የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ከሠራው ስህተት ተምሯል
    በእምነታቸው ምሰሏቸው
    • 12. (ሀ) ዮናስ ማዕበሉ እያናወጣቸው ባለበት ሰዓት መተኛቱ ግዴለሽ መሆኑን የሚያሳይ ነው ብለን ለመፍረድ መቸኮል የሌለብን ለምንድን ነው? (የግርጌ ማስታወሻውንም ተመልከት።) (ለ) ይሖዋ የችግሩ መንስኤ ማን መሆኑን ለይቶ ያሳወቀው እንዴት ነው?

      12 ምንም ነገር ማድረግ እንደማይችል የተሰማው ዮናስ ወደ ታችኛው የመርከቧ ክፍል ሄዶ ተኛ። ከዚያም ጭልጥ ያለ እንቅልፍ ወሰደው።b የመርከቧም አዛዥ ሄዶ ዮናስን ከተኛበት ከቀሰቀሰው በኋላ እንደ ሌሎቹ ሰዎች ሁሉ እሱም አምላኩን እንዲማጸን ነገረው። መርከበኞቹ ይህን ኃይለኛ ማዕበል ያመጣባቸው አንድ መለኮታዊ ኃይል እንደሆነ ስለተሰማቸው ከተሳፋሪዎቹ መካከል ለዚህ ችግር የዳረጋቸውን ሰው ለማወቅ ሲሉ ዕጣ ተጣጣሉ። ዕጣው አንድ በአንድ ሲወጣና ሌሎቹ ሰዎች ሁሉ ጥፋተኞች አለመሆናቸው እየታወቀ ሲሄድ ዮናስ ልቡ በፍርሃት ሳይቀልጥ አይቀርም። ብዙም ሳይቆይ እውነታው ገሃድ ወጣ። ማዕበሉ እንዲነሳም ሆነ ዕጣው በዮናስ ላይ እንዲወጣ ያደረገው ይሖዋ ነበር!—ዮናስ 1:5-7⁠ን አንብብ።

  • ከሠራው ስህተት ተምሯል
    በእምነታቸው ምሰሏቸው
    • b የሰብዓ ሊቃናት ትርጉም፣ ዮናስ በተኛበት ወቅት ያንኮራፋ እንደነበር በመግለጽ ምን ያህል ጭልጥ ያለ እንቅልፍ እንደወሰደው ይጠቁማል። ይሁንና ዮናስ መተኛቱ ግዴለሽ እንደነበር የሚያሳይ ምልክት ነው ብለን መደምደም የለብንም፤ ከዚህ ይልቅ አንዳንዶች ስሜታቸው በጣም በሚደቆስበት ጊዜ በእንቅልፍ ሊሸነፉ እንደሚችሉ ማስታወስ ይኖርብናል። ኢየሱስ በጌቴሴማኒ የአትክልት ስፍራ በጣም ተጨንቆ በነበረበት ወቅት ጴጥሮስ፣ ያዕቆብና ዮሐንስ “ከሐዘን የተነሳ ሲያንቀላፉ” ነበር።—ሉቃስ 22:45

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ