የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • “በልቧ ይዛ ታሰላስል ነበር”
    መጠበቂያ ግንብ—2008 | ጥቅምት 1
    • ወደ ቤተ ልሔም የተደረገ ጉዞ

      እንዲህ ያለውን ጉዞ ያደረጉት ዮሴፍና ማርያም ብቻ አልነበሩም። በወቅቱ አውግስጦስ ቄሳር ሁሉም ሰው ወደየራሱ ከተማ በመሄድ እንዲመዘገብ አዋጅ አውጥቶ ነበር። ታዲያ ዮሴፍ ለዚህ አዋጅ ምን ምላሽ ሰጠ? ዘገባው እንዲህ ይላል፦ “ዮሴፍም ከዳዊት ቤትና ወገን ስለ ነበረ፣ በገሊላ አውራጃ ከምትገኘው ከናዝሬት ከተማ ተነሥቶ የዳዊት ከተማ ወደሆነችው፣ ቤተ ልሔም ወደምትባል ከተማ ወደ ይሁዳ ወጣ።”—ሉቃስ 2:1-4

      ቄሳር በዚህ ጊዜ ይህን አዋጅ ማውጣቱ የአጋጣሚ ጉዳይ አልነበረም። ከሰባት መቶ ዓመታት ገደማ በፊት የተነገረ አንድ ትንቢት መሲሑ በቤተ ልሔም እንደሚወለድ ይገልጻል። ከናዝሬት 11 ኪሎ ሜትር ብቻ ርቃ የምትገኝ ቤተ ልሔም የተባለች ከተማ የነበረች ቢሆንም ትንቢቱ መሲሑ የሚወለደው ‘በቤተ ልሔም ኤፍራታ’ መሆኑን ለይቶ ይጠቅሳል። (ሚክያስ 5:2) በዛሬው ጊዜ በናዝሬትና ከናዝሬት በስተ ደቡብ በምትገኘው በዚህች ትንሽ መንደር መካከል ኮረብታማ አካባቢዎችን አቋርጦ የሚያልፍ 150 ኪሎ ሜትር የሚሆን መንገድ አለ። ዮሴፍ እንዲሄድ የታዘዘው ደግሞ ወደዚህችኛዋ መንደር ነበር፤ ይህች ስፍራ የንጉሥ ዳዊት ዘሮች የትውልድ ከተማ ስትሆን ዮሴፍም ሆነ ሚስቱ ከዳዊት ወገን ነበሩ።

  • “በልቧ ይዛ ታሰላስል ነበር”
    መጠበቂያ ግንብ—2008 | ጥቅምት 1
    • ማርያም፣ ዮሴፍን ለመታዘዝ ያነሳሳት ሌላ ምክንያት ይኖር ይሆን? መሲሑ በቤተ ልሔም እንደሚወለድ የሚናገረውንስ ትንቢት ታውቅ ነበር? መጽሐፍ ቅዱስ ስለዚህ ጉዳይ የሚናገረው ነገር የለም። ይህ ትንቢት፣ በሃይማኖት መሪዎች ሌላው ቀርቶ በሕዝቡ ዘንድ እንኳ በስፋት ይታወቅ ስለነበር ማርያም ስለ ሁኔታው ሳታውቅ አትቀርም። (ማቴዎስ 2:1-7፤ ዮሐንስ 7:40-42) ከዚህም በተጨማሪ ማርያም ቅዱሳን መጻሕፍትን ጠንቅቃ ታውቅ ነበር። (ሉቃስ 1:46-55) ማርያም ለመሄድ የወሰነችው ይሖዋ ያስነገረውን ትንቢት በማወቋም ይሁን የባሏን ወይም የመንግሥትን ትእዛዝ ለማክበር በመፈለጓ አሊያም በሁሉም ምክንያቶች፣ ለእኛ ግሩም ምሳሌ ትሆነናለች። ይሖዋ፣ ትሑትና ታዛዥ የሆኑ ወንዶችንና ሴቶችን ከፍ አድርጎ ይመለከታቸዋል። ታዛዥነት ከፍ ተደርጎ በማይታይበት በዛሬው ጊዜ ማርያም በየትም ቦታ ለሚኖሩ ታማኝ ሰዎች መልካም አርዓያ ትሆናለች።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ