-
‘የሰሜኑ ንጉሥ’ በፍጻሜው ዘመንመጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2020 | ግንቦት
-
-
8. በመጨረሻዎቹ ቀናት የደቡቡ ንጉሥ የሆነው ማን ነው?
8 በአንደኛው የዓለም ጦርነት ወቅት ዩናይትድ ስቴትስ እና ብሪታንያ ከፍተኛ ኃይል ያለው ወታደራዊ ጥምረት መሠረቱ። በዚህ ጊዜ ብሪታንያና የቀድሞ ቅኝ ግዛቷ የሆነችው ዩናይትድ ስቴትስ የአንግሎ አሜሪካ የዓለም ኃያል መንግሥት ሆኑ። ዳንኤል በትንቢት እንደተናገረው ይህ ንጉሥ “እጅግ ታላቅና ኃያል የሆነ ሠራዊት” ሰብስቦ ነበር። (ዳን. 11:25) በመጨረሻዎቹ ቀናት የአንግሎ አሜሪካ ጥምር ኃይል የደቡቡ ንጉሥ ሆኖ ቀጥሏል።c ይሁንና የሰሜኑ ንጉሥ የሆነውስ ማን ነው?
የሰሜኑ ንጉሥ በድጋሚ ብቅ አለ
9. የሰሜኑ ንጉሥ በድጋሚ ብቅ ያለው መቼ ነው? ዳንኤል 11:25 ፍጻሜውን ያገኘውስ እንዴት ነው?
9 በ1871 ማለትም ራስል እና አጋሮቹ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ቡድን ካቋቋሙ ከአንድ ዓመት በኋላ የሰሜኑ ንጉሥ በድጋሚ ብቅ አለ። በዚህ ዓመት ኦቶ ቮን ቢስማርክ፣ የተለያዩ ክልሎችን አንድ በማድረግ ኃያል የሆነ የጀርመን ግዛት እንዲቋቋም አደረገ። የጀርመኑ ንጉሥ ቀዳማዊ ቪልሄልም የዚህ ግዛት የመጀመሪያ ንጉሠ ነገሥት ሆነ፤ ንጉሠ ነገሥቱ፣ ቢስማርክን የመጀመሪያው መራሄ መንግሥት አድርጎ ሾመው።d በቀጣዮቹ ጥቂት አሥርተ ዓመታት የጀርመን መንግሥት፣ በአፍሪካ እና በፓስፊክ ውቅያኖስ ላይ የሚገኙ አገሮችን በቅኝ ግዛት የተቆጣጠረ ሲሆን ብሪታንያን መቀናቀን ጀምሮ ነበር። (ዳንኤል 11:25ን አንብብ።) የጀርመን ንጉሠ ነገሥታዊ አገዛዝ ጠንካራ ሠራዊት የገነባ ከመሆኑም ሌላ የባሕር ኃይሉ በዓለም ላይ ሁለተኛውን ደረጃ ይዞ ነበር። በአንደኛው የዓለም ጦርነት ወቅት የጀርመን መንግሥት ይህን ሠራዊት ጠላቶቹን ለማጥቃት ተጠቅሞበታል።
10. ዳንኤል 11:25ለ, 26 ፍጻሜውን ያገኘው እንዴት ነው?
10 በመቀጠል ዳንኤል የጀርመን ንጉሠ ነገሥታዊ ግዛትና የገነባው ወታደራዊ ኃይል ምን እንደሚደርስበት ገልጿል። ትንቢቱ፣ የሰሜኑን ንጉሥ በተመለከተ “መቋቋም አይችልም” በማለት ይናገራል። ለምን? ምክንያቱም ‘ሴራ ይጠነስሱበታል’፤ “የእሱን ምርጥ ምግብ የሚበሉም ለውድቀት ይዳርጉታል።” (ዳን. 11:25ለ, 26ሀ) በዳንኤል ዘመን “[ለንጉሡ] ከሚቀርበው ምርጥ ምግብ” ከሚበሉት መካከል “ንጉሡን ለማገልገል” የተሰማሩ ሰዎች ይገኙበታል። (ዳን. 1:5) ታዲያ ይህ ትንቢት የሚናገረው ስለ እነማን ነው? ትንቢቱ የሚናገረው የንጉሠ ነገሥቱን ጄኔራሎች እና የጦር አማካሪዎች ጨምሮ በጀርመን ንጉሠ ነገሥታዊ አገዛዝ ውስጥ ከፍተኛ ሥልጣን ስለነበራቸው ሰዎች ነው፤ እነዚህ ሰዎች ውሎ አድሮ ንጉሠ ነገሥታዊ አገዛዙ እንዲወድቅ አድርገዋል።e ትንቢቱ፣ ንጉሠ ነገሥታዊ አገዛዙ እንደሚወድቅ ከመግለጽ ባለፈ የሰሜኑ ንጉሥ ከደቡቡ ንጉሥ ጋር የሚያደርገው ጦርነት ውጤት ምን እንደሚሆን ይናገራል። ስለ ሰሜኑ ንጉሥ ሲናገር “ሠራዊቱ ተጠራርጎ ይወሰዳል፤ ብዙዎችም ተገድለው ይወድቃሉ” ይላል። (ዳን. 11:26ለ) ልክ በትንቢት በተነገረው መሠረት በአንደኛው የዓለም ጦርነት ወቅት የጀርመን ሠራዊት ‘ተጠራርጎ የተወሰደ’ ሲሆን ብዙ ሰዎች ‘ተገድለው ወድቀዋል።’ ይህ ጦርነት እስከዚያ ጊዜ ድረስ ከተካሄዱ ጦርነቶች ሁሉ በርካታ ሰው ያለቀበት ነው።
-
-
‘የሰሜኑ ንጉሥ’ በፍጻሜው ዘመንመጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2020 | ግንቦት
-
-
e እነዚህ ሰዎች፣ የንጉሠ ነገሥታዊ አገዛዙን ውድቀት ለማፋጠን የተለያዩ ነገሮችን አድርገዋል። ለምሳሌ ያህል፣ ለንጉሡ የሚሰጡትን ድጋፍ አቁመዋል፤ ስለ ጦርነቱ በሚስጥር ሊያዙ የሚገቡ መረጃዎችን አውጥተዋል፤ እንዲሁም ንጉሡ ሥልጣኑን እንዲለቅ ጫና አሳድረዋል።
-