የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ክፉዎች የቀራቸው ጊዜ ምን ያህል ነው?
    መጠበቂያ ግንብ—2000 | የካቲት 1
    • 9 ዕንባቆም በምዕራፍ 1:​6-11 ላይ የሚገኙትን ተጨማሪ ቃላት በትኩረት ያዳምጣል። ይህ መልእክት የራሱ የይሖዋ ስለሆነ ማንም የሐሰት አምላክ፣ ማንም በድን ጣዖት መልእክቱ እንዳይፈጸም ሊያግደው አይችልም። “እነሆ፣ የእነርሱ ያልሆነውን መኖሪያ ይወርሱ ዘንድ በምድር ስፋት ላይ የሚሄዱትን መራሮችንና ፈጣኖችን ሕዝብ ከለዳውያንን አስነሣለሁ። እነርሱ የሚያስፈሩና የሚያስደነግጡ ናቸው፤ ፍርዳቸውና ክብራቸው ከራሳቸው ይወጣል። ፈረሶቻቸውም ከነብር ይልቅ ፈጣኖች ናቸው፣ ከማታም ተኩላ ይልቅ ጨካኞች ናቸው፤ ፈረሰኞቻቸውም ይንሳፈፋሉ፣ ከሩቅም ይመጣሉ፣ ለመብልም እንደሚቸኩል ንስር ይበርራሉ። ሁሉም ለግፍ ሥራ ይመጣሉ፣ ፊታቸውንም እንደ ምሥራቅ ነፋስ ያቀናሉ፤ ምርኮኞችንም እንደ አሸዋ ይሰበስባሉ። በነገሥታት ላይ ያላግጣሉ፣ መሳፍንትም ዋዛ ሆነውላቸዋል፤ በምሽጉ ሁሉ ይስቃሉ፣ አፈሩንም ከምረው ይወስዱታል። የዚያን ጊዜም እንደ ነፋስ አልፎ ይሄዳል፣ ይበድልማል፣ ኃይሉንም አምላክ ያደርገዋል።”

  • ክፉዎች የቀራቸው ጊዜ ምን ያህል ነው?
    መጠበቂያ ግንብ—2000 | የካቲት 1
    • 12. የባቢሎናውያኑ ዝንባሌ ምን ነበር? ይህ የማይበገር ጠላት ‘በደለኛ’ ሆኖ የተገኘውስ እንዴት ነው?

      12 አንዳቸውም ቢሆኑ የድል አድራጊነት ግስጋሴውን ሊገቱ ስላልቻሉ የከለዳውያኑ ጭፍራ በነገሥታት ላይ ይስቃል፣ በከፍተኛ ባለሥልጣኖችም ላይ ያላግጣል። ባቢሎናውያን ‘የአፈር ክምር’ ሠርተው ማጥቃት ሲጀምሩ ምሽግ የተባለው ሁሉ ወዲያው ስለሚፈርስ ‘በምሽጎች ሁሉ ላይ ይስቃል።’ ይህ የማይጋፉት ጠላት ይሖዋ በቀጠረው ቀን “እንደ ነፋስ ያልፋል።” በይሁዳና በኢየሩሳሌም ላይ ጥቃት ሲሰነዝር በአምላክ ሕዝቦች ላይ ጉዳት ማድረሱ ስለሆነ ‘በደል’ ይሆንበታል። የከለዳውያን ጦር አዛዥ እንደ አውሎ ነፋስ ፈጣን የሆነ ድል ከተቀዳጀ በኋላ ‘ይህን ኃይል ያገኘነው ከአምላካችን ነው’ ብሎ ይፎክራል። ግን ምንኛ ተሳስቷል!

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ