የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ክፉዎች የቀራቸው ጊዜ ምን ያህል ነው?
    መጠበቂያ ግንብ—2000 | የካቲት 1
    • 9 ዕንባቆም በምዕራፍ 1:​6-11 ላይ የሚገኙትን ተጨማሪ ቃላት በትኩረት ያዳምጣል። ይህ መልእክት የራሱ የይሖዋ ስለሆነ ማንም የሐሰት አምላክ፣ ማንም በድን ጣዖት መልእክቱ እንዳይፈጸም ሊያግደው አይችልም። “እነሆ፣ የእነርሱ ያልሆነውን መኖሪያ ይወርሱ ዘንድ በምድር ስፋት ላይ የሚሄዱትን መራሮችንና ፈጣኖችን ሕዝብ ከለዳውያንን አስነሣለሁ። እነርሱ የሚያስፈሩና የሚያስደነግጡ ናቸው፤ ፍርዳቸውና ክብራቸው ከራሳቸው ይወጣል። ፈረሶቻቸውም ከነብር ይልቅ ፈጣኖች ናቸው፣ ከማታም ተኩላ ይልቅ ጨካኞች ናቸው፤ ፈረሰኞቻቸውም ይንሳፈፋሉ፣ ከሩቅም ይመጣሉ፣ ለመብልም እንደሚቸኩል ንስር ይበርራሉ። ሁሉም ለግፍ ሥራ ይመጣሉ፣ ፊታቸውንም እንደ ምሥራቅ ነፋስ ያቀናሉ፤ ምርኮኞችንም እንደ አሸዋ ይሰበስባሉ። በነገሥታት ላይ ያላግጣሉ፣ መሳፍንትም ዋዛ ሆነውላቸዋል፤ በምሽጉ ሁሉ ይስቃሉ፣ አፈሩንም ከምረው ይወስዱታል። የዚያን ጊዜም እንደ ነፋስ አልፎ ይሄዳል፣ ይበድልማል፣ ኃይሉንም አምላክ ያደርገዋል።”

  • ክፉዎች የቀራቸው ጊዜ ምን ያህል ነው?
    መጠበቂያ ግንብ—2000 | የካቲት 1
    • 11. የባቢሎን ኃይል በይሁዳ ላይ ያደረገውን ዘመቻ እንዴት ትገልጸዋለህ?

      11 የባቢሎን ፈረሶች ከነብር ይልቅ የፈጠኑ ናቸው። ፈረሰኞቹ በሌሊት ለአደን ከተሰማሩ የተራቡ ተኩላዎች ይበልጥ የሚያስፈሩ ናቸው። ለመሄድ እየተቁነጠነጡ ‘በኮቴያቸው መሬቱን ይቆፍራሉ።’ ሩቅ ከሆነው አገራቸው ከባቢሎን ተነስተው ወደ ይሁዳ ያቀናሉ። የሚጓጓለትን ምግብ ለማግኘት እንደሚበር ንሥር ከለዳውያን እንደ መብል በሆነላቸው ሕዝብ ላይ ድንገት ዘልለው ጉብ ይላሉ። ይህ ግን በጥቂት ወታደሮች ብቻ የሚደረግ ለአጭር ጊዜ የሚቆይ ወረራ ነውን? ፈጽሞ አይደለም! ምድሪቱን በሙሉ ለማውደም በጣም ትልቅ ሠራዊት ሆነው “ሁሉም ለግፍ ሥራ ይመጣሉ።” በጉጉት ስሜት ተውጠው እንደ ምሥራቅ ነፋስ በከፍተኛ ፍጥነት በስተ ምዕራብ ወደሚገኙት ወደ ይሁዳና ወደ ኢየሩሳሌም ይጋልባሉ። የባቢሎን ጭፍሮች በጣም ብዙ እስረኞችን ስለሚያግዙ ‘ምርኮኞችን እንደ ባሕር አሸዋ ይሰበስባሉ።’

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ