የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ተፈትነው ለይሖዋ ታማኝ ሆነው የተገኙ!
    የዳንኤልን ትንቢት በትኩረት ተከታተል!
    • የኢየሩሳሌም ወጣቶች ቁንጮ

      7, 8. ከ⁠ዳንኤል 1:3, 4 እና 6 ስለ ዳንኤልና ሦስቱ ጓደኞቹ ትውልድ ምን ብለን መደምደም እንችላለን?

      7 ወደ ባቢሎን የተጋዘው በይሖዋ ቤተ መቅደስ ያለው ዕቃ ብቻ አልነበረም። ዘገባው እንዲህ ይላል:- “ንጉሡም ነውር የሌለባቸውንና መልከ መልካሞቹን፣ በጥበብ ሁሉ የሚያስተውሉትን እውቀትም የሞላባቸውን ብልሃተኞችና አስተዋዮች የሆኑትን፣ በንጉሡም ቤት መቆም የሚችሉትን ብላቴኖች ከእስራኤል ልጆች ከነገሥታቱና ከመሳፍንቱ ዘር ያመጣ ዘንድ . . . ለጃንደረቦቹ አለቃ ለአስፋኔዝ ነገረ።”—ዳንኤል 1:3, 4

      8 የተመረጡት እነማን ነበሩ? እንዲህ የሚል እናነባለን:- “በእነዚህም መካከል ከይሁዳ ልጆች ዳንኤልና አናንያ ሚሳኤልና አዛርያ ነበሩ።” (ዳንኤል 1:6) ይህም የዳንኤልና የጓደኞቹን ትውልድ እንድናውቅ ፍንጭ ይሰጠናል። ይህ መግለጫ ባይሰጥ ኖሮ ስለ ትውልድ ሐረጋቸው ማወቅ አንችልም ነበር። ለምሳሌ ያህል ‘የይሁዳ ልጆች’ እንደሆኑ መገለጹ የነገሥታት መገኛ ከሆነው ነገድ የመጡ መሆናቸውን ያሳያል። በነገሥታት መስመር የነበሩ ሆኑም አልሆኑ ቢያንስ ከፍ ያለ ግምት ከሚሰጣቸው ቤተሰቦች የተገኙ ናቸው ብሎ ማሰቡ ምክንያታዊ ይሆናል። ሁሉም “ልጆች” በሚባሉበት በለጋ ዕድሜያቸው፣ ምናልባትም በአሥራዎቹ ዕድሜያቸው መጀመሪያ ላይ ሳይሆን አይቀርም ጤናማ አእምሮና አካል እንዲሁም ጥልቅ ማስተዋል፣ ጥበብና እውቀት ነበራቸው። ዳንኤልና ጓደኞቹ ግሩም ችሎታ የነበራቸው በሌላ አባባል የኢየሩሳሌም ወጣቶች ቁንጮ ነበሩ ለማለት ይቻላል።

  • ተፈትነው ለይሖዋ ታማኝ ሆነው የተገኙ!
    የዳንኤልን ትንቢት በትኩረት ተከታተል!
    • አእምሮአቸውን ለመቅረጽ የተደረገ ትግል

      10. ወጣቶቹ ዕብራውያን የተሰጣቸው ትምህርት ምን ነበር? ዓላማውስ ምንድን ነው?

      10 ብዙም ሳይቆይ በግዞት የተወሰዱትን የእነዚህን ወጣቶች አእምሮ ለመቅረጽ ትግል ተጀመረ። ዕብራውያኑ ልጆች ከባቢሎናውያን ሥርዓት ጋር እንዲስማሙ ለማድረግ ሲባል ናቡከደነፆር “የከለዳውያንንም ትምህርትና ቋንቋ ያስተምሯቸው ዘንድ” ጃንደረቦቹን አዘዘ። (ዳንኤል 1:4) ይህ ዝም ብሎ ተራ ትምህርት አልነበረም። ዚ ኢንተርናሽናል ስታንዳርድ ባይብል ኢንሳይክለፒዲያ እንዳብራራው “የሱሜሪያንን፣ የአካድያንን፣ የአረማይክን . . . እንዲሁም ሌሎች ቋንቋዎችንና በእነዚህ ቋንቋዎች የተጻፉ ሰፊ የሥነ ጽሑፍ ሥራዎችን ማጥናትን የሚጨምር ነበር።” ይህ “ሰፊ የሥነ ጽሑፍ ሥራ” ታሪክን፣ ሒሳብን፣ የከዋክብትን ጥናትና የመሳሰሉትን ነገሮች የሚያካትት ነው። ይሁን እንጂ “ትልቁን ቦታ የያዙት ከዚሁ ጋር ተዛማጅነት ያላቸው የአውደ ነገሥትና የኮከብ ቆጠራ ሃይማኖታዊ ጽሑፎች . . . ነበሩ።”

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ