የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ከሠራው ስህተት ተምሯል
    መጠበቂያ ግንብ—2009 | ጥር 1
    • ሆኖም እዚያው ተቀብሮ አልቀረም! በአቅራቢያው አንድ ጠቆር ያለና በጣም ግዙፍ የሆነ ሕይወት ያለው ነገር ሲንቀሳቀስ ተመለከተ። ይህ ፍጡር በፍጥነት ወደ እሱ እየቀረበ መጣ። ከዚያም አንድ ትልቅ አፍ ተከፍቶ ዋጠው!

      ዮናስ ያበቃለት ይመስል ነበር። ይሁንና ምንም አለመሆኑ በግርምት እንዲዋጥ አደረገው። በሰውነቱ ላይ ምንም ዓይነት ጉዳት አልደረሰም፤ ሌላው ቢቀር አየር አጥቶ እንኳ አልታፈነም። ሕይወቱን ሊያሳጣውና መቀበሪያው ሊሆን በሚችል ቦታ ውስጥ የነበረ ቢሆንም በሕይወት መቀጠል ችሏል! ይህም ለአምላክ አክብሮታዊ ፍርሃት እንዲያድርበት አደረገው። “ዮናስን የሚውጥ ትልቅ ዓሣ [ያዘጋጀው]” አምላኩ ይሖዋ እንደሆነ ጥርጥር የለውም።c—ዮናስ 1:17

      ደቂቃዎች አልፈው በሰዓታት ተተኩ። ዮናስ አይቶት በማያውቅ ድቅድቅ ጨለማ ውስጥ ሆኖ የተለያዩ ነገሮችን ሲያውጠነጥን ከቆየ በኋላ ወደ ይሖዋ አምላክ ጸለየ። በዮናስ መጽሐፍ ሁለተኛ ምዕራፍ ላይ ሙሉ በሙሉ ተመዝግቦ የሚገኘው ጸሎቱ ብዙ የሚገልጸው ነገር አለ። ዮናስ በተደጋጋሚ ጊዜ ከመዝሙር መጽሐፍ ይጠቅስ ስለነበር ጥልቅ የሆነ የቅዱሳን ጽሑፎች እውቀት እንደነበረው ያሳያል። በተጨማሪም ግሩም የሆነ የአመስጋኝነት ባሕርይ እንደነበረው ይጠቁማል። ዮናስ “እኔ ግን በምስጋና መዝሙር፣ መሥዋዕት እሠዋልሃለሁ፤ የተሳልሁትንም እሰጣለሁ፤ ድነት ከእግዚአብሔር ዘንድ ነው” በማለት ጸሎቱን ደምድሟል።—ዮናስ 2:9

      ዮናስ፣ ይሖዋ ማንኛውንም ሰው በየትኛውም ጊዜና ቦታ ማዳን እንደሚችል ከደረሰበት ሁኔታ መማር ችሏል። ይሖዋ “በዓሣው ሆድ ውስጥ” የነበረውን አገልጋዩን እንኳ ታድጎታል። (ዮናስ 1:17) የአንድን ሰው ሕይወት በዓሣ ሆድ ውስጥ ለሦስት ቀንና ሌሊት ጠብቆ ማቆየት የሚችለው እሱ ብቻ ነው። ‘ሕይወታችን በአምላክ እጅ’ እንደሆነ ማስታወሳችን በጣም አስፈላጊ ነው። (ዳንኤል 5:23) እስትንፋሳችንም ሆነ ሕልውናችን ሙሉ በሙሉ በእሱ ላይ የተመካ ነው። ታዲያ ለዚህ ነገር አመስጋኞች ነን? ይሖዋን ልንታዘዘውስ አይገባም?

      ስለ ዮናስስ ምን ማለት ይቻላል? ይሖዋን በመታዘዝ አመስጋኝነቱን በተግባር አሳይቷል? አዎን፣ አሳይቷል። ከሦስት ቀንና ሌሊት በኋላ ዓሣው ዮናስን ወደ ባሕሩ ዳርቻ ወስዶ “በደረቅ ምድር ላይ ተፋው።” (ዮናስ 2:10) እስቲ አስበው፣ ይህ ሁሉ ከሆነም በኋላ እንኳ ዮናስ ከባሕር ውስጥ ለመውጣት መዋኘት አላስፈለገውም! እርግጥ ነው፣ ዓሣው የተፋው የትም ይሁን የት ከባሕሩ ዳርቻ ተነስቶ መጓዝ ነበረበት። ይሁን እንጂ ብዙም ሳይቆይ ምን ያህል አመስጋኝ እንደሆነ የሚፈተንበት ጊዜ ደረሰ። ዮናስ 3:1, 2 እንዲህ ይላል፦ “የእግዚአብሔርም ቃል ለሁለተኛ ጊዜ እንዲህ ሲል ወደ ዮናስ መጣ፤ ‘ወደ ታላቂቱ ከተማ ወደ ነነዌ ሄደህ የምነግርህን መልእክት ስበክላት።’” ታዲያ ዮናስ ምን ያደርግ ይሆን?

  • ከሠራው ስህተት ተምሯል
    መጠበቂያ ግንብ—2009 | ጥር 1
    • c “ዓሣ” ተብሎ የተተረጎመው የዕብራይስጥ ቃል በግሪክኛ “አስፈሪ የባሕር እንስሳ” ወይም “ግዙፍ ዓሣ” የሚል ፍቺ ተሰጥቶታል። ይህ ዓሣ በትክክል ምን ዓይነት የባሕር እንስሳ እንደሆነ ማወቅ ባይቻልም በሜድትራንያን ሰውን ሙሉ በሙሉ መዋጥ የሚችሉ ሻርኮች እንዳሉ ማስተዋል ተችሏል። በሌሎች ቦታዎች ከእነዚህ በጣም የሚበልጡ ሻርኮች ይገኛሉ፤ ዌል ሻርክ የተባለው የዓሣ ዝርያ 15 ሜትር ወይም ከዚያ የሚበልጥ ርዝማኔ ሊኖረው ይችላል!

  • ከሠራው ስህተት ተምሯል
    መጠበቂያ ግንብ—2009 | ጥር 1
    • ሌላው ቀርቶ ያለ ምንም መለኮታዊ ጣልቃ ገብነት በጣም አስደናቂ የሆኑ ነገሮች የሚፈጸሙባቸው ጊዜያት አሉ። ለምሳሌ ያህል፣ በ1758 አንድ መርከበኛ በሜድትራንያን ባሕር ላይ እየተጓዘ ሳለ ከመርከቡ ላይ በመውደቁ አንድ ሻርክ ውጦት እንደነበር ይነገራል። ይሁንና ሻርኩ በመድፍ በመመታቱ መርከበኛውን መልሶ ተፋው፤ ሰውየው ይህ ነው የሚባል ጉዳት ሳይደርስበት መትረፍ ችሏል። ይህ እውነት ከሆነ፣ ታሪኩ አጀብ የሚያሰኝ ነው፤ ተአምር ግን አይደለም። ታዲያ አምላክ ኃይሉን ተጠቅሞ ከዚህ የበለጠ ነገር መፈጸም አይችልም?

      በዮናስ መጽሐፍ ላይ ጥርጣሬ ያላቸው ሰዎች፣ ማንኛውም ሰው ቢሆን አየር ስለሚያጥረው በዓሣ ሆድ ውስጥ ለሦስት ቀናት ሊቆይ አይችልም ብለው ይከራከራሉ። ሆኖም ሰዎች እንኳ በዕቃ ውስጥ የታመቀ አየር ይዘው ባሕር ውስጥ በመግባት በውኃ ውስጥ ለረጅም ሰዓት መቆየት ችለዋል። ታዲያ አምላክ ይህ ነው የማይባለውን ታላቅ ኃይሉንና ጥበቡን በመጠቀም ዮናስ ለሦስት ቀናት በሕይወት እንዲቆይ ማድረግ ይሳነዋል? አንድ የይሖዋ መልአክ በአንድ ወቅት የኢየሱስ እናት ለሆነችው ለማርያም እንደገለጸው ‘ለአምላክ የሚሳነው ነገር የለም።’—ሉቃስ 1:37 አዲሱ መደበኛ ትርጉም

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ