የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ከአምላክ ዘንድ የመጣ መልእክተኛ አበረታው
    የዳንኤልን ትንቢት በትኩረት ተከታተል!
    • 7. ዳንኤል ሦስት ሳምንት ሙሉ ምን አደረገ?

      7 ዘገባው እንዲህ ይላል:- “በዚያም ወራት እኔ ዳንኤል ሦስ⁠ት ሳምንት ሙሉ ሳዝን ነበርሁ። ማለፊያ እንጀራም አልበላሁም፣ ሥጋና ጠጅም በአፌ አልገባም፣ ሦስቱም ሳምንት እስኪፈጸም ድረስ ዘይት አልተቀባሁም።” (ዳንኤል 10:2, 3) “ሦስት ሳምንት ሙሉ” ወይም 21 ቀናት ማዘንና መጾም ቀላል አይደለም። ጾሙና ሐዘኑ ያበቃው ‘በመጀመሪያው ወር በሃያ አራተኛው ቀን’ ይመስላል። (ዳንኤል 10:4) በመሆኑም ዳንኤል የጾመበት ወቅት በመጀመሪያው የኒሳን ወር 14ኛ ቀን የሚከበረውን የማለፍ በዓልና ከዚያ ጋር ተያይዞ የሚመጣውን የሰባት ቀናት የቂጣ በዓል የሚጨምር ነበር።

  • ከአምላክ ዘንድ የመጣ መልእክተኛ አበረታው
    የዳንኤልን ትንቢት በትኩረት ተከታተል!
    • 9, 10. (ሀ) ዳንኤል ራእዩ ሲመጣለት የት ነበር? (ለ) ዳንኤል በራእይ ያየው ነገር ምን እንደሆነ ግለጽ።

      9 ዳንኤል በተስፋ መቁረጥ አልተዋጠም። ቀጥሎ ስለሆነው ነገር እንዲህ በማለት ይነግረናል:- “ጤግሮስ [“ሂዴኬል፣” NW] በተባለው በታላቁ ወንዝ አጠገብ ሳለሁ፣ ዓይኔን አነሣሁ፣ እነሆም፣ በፍታ የለበሰውን ጥሩም የአፌዝን ወርቅ በወገቡ ላይ የታጠቀውን ሰው አየሁ።” (ዳንኤል 10:4, 5) ሂዴኬል ከኤደን ገነት ይወጡ ከነበሩት አራት ወንዞች መካከል አንዱ ነው። (ዘፍጥረት 2:10-14) በጥንቷ ፋርስ ሂዴኬል የሚታወቀው ጤግራ በመባል ሲሆን ጤግሮስ ከሚለው የግሪክኛ ስም የተገኘ ነው። በሂዴኬልና በኤፍራጥስ ወንዝ መካከል ያለው ቦታ መሶጴጣሚያ ተብሎ የሚጠራ ሲሆን ትርጉሙም “በሁለት ወንዞች መካከል ያለ ቦታ” ማለት ነው። ይህም ዳንኤል ራእዩን ሲቀበል በባቢሎን ከተማ ላይሆን ቢችልም በባቢሎንያ ምድር እንደነበር ያረጋግጣል።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ