የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • መሲሑ የሚመጣበት ጊዜ ታወቀ
    የዳንኤልን ትንቢት በትኩረት ተከታተል!
    • 23. ‘አለቃው መሲሕ’ መሞት የነበረበት ለምንድን ነው? ይህስ የሚሆነው መቼ ነበር?

      23 በ70ኛው ሳምንት ላይ መከናወን የነበረበት ነገር ምንድን ነው? ገብርኤል ‘ሰባ ሳምንት’ የተቀጠረው “መተላለፍን ያስቀር፣ ኃጢአትንም ወደ ፍጻሜው ያመጣ፣ በደልንም ያስተሰርይ፣ የዘላለምንም ጽድቅ ያገባ፣ ራእይንና ነቢይን ያትም፣ ቅዱሰ ቅዱሳንንም ይቀባ ዘንድ” ነው ሲል ተናግሯል። ይህን ሁሉ ለማከናወን ‘አለቃው መሢሕ’ መሞት ነበረበት። መቼ? ገብርኤል እንዲህ ብሏል:- “ከስድሳ ሁለት ጊዜ ሰባትም በኋላ መሢሕ ይገደላል፣ በእርሱም ዘንድ ምንም የለም፤ . . . እርሱም ከብዙ ሰዎች ጋር ጽኑ ቃል ኪዳን ለአንድ ሱባዔ ያደርጋል፤ በሱባዔውም እኩሌታ መሥዋዕቱንና ቁርባኑን ያስቀራል።” (ዳንኤል 9:26ሀ [NW], 27ሀ) ወሳኝ የሆነው ጊዜ፤ ‘የሣምንቱ እኩሌታ’ ነው። ይህም የመጨረሻው የዓመታት ሳምንት አጋማሽ ነው።

      24, 25. (ሀ) በትንቢት በተነገረው መሠረት ክርስቶስ የሞተው መቼ ነው? የእርሱ ሞትና ትንሣኤስ ምን ነገር ወደ ፍጻሜው እንዲመጣ አድርጓል? (ለ) የኢየሱስ ሞት ምን ነገር አከናውኗል?

      24 የኢየሱስ ክርስቶስ ሕዝባዊ አገልግሎት የጀመረው በ29 እዘአ መገባደጃ ላይ ሲሆን ለሦስት ዓመት ተኩል ያህል ቀጥሏል። በትንቢት በተነገረው መሠረት ክርስቶስ በ33 እዘአ በመከራ እንጨት ላይ ተሰቅሎ ‘በተገደለ’ ጊዜ ሰብዓዊ ሕይወቱን ለሰው ልጆች ቤዛ አድርጎ ሰጥቷል። (ኢሳይያስ 53:8፤ ማቴዎስ 20:28) ትንሣኤ ያገኘው ኢየሱስ የሰብዓዊ ሕይወቱን መሥዋዕት ዋጋ በሰማይ ለአምላክ ካቀረበ በኋላ የእንስሳ መሥዋዕትና ቁርባን የማቅረቡ አስፈላጊነት ቀርቷል። የአይሁድ ካህናት በ70 እዘአ የኢየሩሳሌም ቤተ መቅደስ እስከ ጠፋበት ጊዜ ድረስ የእንስሳ መሥዋዕት ያቀርቡ የነበረ ቢሆንም እንዲህ ዓይነቶቹ መሥዋዕቶች በአምላክ ፊት ተቀባይነት አጡ። ዳግመኛ መቅረብ በማያስፈልገው የተሻለ መሥዋዕት ተተኩ። ሐዋርያው ጳውሎስ እንዲህ ሲል ጽፏል:- “[ክርስቶስ] ግን ስለ ኃጢአት አንድን መሥዋዕት ለዘላለም . . .፣ አንድ ጊዜ በማቅረብ የሚቀደሱትን የዘላለም ፍጹማን አድርጎአቸዋልና።”—ዕብራውያን 10:12, 14

  • መሲሑ የሚመጣበት ጊዜ ታወቀ
    የዳንኤልን ትንቢት በትኩረት ተከታተል!
    • 26. (ሀ) የሕጉ ቃል ኪዳን ተወግዶ የነበረ ቢሆንም ‘ለአንድ ሳምንት የጸናው ቃል ኪዳን’ የትኛው ነው? (ለ) በሰባኛው ሳምንት መጨረሻ ላይ ምን ነገር ተከናውኗል?

      26 በመሆኑም ይሖዋ በክርስቶስ ሞት አማካኝነት በ33 እዘአ የሕጉን ቃል ኪዳን አስወግዶታል። ታዲያ መሲሑ “ከብዙ ሰዎች ጋር ጽኑ ቃል ኪዳን ለአንድ ሱባዔ” ያደርጋል ሊባል የሚችለው እንዴት ነው? የአብርሃምን ቃል ኪዳን በማጽናቱ ነው። ሰባኛው ሳምንት እስኪጠናቀቅ ድረስ አምላክ የዚህን ቃል ኪዳን በረከት ለዕብራውያኑ የአብርሃም ዝርያዎች ዘርግቶላቸው ነበር። ይሁን እንጂ ‘በሰባው ሳምንት’ ማብቂያ ላይ ማለትም በ36 እዘአ ሐዋርያው ጴጥሮስ የአምልኮ ፍቅር ለነበረው ለኢጣሊያዊው ቆርኔሌዎስና ለቤተሰቦቹ እንዲሁም ለሌሎች አሕዛብ ሰብኳል። ከዚያ ዕለት አንስቶ ምሥራቹ በአሕዛብ ሁሉ ዘንድ መታወጅ ጀምሯል።—ሥራ 3:25, 26፤ 10:1-48፤ ገላትያ 3:8, 9, 14

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ