የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ‘የሰሜኑ ንጉሥ’ በፍጻሜው ዘመን
    መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2020 | ግንቦት
    • 10. ዳንኤል 11:25ለ, 26 ፍጻሜውን ያገኘው እንዴት ነው?

      10 በመቀጠል ዳንኤል የጀርመን ንጉሠ ነገሥታዊ ግዛትና የገነባው ወታደራዊ ኃይል ምን እንደሚደርስበት ገልጿል። ትንቢቱ፣ የሰሜኑን ንጉሥ በተመለከተ “መቋቋም አይችልም” በማለት ይናገራል። ለምን? ምክንያቱም ‘ሴራ ይጠነስሱበታል’፤ “የእሱን ምርጥ ምግብ የሚበሉም ለውድቀት ይዳርጉታል።” (ዳን. 11:25ለ, 26ሀ) በዳንኤል ዘመን “[ለንጉሡ] ከሚቀርበው ምርጥ ምግብ” ከሚበሉት መካከል “ንጉሡን ለማገልገል” የተሰማሩ ሰዎች ይገኙበታል። (ዳን. 1:5) ታዲያ ይህ ትንቢት የሚናገረው ስለ እነማን ነው? ትንቢቱ የሚናገረው የንጉሠ ነገሥቱን ጄኔራሎች እና የጦር አማካሪዎች ጨምሮ በጀርመን ንጉሠ ነገሥታዊ አገዛዝ ውስጥ ከፍተኛ ሥልጣን ስለነበራቸው ሰዎች ነው፤ እነዚህ ሰዎች ውሎ አድሮ ንጉሠ ነገሥታዊ አገዛዙ እንዲወድቅ አድርገዋል።e ትንቢቱ፣ ንጉሠ ነገሥታዊ አገዛዙ እንደሚወድቅ ከመግለጽ ባለፈ የሰሜኑ ንጉሥ ከደቡቡ ንጉሥ ጋር የሚያደርገው ጦርነት ውጤት ምን እንደሚሆን ይናገራል። ስለ ሰሜኑ ንጉሥ ሲናገር “ሠራዊቱ ተጠራርጎ ይወሰዳል፤ ብዙዎችም ተገድለው ይወድቃሉ” ይላል። (ዳን. 11:26ለ) ልክ በትንቢት በተነገረው መሠረት በአንደኛው የዓለም ጦርነት ወቅት የጀርመን ሠራዊት ‘ተጠራርጎ የተወሰደ’ ሲሆን ብዙ ሰዎች ‘ተገድለው ወድቀዋል።’ ይህ ጦርነት እስከዚያ ጊዜ ድረስ ከተካሄዱ ጦርነቶች ሁሉ በርካታ ሰው ያለቀበት ነው።

  • ‘የሰሜኑ ንጉሥ’ በፍጻሜው ዘመን
    መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2020 | ግንቦት
    • e እነዚህ ሰዎች፣ የንጉሠ ነገሥታዊ አገዛዙን ውድቀት ለማፋጠን የተለያዩ ነገሮችን አድርገዋል። ለምሳሌ ያህል፣ ለንጉሡ የሚሰጡትን ድጋፍ አቁመዋል፤ ስለ ጦርነቱ በሚስጥር ሊያዙ የሚገቡ መረጃዎችን አውጥተዋል፤ እንዲሁም ንጉሡ ሥልጣኑን እንዲለቅ ጫና አሳድረዋል።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ