-
ባላንጣዎቹ ነገሥታት ፍጻሜያቸው ቀርቧልየዳንኤልን ትንቢት በትኩረት ተከታተል!
-
-
የመጨረሻው ዘመቻ
20. መልአኩ የሰሜኑ ንጉሥ የሚያደርገውን የመጨረሻ ዘመቻ የገለጸው እንዴት ነው?
20 በሰሜኑና በደቡቡ ንጉሥ መካከል የሚደረጉት ወታደራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ ወይም ሌላ ዓይነት ሽኩቻዎች ሁሉ የሚያበቁበት ጊዜ ቅርብ ነው። መልአኩ ገና ወደፊት ስለሚፈጠረው ቅራኔ ዝርዝር ሲገልጽ እንዲህ ብሏል:- “[የሰሜኑን ንጉሥ] ከምሥራቅና ከሰሜን ግን ወሬ ያውከዋል፤ ብዙ ሰዎችንም ይገድል ዘንድና ፈጽሞ ያጠፋ ዘንድ በታላቅ ቁጣ ይወጣል። ንጉሣዊ ድንኳኑንም በባሕርና በከበረው በቅዱሱ ተራራ [“በታላቁ ባሕርና በጌጡ ቅዱስ ተራራ፣” NW] መካከል ይተክላል፤ ወደ ፍጻሜው ግን ይመጣል፣ ማንም አይረዳውም።”—ዳንኤል 11:44, 45
21. ስለ ሰሜኑ ንጉሥ ምን ገና ወደፊት የሚገለጥ ነገር አለ?
21 በታኅሣሥ 1991 ሶቪየት ኅብረት ስትበታተን የሰሜኑ ንጉሥ ከባድ ሽንፈት ገጥሞታል። ዳንኤል 11:44, 45 ፍጻሜውን ሲያገኝ የሰሜን ንጉሥ የሚሆነው ማን ይሆን? የቀድሞዋ ሶቪየት ኅብረት ክፍል ከነበሩት አገሮች መካከል አንዱ የሰሜን ንጉሥ ሆኖ ብቅ ይል ይሆን? ወይስ እስካሁን ሲያደርግ እንደነበረው ማንነቱን ቀይሮ ብቅ ይላል? ተጨማሪ ብሔራት የኑክሌር መሣሪያዎችን መሥራታቸው ሌላ የጦር መሣሪያ እሽቅድድም እንዲጀመር ምክንያት ሆኖ በዚህ ንጉሥ ማንነት ላይ የሚያመጣው ለውጥ ይኖር ይሆን? ለእነዚህ ጥያቄዎች መልሱን የሚሰጠን ጊዜ ብቻ ይሆናል። መልሱን ለመገመት አለመሞከራችን ጥበብ ነው። የሰሜን ንጉሥ የመጨረሻውን ዘመቻ ሲያደርግ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተመሠረተ ማስተዋል ያላቸው ሁሉ የትንቢቱን ፍጻሜ በግልጽ ማስተዋል ይችላሉ።—በገጽ 284 ላይ የሚገኘውን “በዳንኤል ምዕራፍ 11 ላይ የተጠቀሱት ነገሥታት” የሚለውን ርዕስ ተመልከት።
22. የሰሜኑ ንጉሥ ስለሚሰነዝረው የመጨረሻ ጥቃት ምን ጥያቄዎች ይነሳሉ?
22 ይሁን እንጂ የሰሜን ንጉሥ በቅርቡ ምን እርምጃ እንደሚወስድ እናውቃለን። “ከምሥራቅና ከሰሜንም” በሚያውከው ወሬ ተነሣስቶ ‘ብዙዎችን’ ለማጥፋት ዘመቻ ያካሂዳል። ይህ ዘመቻ ዒላማ ያደረገው ማንን ነው? እንዲህ ያለውን ጥቃት እንዲፈጽም የሚያነሳሳውስ “ወሬ” ምንድን ነው?
የሚያውክ ወሬ ይደርሰዋል
23. (ሀ) ከአርማጌዶን በፊት ምን ጉልህ ክንውን መፈጸም ይኖርበታል? (ለ) ‘ከፀሐይ መውጫ የሚመጡት ነገሥታት’ እነማን ናቸው?
23 የራእይ መጽሐፍ የዓለም የሐሰት ሃይማኖት ድርጅት የሆነችውን የታላቂቱ ባቢሎንን ፍጻሜ በሚመለከት ምን እንደሚል ልብ በል። ከአርማጌዶን ማለትም ‘ሁሉን ከሚችለው አምላክ ታላቅ የጦርነት ቀን’ በፊት ይህቺ የእውነተኛው አምልኮ ቀንደኛ ጠላት ‘ሙሉ በሙሉ በእሳት ትቃጠላለች።’ (ራእይ 16:14, 16፤ 18:2-8) የሚደርስባት ጥፋት በምሳሌያዊው የኤፍራጥስ ወንዝ ላይ በፈሰሰው ስድስተኛው የአምላክ የቁጣ ጽዋ ተገልጿል። ‘ከፀሐይ መውጫ ለሚመጡ ነገሥታት መንገድ ይሰናዳላቸው ዘንድ’ ወንዙ ደረቀ። (ራእይ 16:12) እነዚህ ነገሥታት እነማን ናቸው? ከይሖዋ አምላክና ከኢየሱስ ክርስቶስ ሌላ ማንም ሊሆን አይችልም!—ከኢሳይያስ 41:2፤ 46:10, 11 ጋር አወዳድር።
24. የሰሜኑን ንጉሥ የሚያውከው ይሖዋ የሚወስደው የትኛው እርምጃ ሊሆን ይችላል?
24 የታላቂቱ ባቢሎን ጥፋት በራእይ መጽሐፍ ውስጥ እንደሚከተለው ተደርጎ በሥዕላዊ መንገድ ተገልጿል:- “ያየሃቸውም አሥር ቀንዶችና [በፍጻሜው ዘመን የሚገዙት ነገሥታትና] አውሬው [የተባበሩት መንግሥታት] ጋለሞታይቱን ይጣላሉ፤ ባዶዋንና ራቁትዋንም ያደርጓታል፣ ሥጋዋንም ይበላሉ፣ በእሳትም ያቃጥሉአታል።” (ራእይ 17:16) ገዥዎቹ ታላቂቱ ባቢሎንን የሚያጠፏት ለምንድን ነው? ‘አምላክ ሐሳቡን እንዲፈጽሙ ወደ ልባቸው ስለሚያገባው’ ነው። (ራእይ 17:17) ከእነዚህ ነገሥታት መካከል የሰሜኑ ንጉሥም ይገኝበታል። ‘ከምሥራቅ’ የሚሰማው ነገር ይሖዋ ታላቂቷን ሃይማኖታዊ ጋለሞታ ያጠፉ ዘንድ በገዥዎች ልብ ውስጥ ሐሳቡን በማስገባት የሚወስደውን እርምጃ የሚገልጽ ሊሆን ይችላል።
-
-
ባላንጣዎቹ ነገሥታት ፍጻሜያቸው ቀርቧልየዳንኤልን ትንቢት በትኩረት ተከታተል!
-
-
26. በሕዝቅኤል ትንቢት ውስጥ እንደተገለጸው ‘ከሰሜን የሚመጣው’ ዜና ምንጭ ማን ሊሆን ይችላል?
26 በዳንኤል ዘመን የኖረው ሕዝቅኤልም “በኋለኛው ዘመን” በአምላክ ሕዝቦች ላይ ጥቃት እንደሚሰነዘር ተንብዮአል። ይህን ጥላቻ የሚቆሰቁሰው የማጎጉ ጎግ ማለትም ሰይጣን ዲያብሎስ እንደሆነ ገልጿል። (ሕዝቅኤል 38:14, 16) በምሳሌያዊ አነጋገር ጎግ የሚመጣው ከየት አቅጣጫ ነው? ይሖዋ በሕዝቅኤል አማካኝነት ‘በስተ ሰሜን በኩል ካለ ሩቅ ስፍራ’ መሆኑን ይነግረናል። (ሕዝቅኤል 38:15 የ1980 ትርጉም) ይህ ጥቃት የቱንም ያህል ጠንካራ ቢሆን የይሖዋን ሕዝቦች ጨርሶ የሚያጠፋ አይሆንም። ይህ አስገራሚ ክንውን ይሖዋ የጎግን ኃይሎች ለመደምሰስ የሚወስደው ስትራቴጃዊ እርምጃ ውጤት ነው። በመሆኑም ይሖዋ ሰይጣንን እንዲህ ይለዋል:- “በመንጋጋህም ልጓም አገባብሃለሁ።” “ከሰሜን ዳርቻ እጎትትሃለሁ፣ ወደ እስራኤልም ተራሮች አመጣሃለሁ።” (ሕዝቅኤል 38:4፤ 39:2) በመሆኑም “ከሰሜን” የሚመጣውና የሰሜኑን ንጉሥ የሚያስቆጣው ዜና የሚመነጨው ከይሖዋ መሆን አለበት። ይሁን እንጂ “ከምሥራቅና ከሰሜን” የሚወጡት ወሬዎች በመጨረሻ ምን ይያዙ ምን የሚወስነው አምላክ ራሱ ሲሆን ለእኛም ጊዜ የሚያሳየን ይሆናል።
27. (ሀ) ጎግ የሰሜኑን ንጉሥ ጨምሮ ሁሉም ብሔራት የይሖዋን ሕዝቦች እንዲያጠቁ የሚያነሳሳቸው ለምንድን ነው? (ለ) የጎግ ጥቃት መጨረሻው ምን ይሆናል?
27 ጎግ ግን የዓለም ክፍል ሳይሆኑ የሚመላለሱት ‘የእግዚአብሔር እስራኤልና’ ‘የሌሎች በጎች’ ክፍል የሆኑት “እጅግ ብዙ ሰዎች” በሚኖራቸው ብልጽግና ተነሣስቶ መጠነ ሰፊ ጥቃት ይሰነዝራል። (ገላትያ 6:16፤ ራእይ 7:9፤ ዮሐንስ 10:16፤ 17:15, 16፤ 1 ዮሐንስ 5:19) ጎግ ‘ከብሔራት ተውጣጥተው የተሰበሰቡትንና [መንፈሳዊ] ሀብትና ንብረት ያከማቹትን ሕዝቦች’ የሚያያቸው በክፉ ዓይን ነው። (ሕዝቅኤል 38:12 NW) የክርስቲያኖችን መንፈሳዊ ይዞታ በግላጭ እንደተገኘ ‘ቅጥር የሌለው መንደር’ በመቁጠር መላውን የሰው ዘር እንዳይቆጣጠር እንቅፋት የሆነበትን ነገር ጨርሶ ለማስወገድ በሙሉ ኃይሉ ይንቀሳቀሳል። ይሁን እንጂ አይሳካለትም። (ሕዝቅኤል 38:11, 18፤ 39:4) የሰሜኑን ንጉሥ ጨምሮ የምድር ነገሥታት በይሖዋ ሕዝቦች ላይ ጥቃት ሲሰነዝሩ ‘ወደ ፍጻሜያቸው ይመጣሉ።’
‘ንጉሡ ወደ ፍጻሜው ይመጣል’
28. የሰሜኑንና የደቡቡን ነገሥታት የወደፊት ዕጣ በሚመለከት ምን የምናውቀው ነገር አለ?
28 የሰሜን ንጉሥ የሚያደርገው የመጨረሻ ዘመቻ በደቡብ ንጉሥ ላይ ያነጣጠረ አይደለም። በመሆኑም የሰሜን ንጉሥ ወደ ፍጻሜው የሚመጣው በዋነኛ ተቀናቃኙ እጅ አይደለም። በተመሳሳይም የደቡቡ ንጉሥ የሚጠፋው በሰሜኑ ንጉሥ አይደለም። የደቡቡ ንጉሥ የሚጠፋው ‘[በሰው] እጅ’ ሳይሆን በአምላክ መንግሥት ነው።a (ዳንኤል 8:25) እንዲያውም በአርማጌዶን ጦርነት ጊዜ ምድራዊ መንግሥታት በሙሉ በአምላክ መንግሥት አማካኝነት ከሕልውና ውጭ ይሆናሉ። የሰሜኑ ንጉሥ ዕጣም ቢሆን ከዚህ የተለየ እንደማይሆን ግልጽ ነው። (ዳንኤል 2:44) ዳንኤል 11:44, 45 የሚገልጸው ወደ መጨረሻው ውጊያ የሚያመሩትን ክንውኖች ነው። የሰሜኑ ንጉሥ ወደ ፍጻሜው ሲመጣ የሚረዳው አለመኖሩ ምንም አያስገርምም!
-