የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • “ጎግ ሆይ፣ እኔ በአንተ ላይ ተነስቻለሁ”
    የይሖዋ ንጹሕ አምልኮ መልሶ ተቋቋመ!
    • 8 ‘የሰሜኑ ንጉሥ።’ (ዳንኤል 11:40-45⁠ን አንብብ።) ዳንኤል ከእሱ ዘመን አንስቶ እስከ ዘመናችን ድረስ ስለሚነሱ የተለያዩ የዓለም ኃያላን መንግሥታት ተንብዮአል። በተጨማሪም ትንቢቱ ‘የሰሜን ንጉሥ’ እና ‘የደቡብ ንጉሥ’ በሚባሉ ተፎካካሪ የፖለቲካ ኃይሎች መካከል ስለሚኖር ሽኩቻ ይጠቅሳል፤ ባለፉት በርካታ መቶ ዘመናት የተለያዩ ብሔራት የበላይነት ለመጨበጥ ባካሄዱት ትግል የእነዚህ ሁለት ጠላቶች ማንነት ሲለዋወጥ ቆይቷል። ዳንኤል የሰሜኑ ንጉሥ “በፍጻሜው ዘመን” የሚያደርገውን የመጨረሻ ዘመቻ አስመልክቶ ሲናገር “እሱም ለማጥፋትና ብዙዎችን ለመደምሰስ በታላቅ ቁጣ ይወጣል” ብሏል። የሰሜኑ ንጉሥ ዋነኛ የጥቃት ዒላማዎች የይሖዋ አምላኪዎች ናቸው።c ነገር ግን እንደ ማጎጉ ጎግ ሁሉ የሰሜኑ ንጉሥም በአምላክ ሕዝቦች ላይ የሚሰነዝረው ጥቃት ከከሸፈበት በኋላ “ወደ ፍጻሜው ይመጣል።”

  • “ጎግ ሆይ፣ እኔ በአንተ ላይ ተነስቻለሁ”
    የይሖዋ ንጹሕ አምልኮ መልሶ ተቋቋመ!
    • c ዳንኤል 11:45 የሰሜኑ ንጉሥ ‘ንጉሣዊ ድንኳኖቹን በታላቁ ባሕር [ሜድትራንያን ባሕር] እና ቅዱስ በሆነው ውብ ተራራ [የአምላክ ቤተ መቅደስ ይገኝበት የነበረውና የአምላክ ሕዝቦች አምልኮ ያቀርቡበት የነበረው ቦታ] መካከል እንደሚተክል’ ይናገራል፤ ይህ ሐሳብ የሰሜኑ ንጉሥ የአምላክ ሕዝቦችን የጥቃት ዒላማው እንደሚያደርግ ይጠቁማል።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ