-
በይሖዋ ስም ለዘላለም እንሄዳለን!መጠበቂያ ግንብ—2003 | ነሐሴ 15
-
-
15. በሚክያስ 4:1-4 ላይ ያለውን ትንቢት በራስህ አባባል ግለጽ።
15 ሚክያስ በመቀጠል አስደሳች ተስፋ ያዘለ መልእክት እንደሚያስተላልፍ እንመለከታለን። በሚክያስ 4:1-4 ላይ የሚገኙት ቃላት ምንኛ የሚያጽናኑ ናቸው! ጥቅሱ በከፊል እንዲህ ይላል፦ “በመጨረሻውም ዘመን የእግዚአብሔር ቤት ተራራ በተራሮች ራስ ላይ ጸንቶ ይቆማል፣ ከኮረብቶችም በላይ ከፍ ከፍ ይላል፤ አሕዛብም ወደ እርሱ ይጎርፋሉ። . . . በብዙዎችም አሕዛብ መካከል ይፈርዳል፣ በሩቅም ባሉ በብርቱዎች አሕዛብ ላይ ይበይናል፤ ሰይፋቸውንም ማረሻ፣ ጦራቸውንም ማጭድ ለማድረግ ይቀጠቅጣሉ፤ ሕዝብም በሕዝብ ላይ ሰይፍ አያነሣም ከእንግዲህም ወዲህ ሰልፍ አይማሩም። የሠራዊት ጌታ የእግዚአብሔር አፍም ተናግሮአልና ሰው እያንዳንዱ ከወይኑና ከበለሱ በታች ይቀመጣል፣ የሚያስፈራውም የለም።”
-
-
በይሖዋ ስም ለዘላለም እንሄዳለን!መጠበቂያ ግንብ—2003 | ነሐሴ 15
-
-
17 በሚክያስ ትንቢት መሠረት ከንጹሑ የይሖዋ አምልኮ በስተቀር በምድር ላይ ምንም ዓይነት ሌላ አምልኮ የማይኖርበት ጊዜ ይመጣል። አሁንም እንኳን “ለዘላለም ሕይወት የተዘጋጁ” ሰዎች የይሖዋን መንገዶች እየተማሩ ነው። (ሥራ 13:48) ይሖዋ ከመንግሥቱ ጎን ለሚሰለፉ አማኞች ሁሉ እየፈረደና በመንፈሳዊ ሁኔታ ነገሮችን እያስተካከለ ነው። እነዚህ ሰዎች ‘የእጅግ ብዙ ሰዎች’ ክፍል በመሆን ‘ታላቁን መከራ’ በሕይወት ያልፋሉ። (ራእይ 7:9, 14) ሰይፋቸውን ቀጥቅጠው ማረሻ ስላደረጉ ባልንጀሮቻቸው ከሆኑት የይሖዋ ምሥክሮችና ከሌሎች ሰዎች ጋር በሰላም ይኖራሉ። ከእነርሱ እንደ አንዱ መሆን እንዴት ያለ መታደል ነው!
በይሖዋ ስም ለመሄድ ቆርጠናል
18. ‘በወይንና በለስ ሥር መቀመጥ’ ምን ያመለክታል?
18 ፍርሃት በመላው ምድር ላይ እንደ ጥቁር ዳመና ባጠላበት በዚህ ዘመን ብዙ ሰዎች የይሖዋን መንገዶች እየተማሩ መሆናቸው በጣም ያስደስተናል። እንደነዚህ ያሉት አምላክን የሚወድዱ ሰዎች ጦርነት የማይማሩበትንና ከወይናቸውና ከበለሳቸው በታች የሚቀመጡበትን ጊዜ በናፍቆት እንጠባበቃለን። የበለስ ዛፎች አብዛኛውን ጊዜ የሚተከሉት በወይን የአትክልት ቦታዎች ነው። (ሉቃስ 13:6) በራስ ወይንና በለስ ሥር መቀመጥ ሰላምና ብልጽግና የሰፈነበት እንዲሁም ሥጋት የሌለበት ሁኔታ መኖሩን ያመለክታል። በአሁኑ ጊዜም እንኳ ከይሖዋ ጋር የመሠረትነው ዝምድና የአእምሮ ሰላምና መንፈሳዊ ደህንነት ያስገኝልናል። እነዚህ ሁኔታዎች በአምላክ መንግሥት አገዛዝ ሥር ሲሰፍኑ ከፍርሃትና ከስጋት ሙሉ በሙሉ ነጻ እንሆናለን።
-