የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ይሖዋ “በቅርብ ጊዜ ውስጥ ሊፈጸሙ የሚገባቸውን ነገሮች” ይገልጣል
    መጠበቂያ ግንብ—2012 | ሰኔ 15
    • 9 የይሖዋ አገልጋዮች የምስሉ እግር ምን ትርጉም እንዳለው ለማወቅ ለረጅም ጊዜ ጥረት ሲያደርጉ ቆይተዋል። ዳንኤል 2:41 የብረቱና የሸክላው ድብልቅ የሚያመለክተው በርካታ መንግሥታትን ሳይሆን አንድን “መንግሥት” ብቻ እንደሆነ ይናገራል። በመሆኑም ሸክላው የሚያመለክተው በንጹሕ ብረት ከተመሰለው ከሮም ግዛት ያነሰ ጥንካሬ ያለው የአንግሎ አሜሪካ የዓለም ኃያል መንግሥት ተጽዕኖ በሚያሳድርባቸው የምድር ክፍሎች ውስጥ የሚገኙትን የእሱን አቅም የሚያዳክሙ የኅብረተሰብ ክፍሎችን ነው። ሸክላው ‘የሰው ዘርን’ ማለትም ተራውን ሕዝብ እንደሚያመለክት የዳንኤል መጽሐፍ ይገልጻል። (ዳን. 2:43 የ1954 ትርጉም) በአንግሎ አሜሪካ የዓለም ኃያል መንግሥት ውስጥ ሰዎች በሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች እንቅስቃሴ፣ በሠራተኛ ማኅበራትና ነፃነት ለማግኘት በተደረጉ እንቅስቃሴዎች አማካኝነት መብታቸውን ለማስከበር ሞክረዋል። ተራው ሕዝብ፣ የአንግሎ አሜሪካ የዓለም ኃያል መንግሥት እንደ ብረት ያለ ጥንካሬውን እንዳያሳይ አዳክሞታል። በተጨማሪም የምርጫ ተወዳዳሪዎች የሚያገኙት ተቀራራቢ ውጤትና ተጻራሪ የሆኑ የፖለቲካ አመለካከቶች መኖራቸው ሰፊ ተቀባይነት ያገኙ መሪዎችም እንኳ ፖሊሲዎቻቸውን ለማስፈጸም የሚያስችል የተሟላ ሥልጣን እንዳይኖራቸው አድርጓል። ዳንኤል ይህ “መንግሥት በከፊሉ ብርቱ በከፊሉ ደካማ” እንደሚሆን አስቀድሞ ተናግሯል።​—ዳን. 2:42፤ 2 ጢሞ. 3:1-3

  • ይሖዋ “በቅርብ ጊዜ ውስጥ ሊፈጸሙ የሚገባቸውን ነገሮች” ይገልጣል
    መጠበቂያ ግንብ—2012 | ሰኔ 15
    • 11 የጣቶቹ ቁጥርስ የሚያመለክተው ነገር አለ? ዳንኤል ባያቸው ሌሎች ራእዮች ላይ ትንቢታዊ ትርጉም ያላቸውን ቁጥሮች ለይቶ ተናግሯል፤ ለምሳሌ በተለያዩ አራዊት ራሶች ላይ የታዩትን ቀንዶች ቁጥር ጠቅሷል። ይሁንና ዳንኤል ስለ ምስሉ ሲናገር የጣቶቹን ቁጥር አልገለጸም። በመሆኑም የምስሉ እጆችና እግሮች እንዲሁም የእጆቹ ጣቶች፣ ቁጥራቸው ምንም ዓይነት ትርጉም እንደሌለው ሁሉ የጣቶቹ ቁጥርም ምንም ትርጉም ያለው አይመስልም። ይሁንና ዳንኤል የምስሉ እግር ጣቶች ከብረትና ከሸክላ እንደተሠሩ ተናግሯል። ዳንኤል ከሰጠው መግለጫ መረዳት እንደሚቻለው የአምላክን መንግሥት የሚወክለው “ድንጋይ” ምስሉን በሚመታበት ጊዜ የዓለም ኃያል መንግሥት የሚሆነው አንግሎ አሜሪካ ነው።​—ዳን. 2:45

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ