የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ሌሎችን በይሖዋ ዓይን ለማየት ጣሩ
    መጠበቂያ ግንብ—2003 | መጋቢት 15
    • 7. ዮናስ እስራኤል ውስጥ ይሖዋን ያገለገለው በምን ዓይነት ሁኔታዎች ሥር ነው? ይህን ማወቅህ ስለ እርሱ ባለህ አመለካከት ላይ ምን ለውጥ ያመጣል?

      7 ዮናስ ለመልእክቱ አዎንታዊ ምላሽ ባላገኘበት በእስራኤል ምድር በታማኝነት አገልግሏል። በእርሱ ዘመን የኖረው ነቢዩ አሞጽ በወቅቱ እስራኤላውያን ፍቅረ ነዋይ የተጠናወታቸው እንደነበሩ ተናግሯል።b በእስራኤል ክፋት ተስፋፍቶ የነበረ ቢሆንም እስራኤላውያን ሁኔታውን በቸልታ ያልፉ ነበር። (አሞጽ 3:​13–15፤ 4:​4፤ 6:​4-6) ሆኖም ዮናስ መልእክቱን እንዲያውጅ የተሰጠውን ተልእኮ ያለማሰለስ በታማኝነት ፈጽሟል። የምሥራቹ አዋጅ ነጋሪ ከሆንክ ደንታ ቢስና ግድ የለሽ ለሆኑ ሰዎች መልእክቱን ማድረስ ምን ያህል አዳጋች መሆኑን እንደምትገነዘብ የታወቀ ነው። እንግዲያው ዮናስ ደካማ ጎኖች እንደነበሩት የማይካድ ቢሆንም እምነት የለሽ ለሆኑት እስራኤላውያን በሚሰብክበት ጊዜ ያሳየውን ታማኝነትና ጽናት መዘንጋት አይኖርብንም።

  • ሌሎችን በይሖዋ ዓይን ለማየት ጣሩ
    መጠበቂያ ግንብ—2003 | መጋቢት 15
    • b ዳግማዊ ኢዮርብዓም አንዳንድ ወሳኝ ድሎችን በመቀዳጀቱና ቀድሞ በእስራኤል ግዛት ሥር የነበሩ ክልሎችን በማስመለሱ ምክንያት ይሰበሰብለት የነበረው ግብር በመጨመሩ ሰሜናዊው መንግሥት ከፍተኛ ብልጽግና እንዲያገኝ አስችሎታል።​—⁠2 ሳሙኤል 8:​6፤ 2 ነገሥት 14:​23-28፤ 2 ዜና መዋዕል 8:​3, 4፤ አሞጽ 6:​2

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ