ሰዎችን ወደ እቶን እሳት ከመጣል ጋር በተያያዘም በጥንታዊ የባቢሎን መዛግብት ውስጥ የተጠቀሱ መረጃዎች እናገኛለን፤ አንዳንዶቹ ዘገባዎች በንጉሡ ትእዛዝ ወደ እሳት የተጣሉ ሰዎች እንዳሉ ይገልጻሉ። በናቡከደነጾር ዘመን የተጻፈ አንድ ጥንታዊ ጽሑፍ የባቢሎንን አማልክት ያቃለሉ ባለሥልጣናት ስለተበየነባቸው ቅጣት ይናገራል። ጽሑፉ እንዲህ ይላል፦ “አጥፏቸው፣ አቃጥሏቸው፣ ለብልቧቸው፣ . . . ወደ ምድጃው ጣሏቸው . . . ጭሳቸው እየተትጎለገለ እንዲወጣ በሚንበለበለው እሳት አጋዩአቸው።”