የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ከሚያምኑት ወገን እንሁን
    መጠበቂያ ግንብ—1999 | ታኅሣሥ 15
    • 8. የዕንባቆም ምሳሌ በመጀመሪያው መቶ ዘመን ለነበሩትም ሆነ ዛሬ ላሉት ክርስቲያኖች ጠቃሚ የሆነው ለምንድን ነው?

      8 ዕንባቆም የኢየሩሳሌም ጥፋት ምን ያህል እንደቀረበ አያውቅም ነበር። በተመሳሳይም የመጀመሪያው መቶ ዘመን ክርስቲያኖች የአይሁድ የነገሮች ሥርዓት ፍጻሜ መቼ እንደሚሆን አያውቁም ነበር። እኛም ብንሆን በዚህ ክፉ የነገሮች ሥርዓት ላይ የይሖዋ ፍርድ የሚጀምርበትን ‘ቀንና ሰዓት’ አናውቅም። (ማቴዎስ 24:​36) እንግዲያው ይሖዋ ለዕንባቆም የሰጠውን ድርብ መልስ ልብ እንበል። በመጀመሪያ ደረጃ ፍጻሜው ከተቀጠረለት ጊዜ ዝንፍ እንደማይል ለነቢዩ አረጋገጠለት። በሰብዓዊ አመለካከት የዘገየ ቢመስልም እንኳ አምላክ “አይዘገይም” ሲል ተናግሯል። (ዕንባቆም 2:​3) በሁለተኛ ደረጃ ደግሞ ይሖዋ “ጻድቅ በእምነቱ በሕይወት ይኖራል” በማለት ለዕንባቆም ነገረው። (ዕንባቆም 2:​4) ይህ እንዴት ያለ ግሩምና ለመረዳት የማይከብድ እውነት ነው! ትልቅ ለውጥ የሚያመጣው መጨረሻው የሚመጣበት ጊዜ ሳይሆን የእኛ በእምነት መቀጠል አለመቀጠል ነው።

      9. ታዛዥ የሆኑ የይሖዋ አገልጋዮች ታማኝ ሆነው በመገኘታቸው (ሀ) በ607 ከዘአበ (ለ) ከ66 እዘአ በኋላ በሕይወት ሊተርፉ የቻሉት እንዴት ነው? (ሐ) እምነታችንን ማጎልበታችን በጣም አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው?

      9 ኢየሩሳሌም በ607 ከዘአበ በጠፋችበት ወቅት ኤርምያስ፣ የእሱ ጸሐፊ የነበረው ባሮክ፣ አቤሜሌክና ታማኞቹ ሬካባውያን ይሖዋ ለዕንባቆም የሰጠው ተስፋ ሲፈጸም ተመልክተዋል። በኢየሩሳሌም ላይ ከደረሰው አሰቃቂ ጥፋት ተርፈው ‘በሕይወት መኖራቸውን ቀጥለዋል።’ ለምን? ይሖዋ ለታማኝነታቸው ወሮታ ስለከፈላቸው ነው። (ኤርምያስ 35:​1-19፤ 39:​15-18፤ 43:​4-7፤ 45:​1-5) በተመሳሳይም በመጀመሪያው መቶ ዘመን የነበሩት ዕብራውያን ክርስቲያኖች ለጳውሎስ ምክር አዎንታዊ ምላሽ ሰጥተው መሆን አለበት። ምክንያቱም በ66 እዘአ የሮማ ሠራዊት በኢየሩሳሌም ላይ ጥቃት መሰንዘር ከጀመረ በኋላ ባልታወቀ ምክንያት ወደ ኋላ ሲያፈገፍግ በወቅቱ የነበሩት ክርስቲያኖች ኢየሱስ ወደ ተራራ ስለመሸሽ የሰጠውን ማስጠንቀቂያ በታማኝነት ተግባራዊ አድርገዋል። (ሉቃስ 21:​20, 21) በሕይወት መኖራቸውን መቀጠል የቻሉት ታማኝ ሆነው በመገኘታቸው ነው። እኛም በተመሳሳይ መጨረሻው በሚመጣበት ጊዜ ታማኝ ሆነን ከተገኘን በሕይወት መኖራችንን እንቀጥላለን። ከአሁኑ እምነታችንን እንድናጠነክር የሚያበረታታ እንዴት ያለ ግሩም ሐሳብ ነው!

  • ከሚያምኑት ወገን እንሁን
    መጠበቂያ ግንብ—1999 | ታኅሣሥ 15
    • a ጳውሎስ የጠቀሰው በሰፕቱጀንት መሠረት “ማንም ወደ ኋላ ቢያፈገፍግ ነፍሴ በእሱ ደስ አይላትም” የሚል ሐረግ የሚጨምረውን ዕንባቆም 2:​4ን ነበር። ይህ አገላለጽ አሁን በእጅ ባሉ የብራና ዕብራይስጥ ጽሑፎች ውስጥ በአንዳቸውም ላይ አይገኝም። አንዳንዶች ሰፕቱጀንት የተገለበጠው አሁን በእጅ በማይገኙ በጣም ጥንታዊ የብራና ጽሑፎች ላይ ነው የሚል አስተያየት ይሰጣሉ። ያም ሆነ ይህ ጳውሎስ በመንፈስ ቅዱስ አነሳሽነት ይህን ጥቅስ በመልእክቱ ውስጥ ጨምሮታል። ስለዚህ ይህ ሐሳብ መለኮታዊ ድጋፍ አለው ማለት ነው።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ