-
እምነታቸው ከባዱን ፈተና ተቋቋመየዳንኤልን ትንቢት በትኩረት ተከታተል!
-
-
12. አንዳንድ ከለዳውያን ሦስቱን ዕብራውያን ምን ብለው ከሰሷቸው? ለምንስ?
12 እነዚህ ዕብራውያን ባለ ሥልጣኖች ለምስሉ አንሰግድም ማለታቸው አንዳንዶቹን ከለዳውያን እጅግ አስቆጣቸው። ወዲያውኑ ንጉሡ ዘንድ ሄደው ‘አይሁዳውያኑን ከሰሱ።’d የእነርሱን ሐሳብ መስማት አልፈለጉም ነበር። ዕብራውያኑ ታማኝነት በማጉደልና አገርን በመክዳት ወንጀል እንዲቀጡላቸው በማሰብ ከሳሾቻቸው እንዲህ አሉ:- “በባቢሎን አውራጃ ሥራ ላይ የሾምሃቸው ሲድራቅና ሚሳቅ አብደናጎም የሚባሉ አይሁድ አሉ፤ ንጉሥ ሆይ፣ እነዚህ ሰዎች ትእዛዝህን እምቢ ብለዋል፤ አማልክትህን አያመልኩም፣ ላቆምኸውም ለወርቁ ምስል አይሰግዱም።”—ዳንኤል 3:8-12
-
-
እምነታቸው ከባዱን ፈተና ተቋቋመየዳንኤልን ትንቢት በትኩረት ተከታተል!
-
-
d “ከሰሱ” ተብሎ የተተረጎመው የአረማይክ አገላለጽ ‘የሰውን ሥጋ የመቦጫጨቅ’ ያህል ስሙን እያነሱ በሐሜት ማኘክ የሚል መልእክት አለው።
-