-
በፍጻሜው ዘመን ያሉትን እውነተኛ አምላኪዎች ለይቶ ማወቅየዳንኤልን ትንቢት በትኩረት ተከታተል!
-
-
21. (ሀ) በዳንኤል 12:11 ላይ በትንቢት የተገለጸው ጊዜ የሚጀምረው ምን ነገሮች ሲፈጸሙ ነው? (ለ) ‘የዘወትሩ መሥዋዕት’ ምን ነበር? የቀረውስ መቼ ነበር? (በገጽ 298 ላይ የሚገኘውን ሣጥን ተመልከት።)
21 ዳንኤል እንደሚከተለው በማለት ተነግሮታል:- “የዘወትሩም መሥዋዕት ከቀረ ጀምሮ፣ የጥፋትም ርኩሰት ከቆመ ጀምሮ ሺህ ሁለት መቶ ዘጠና ቀን ይሆናል።” በመሆኑም ይህ ጊዜ የሚጀምረው አንድ ነገር ሲፈጸም ነው። “የዘወትሩ መሥዋዕት” መቅረት ነበረበት።a (ዳንኤል 12:11 የአዲሲቱ ዓለም ትርጉም የግርጌ ማስታወሻ) መልአኩ የትኛውን መሥዋዕት ማለቱ ነው? በምድራዊ ቤተ መቅደስ ስለሚቀርበው የእንስሳ መሥዋዕት መናገሩ አልነበረም። በአንድ ወቅት በኢየሩሳሌም ቆሞ የነበረውም ቤተ መቅደስ ቢሆን ‘የእውነተኛው ነገር’ ማለትም ኢየሱስ በ29 እዘአ ሊቀ ካህናት ሆኖ ብቅ ሲል ወደ ሕልውና የመጣው የታላቁ የይሖዋ ቤተ መቅደስ ‘ምሳሌ’ ነበር! ‘ክርስቶስ የብዙዎችን ኃጢአት ሊሸከም አንድ ጊዜ ስለተሠዋ’ የአምላክን ንጹሕ አምልኮ በሚወክለው በዚህ መንፈሳዊ ቤተ መቅደስ ውስጥ ዘወትር የኃጢአት መሥዋዕት ማቅረብ አያስፈልግም። (ዕብራውያን 9:24-28) ይሁን እንጂ ሁሉም እውነተኛ ክርስቲያኖች በዚህ ቤተ መቅደስ ውስጥ መሥዋዕት ያቀርባሉ። ሐዋርያው ጳውሎስ እንዲህ ሲል ጽፏል:- “እንግዲህ ዘወትር ለእግዚአብሔር የምሥጋናን መሥዋዕት፣ ማለት ለስሙ የሚመሰክሩ የከንፈሮችን ፍሬ፣ በእርሱ [በክርስቶስ] እናቅርብለት።” (ዕብራውያን 13:15) በመሆኑም ይህ የትንቢቱ የመጀመሪያ ሁኔታ ማለትም ‘የዘወትሩ መሥዋዕት መቅረት’ ፍጻሜውን ያገኘው የምሥራቹ ሥራ የቆመ መስሎ በታየበት በ1918 አጋማሽ ላይ ነበር።
22. (ሀ) የጥፋት ‘ርኩሰቱ’ ምንድን ነው? የቆመውስ መቼ ነው? (ለ) በዳንኤል 12:11 ላይ በትንቢት የተነገረው ወቅት የሚጀምረው መቼ ነው? የሚያበቃውስ?
22 ይሁን እንጂ ‘የጥፋት ርኩሰት መቆሙ’ ወይም ስለ መተከሉስ ምን ማለት ይቻላል? ስለ ዳንኤል 11:31 ስንወያይ እንዳየነው ይህ ርኩሰት በመጀመሪያ የመንግሥታቱ ቃል ኪዳን ማኅበር የነበረ ሲሆን ከጊዜ በኋላ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ተብሎ በአዲስ መልክ ብቅ ብሏል። ሁለቱም ቢሆኑ በምድር ላይ ሰላም ለማምጣት የሚያስችሉ ብቸኛ ተስፋ እንደሆኑ አድርገው በማስለፈፋቸው ርኩስ ነገር ሆነዋል። በዚህ መንገድ እነዚህ ተቋማት በብዙ ሰዎች ልብ ውስጥ የአምላክ መንግሥት መያዝ የሚገባውን ቦታ ይዘዋል! የቃል ኪዳኑ ማኅበር በኦፊሴል የተቋቋመው በጥር 1919 ነበር። በመሆኑም በዚያ ወቅት በዳንኤል 12:11 ላይ ተጠቅሰው የሚገኙት ሁለቱም ሁኔታዎች ፍጻሜያቸውን አግኝተዋል። በመሆኑም 1,290ዎቹ ቀናት የሚጀምሩት በ1919 መጀመሪያ ላይ ሆኖ እስከ 1922 የበልግ ወቅት (በሰሜኑ ንፍቀ ክበብ) ድረስ ይዘልቃሉ።
23. የአምላክ ቅዱሳን በዳንኤል ምዕራፍ 12 ላይ በትንቢት በተነገረላቸው 1,290 ቀናት ውስጥ በአምላክ ፊት ንጹሕ አቋም ለማግኘት የቻሉት እንዴት ነው?
23 በዚህ ወቅት ቅዱሳኑ ለመጥራትና በአምላክ ፊት ንጹሕ ሆነው ለመታየት ያደረጉት ለውጥ ነበርን? እንዴታ! በመጋቢት 1919 የመጠበቂያ ግንብ ማኅበር ፕሬዚዳንትና የቅርብ ረዳቶቹ ከወህኒ ተለቀቁ። ቆይቶም ከተሰነዘረባቸው የሐሰት ክስ ሙሉ በሙሉ ነፃ ሆኑ። ሥራቸው ሊያልቅ ይቅርና ገና እንዳልተነካ ስለተገነዘቡ ወዲያውኑ በመስከረም 1919 የሚደረግ አንድ የአውራጃ ስብሰባ በማዘጋጀት ሥራ ተጠመዱ። በዚያው ዓመት የመጠበቂያ ግንብ ተጓዳኝ የሆነ መጽሔት ለመጀመሪያ ጊዜ ታትሞ ወጣ። በመጀመሪያ ወርቃማው ዘመን የሚል ስያሜ የነበረው ይህ መጽሔት (ዛሬ ንቁ! ተብሏል) የዚህን ዓለም ብልሹነት ያለፍርሃት በማጋለጥና የአምላክ ሕዝቦች ንጹሕ ሆነው እንዲቀጥሉ በመርዳት የመጠበቂያ ግንብ መጽሔት ተጓዳኝ ሆኖ ቆይቷል። በትንቢት በተነገሩት 1,290 ቀናት ማብቂያ ላይ ቅዱሳኑ ንጹሕና የተስተካከለ አቋም ለመያዝ የሚያስችላቸውን ብዙ ነገር አድርገው ነበር። ልክ ይህ ጊዜ ባበቃበት ወቅት ማለትም በመስከረም 1922 በሴዳር ፖይንት ኦሃዮ ዩ ኤስ ኤ ውስጥ አንድ የላቀ ግምት የሚሰጠው የአውራጃ ስብሰባ አካሄዱ። ስብሰባው ለስብከቱ ሥራ በእጅጉ አነሳስቷቸዋል። ይሁን እንጂ ከዚህ በኋላም ለውጥ ማድረግ ያስፈልጋቸው ነበር። ይህ ደግሞ የሚከናወነው ጉልህ ስፍራ ባለው በቀጣዩ ጊዜ ውስጥ ነበር።

[በገጽ 298 ላይ የሚገኝ ሥዕል]
የዘወትሩ መሥዋዕት መቅረት
በዳንኤል መጽሐፍ ውስጥ ‘የዘወትሩ መሥዋዕት’ የሚለው መግለጫ አምስት ጊዜ ያህል ተጠቅሶ ይገኛል። አገልጋዮቹ ዘወትር ለይሖዋ አምላክ የሚያቀርቡትን የምሥጋና መሥዋዕት ማለትም ‘የከንፈሮችን ፍሬ’ የሚያመለክት ነው። (ዕብራውያን 13:15) ይህ መሥዋዕት እንደሚቀር የተነገረው ትንቢት በዳንኤል 8:11፣ ዳንኤል 11:31 እና ዳንኤል 12:11 ላይ ተጠቅሶ ይገኛል።
በሁለቱ የዓለም ጦርነቶች ወቅት የይሖዋ ሕዝቦች ‘በሰሜኑ ንጉሥና’ ‘በደቡቡ ንጉሥ’ ግዛት ሥር ከባድ ስደት ደርሶባቸዋል። (ዳንኤል 11:14, 15) ‘የዘወትሩ መሥዋዕት’ የቀረው በአንደኛው የዓለም ጦርነት ማብቂያ ገደማ የስብከቱ ሥራ በ1918 አጋማሽ እንደቆመ ያህል በሆነበት ጊዜ ነበር። (ዳንኤል 12:7) በተመሳሳይም በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት ‘የዘወትሩ መሥዋዕት’ በአንግሎ አሜሪካ የዓለም ኃይል ለ2,300 ቀናት ያህል ‘ተወስዶ’ ነበር። (ዳንኤል 8:11-14፤ የዚህን መጽሐፍ 10ኛ ምዕራፍ ተመልከት።) በቅዱሳን ጽሑፎች ውስጥ ተለይቶ ባይጠቀስም በናዚ ‘ክንዶች’ አማካኝነትም ለተወሰነ ጊዜ ቀርቶ ነበር።—ዳንኤል 11:31፤ የዚህን መጽሐፍ 15ኛ ምዕራፍ ተመልከት።
-