-
የኢዩኤል እና የአሞጽ መጻሕፍት ጎላ ያሉ ነጥቦችመጠበቂያ ግንብ—2007 | ጥቅምት 1
-
-
2:32—‘የይሖዋን ስም መጥራት’ ሲባል ምን ማለት ነው? የአምላክን ስም መጥራት ሲባል ስሙን ማወቅና በጥልቅ ማክበር እንዲሁም የዚህ ስም ባለቤት በሆነው አምላክ መታመንና መመካት ማለት ነው።—ሮሜ 10:13, 14
-
-
የኢዩኤል እና የአሞጽ መጻሕፍት ጎላ ያሉ ነጥቦችመጠበቂያ ግንብ—2007 | ጥቅምት 1
-
-
2:28-32፦ ‘ከታላቁና ከሚያስፈራው የይሖዋ ቀን’ የሚድነው ‘የይሖዋን ስም የሚጠራ’ ብቻ ነው። ይሖዋ በሥጋ ለባሽ ሁሉ ላይ መንፈሱን በማፍሰሱና ወጣቶችና አረጋውያን እንዲሁም ወንዶችና ሴቶች ትንቢት እንዲናገሩ ማለትም “የእግዚአብሔርን ታላቅ ሥራ” እንዲያውጁ በማድረጉ ምንኛ አመስጋኞች ነን! (የሐዋርያት ሥራ 2:11) የይሖዋ ቀን እየቀረበ ሲሄድ ‘በቅድስናና በእውነተኛ መንፈሳዊነት ልንኖር’ ይገባናል።—2 ጴጥሮስ 3:10-12
-