ከፈተ

      36 ዓ.ም. 70ዎቹ የዓመታት ሳምንታት አበቁ፤ ጴጥሮስ ዳን. 9:24-27፤

      ቆርኔሌዎስ ከተባለው ካልተገረዙት አሕዛብ መካከል ሥራ 10:1, 45

      ወደ ክርስትና ከመጣው የመጀመሪያው ሰው ጋር ተገናኘ

      41 ዓ.ም. ገ. ማቴዎስ፣ የማቴዎስ ወንጌልን ጻፈ

      47-48 ዓ.ም. ገ. ጳውሎስ፣ የመጀመሪያ ሚስዮናዊ ጉዞውን ጀመረ ሥራ 13:1–14:28

      49 ዓ.ም. ገ. የበላይ አካሉ፣ ከአሕዛብ ወገን ለመጡት አማኞች ሥራ 15:28, 29

      ግርዘትን በተመለከተ ውሳኔ አስተላለፈ

      49-52 ዓ.ም. ገ. የጳውሎስ ሁለተኛ ሚስዮናዊ ጉዞ ሥራ 15:36–18:22

      50 ዓ.ም. ገ. ጳውሎስ በቆሮንቶስ ሆኖ 1 ተሰሎንቄን ጻፈ 1 ተሰ. 1:1

      51 ዓ.ም. ገ. ጳውሎስ በቆሮንቶስ ሆኖ 2 ተሰሎንቄን ጻፈ 2 ተሰ. 1:1

      50-52 ዓ.ም. ገ. ጳውሎስ በቆሮንቶስ ወይም በሶርያዋ አንጾኪያ ሆኖ ገላ. 1:1

      ለገላትያ ክርስቲያኖች ደብዳቤ ጻፈ

      52-56 ዓ.ም. ገ. የጳውሎስ ሦስተኛ ሚስዮናዊ ጉዞ ሥራ 18:23–21:19

      55 ዓ.ም. ገ. ጳውሎስ በኤፌሶን ሆኖ 1 ቆሮንቶስን፣ 1 ቆሮ. 15:32፤

      በመቄዶንያ ሆኖ ደግሞ 2 ቆሮንቶስን ጻፈ 2 ቆሮ. 2:12, 13

      56 ዓ.ም. ገ. ጳውሎስ በቆሮንቶስ ሆኖ ለሮም ክርስቲያኖች ደብዳቤ ጻፈ ሮም 16:1

      56-58 ዓ.ም. ገ. ሉቃስ፣ የሉቃስ ወንጌልን ጻፈ ሉቃስ 1:1, 2

      60-61 ዓ.ም. ገ. ጳውሎስ በሮም ሆኖ የሚከተሉትን ደብዳቤዎች ጻፈ፦

      ኤፌሶን ኤፌ. 3:1

      ፊልጵስዩስ ፊልጵ. 4:22

      ቆላስይስ ቆላ. 4:18

      ፊልሞና ፊልሞና 1

      61 ዓ.ም. ገ. ጳውሎስ በሮም ሆኖ ለዕብራውያን ክርስቲያኖች ደብዳቤ ጻፈ ዕብ. 13:24፤ 10:34

      ሉቃስ በሮም ሆኖ የሐዋርያት ሥራ መጽሐፍን ጽፎ አጠናቀቀ

      ከ62 ዓ.ም. በፊት የኢየሱስ ወንድም የሆነው ያዕቆብ በኢየሩሳሌም ሆኖ ያዕ. 1:1

      “ያዕቆብ” በሚል ስም የሚጠራውን ደብዳቤውን ጻፈ

      60-65 ዓ.ም. ገ. ማርቆስ፣ የማርቆስ ወንጌልን ጻፈ

      61-64 ዓ.ም. ገ. ጳውሎስ በመቄዶንያ ሆኖ 1 ጢሞቴዎስን ጻፈ 1 ጢሞ. 1:3

      ጳውሎስ በመቄዶንያ (?) ሆኖ ቲቶን ጻፈ ቲቶ 1:5

      62-64 ዓ.ም. ገ. ጴጥሮስ በባቢሎን ሆኖ 1 ጴጥሮስን ጻፈ 1 ጴጥ. 1:1፤ 5:13

      64 ዓ.ም. ገ. ጴጥሮስ በባቢሎን (?) ሆኖ 2 ጴጥሮስን ጻፈ 2 ጴጥ. 1:1

      65 ዓ.ም. ገ. ጳውሎስ በሮም ሆኖ 2 ጢሞቴዎስን ጻፈ 2 ጢሞ. 4:16-18

      የኢየሱስ ወንድም የሆነው ይሁዳ፣ ይሁዳ 1, 17, 18

      “ይሁዳ” ተብሎ የሚጠራውን ደብዳቤ ጻፈ

      70 ዓ.ም. ሮማውያን ኢየሩሳሌምን እና ቤተ መቅደሷን አጠፉ ዳን. 9:27፤

      ማቴ. 23:37, 38፤

      ሉቃስ 19:42-44

      96 ዓ.ም. ገ. ዮሐንስ በጳጥሞስ ሳለ የራእይ መጽሐፍን ጻፈ ራእይ 1:9

      98 ዓ.ም. ገ. ዮሐንስ፣ የዮሐንስ ወንጌልን እንዲሁም ዮሐ. 21:22, 23

      1፣ 2 እና 3 ዮሐንስ ተብለው የሚጠሩትን ደብዳቤዎች ጻፈ፤

      መጽሐፍ ቅዱስ ተጽፎ ተጠናቀቀ

      100 ዓ.ም. ገ. በሕይወት የነበረው የመጨረሻው ሐዋርያ ማለትም ዮሐንስ ሞተ 2 ተሰ. 2:7

      ማሳሰቢያ፦ በሠንጠረዡ ውስጥ የተጠቀሱት አብዛኞቹ ዓመታት ትክክለኛውን ጊዜ የሚጠቁሙ ቢሆንም አንዳንዶቹ ዓመታት ግን ካለው ማስረጃ አንጻር ሊሆን ይችላል ተብሎ የተገመተውን ጊዜ የሚያመለክቱ ናቸው። በዚህ ሠንጠረዥ ውስጥ የተጠቀሱት ጊዜያት ሊለወጡ የማይችሉ አይደሉም፤ ከዚህ ይልቅ ይህ ሠንጠረዥ የተዘጋጀው የመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪዎች ክንውኖቹ በየትኛው ጊዜ ላይ እንደተፈጸሙ እንዲሁም በእነዚህ ጊዜያት መካከል ያለውን ተዛማጅነት እንዲያስተውሉ ለመርዳት ታስቦ ነው።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ