የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ከአምላክ ዘንድ የመጣ መልእክተኛ አበረታው
    የዳንኤልን ትንቢት በትኩረት ተከታተል!
    • 17, 18. ዳንኤል ለሁለተኛ ጊዜ እርዳታ ያገኘው እንዴት ነው? ይህስ ምን እንዲያደርግ አስችሎታል?

      17 ዳንኤል እንዲህ ያለ ስሜት ቀስቃሽ መልእክት ሊነገረው መሆኑን ሲሰማ ልቡ አልተንጠለጠለም። ይልቁንም የሰማው ነገር አስደነገጠው። ዘገባው እንዲህ ይላል:- “ይህንም ቃል በተናገረኝ ጊዜ ፊቴን ወደ ምድር አቀረቀርሁ፣ ዲዳም ሆንሁ።” ነገር ግን ተልኮ የመጣው መልአክ ዳንኤልን ለሁለተኛ ጊዜ በፍቅር ሊረዳው ፈቃደኛ ነበር። ዳንኤል እንዲህ ይላል:- “እነሆም፣ የሰው ልጅ የሚመስል ከንፈሬን ዳሰሰኝ፤ የዚያን ጊዜም አፌን ከፍቼ ተናገርሁ።”b—ዳንኤል 10:15, 16⁠ሀ

      18 ዳንኤል መልአኩ ከንፈሩን ሲዳስስለት ብርታት አግኝቷል። (ከ⁠ኢሳይያስ 6:7 ጋር አወዳድር።) የመናገር ችሎታው የተመለሰለት ዳንኤል ምን ያህል እንደተቸገረ ለተላከው መልአክ ማስረዳት ችሎ ነበር። ዳንኤል እንዲህ አለ:- “ጌታዬ ሆይ፣ ከራእዩ የተነሣ ሕመሜ መጣብኝ፣ ኃይልም አጣሁ። ይህ የጌታዬ ባሪያ ከዚህ ከጌታዬ ጋር ይናገር ዘንድ እንዴት ይችላል? አሁንም ኃይል አጣሁ፣ እስትንፋስም አልቀረልኝም አልሁት።”—ዳንኤል 10:16⁠ለ, 17

      19. ዳንኤል ለሦስተኛ ጊዜ እርዳታ ያገኘው እንዴት ነው? ከምንስ ውጤት ጋር?

      19 ዳንኤል የገጠመውን ችግር መግለጹ እንጂ ማጉረምረሙ ወይም ሰበብ መፍጠሩ አልነበረም። መልአኩም ሐሳቡን ተቀብሎታል። በመሆኑም የተላከው መልአክ ዳንኤልን ለሦስተኛ ጊዜ ረዳው። ነቢዩ “ደግሞ ሰው የሚመስል ዳሰሰኝ፣ አበረታኝም” ብሏል። ዳበስ አድርጎት ኃይል ካገኘ በኋላ መልእክተኛው እነዚህን የሚያጽናኑ ቃላት ተናገረ:- “እጅግ የተወደድህ ሰው ሆይ፣ አትፍራ፤ ሰላም ለአንተ ይሁን፤ በርታ፣ ጽና።” ዳንኤል የሚያስፈልገው ይህን በመሰለ ፍቅራዊ መንገድ ዳሰስ የሚያደርገውና በሚያጽናኑ ቃላት የሚናገረው ሰው የነበረ ይመስላል። ውጤቱስ ምን ሆነ? ዳንኤል እንዲህ ሲል ገልጾታል:- “በተናገረኝም ጊዜ በረታሁና:- አበርትተኸኛልና ጌታዬ ይናገር አልሁ።” ከዚህ በኋላ ዳንኤል ከፊቱ ለሚጠብቀው ፈታኝ ኃላፊነት ተዘጋጅቶ ነበር።—ዳንኤል 10:18, 19

  • ከአምላክ ዘንድ የመጣ መልእክተኛ አበረታው
    የዳንኤልን ትንቢት በትኩረት ተከታተል!
    • b የዳንኤልን አፍ የዳሰሰው ከዳንኤል ጋር ሲነጋገር የነበረው መልአክ ራሱ ሊሆን ቢችልም እዚህ ቁጥር ላይ ከገባው አገላለጽ አንጻር ሌላ መልአክ ምናልባትም ገብርኤል ሊሆን ይችላል። ያም ሆነ ይህ ተልኮ የመጣ አንድ መልአክ ዳንኤልን አበርትቶታል።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ