-
በይሖዋ በመታመን በሕይወት ኑሩ!መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2018 | ኅዳር
-
-
17. የዕንባቆም መጽሐፍ ምን ማረጋገጫ ይሰጠናል?
17 የዕንባቆም መጽሐፍ በመጨረሻዎቹ ቀናት ውስጥ ለሚኖሩ ሰዎች ሁሉ ትልቅ ትምህርት ይዟል። ይሖዋ በእሱ ላይ እምነት ላላቸው ጻድቃን በሙሉ የዘላለም ሕይወት የማግኘት ተስፋ ሰጥቷቸዋል። እንግዲያው በማንኛውም ዓይነት መከራ ወይም ችግር ውስጥ ብንሆን ምንጊዜም በአምላክ ላይ ጠንካራ እምነት ይኑረን። ይሖዋ፣ እንደሚደግፈንና እንደሚያድነን የሚገልጽ ማረጋገጫ በዕንባቆም አማካኝነት ሰጥቶናል። በተጨማሪም በእሱ እንድንተማመንና የወሰነውን ጊዜ በትዕግሥት እንድንጠብቅ በደግነት ጠይቆናል፤ በዚያን ጊዜ የአምላክ መንግሥት መላዋ ምድር ደስተኛና ገር በሆኑ የይሖዋ አገልጋዮች እንድትሞላ ያደርጋል።—ማቴ. 5:5፤ ዕብ. 10:36-39
-