-
አዳኛችን በሆነው አምላክ ደስ ይበላችሁመጠበቂያ ግንብ—2000 | የካቲት 1
-
-
14-16. በዕንባቆም 3:14, 15 መሠረት የይሖዋ ሕዝቦችና ጠላቶቻቸው ምን ይደርስባቸዋል?
14 በአርማጌዶን ጦርነት የይሖዋን “ቅቡዕ” ለማጥፋት የሚሞክሩ ሁሉ በትልቅ ግራ መጋባት ውስጥ ይወድቃሉ። በዕንባቆም 3:14, 15 መሠረት ነቢዩ ለአምላክ እንዲህ ይላል:- “የአለቆችን ራስ በገዛ በትራቸው ወጋህ፤ እኔን ይበትኑ ዘንድ እንደ ዐውሎ ነፋስ መጡ፤ ችግረኛውን [“የተጠቃውን፣” NW ] በስውር ለመዋጥ ደስታቸው ነው። ፈረሶችህን በባሕር፣ በብዙ ውኆችም ላይ አስረገጥህ።”
-
-
አዳኛችን በሆነው አምላክ ደስ ይበላችሁመጠበቂያ ግንብ—2000 | የካቲት 1
-
-
16 ይሁን እንጂ በቅርቡ የሚከናወን ተጨማሪ ነገር አለ። ይሖዋ ከሰብዓውያን የበለጠ ኃይል ባላቸው መንፈሳዊ ኃይሎች በመጠቀም በጠላቶቹ ላይ የሚያደርሰውን ጥፋት ወደ ፍጻሜ ያመጣል። በኢየሱስ ክርስቶስ በሚመሩት የሰማያዊ ጭፍሮቹ “ፈረሶች” ‘በባሕሩና በብዙ ወኆች’ ላይ ማለትም ተነዋዋጭ በሆኑት ሰብዓውያን ጠላቶቹ ላይ በድል አድራጊነት ይዘምታል። (ራእይ 19:11-21) በዚያ ጊዜ ክፉዎች ከምድር ላይ ይወገዳሉ። እንዴት ያለ ታላቅ የመለኮታዊ ኃይልና ፍትሕ መግለጫ ነው!
-