የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • አዳኛችን በሆነው አምላክ ደስ ይበላችሁ
    መጠበቂያ ግንብ—2000 | የካቲት 1
    • 18. ዕንባቆም መከራ እንደሚመጣ ቢጠብቅም ምን ዓይነት ዝንባሌ ነበረው?

      18 ጦርነት በድል አድራጊዎቹ ላይ ሳይቀር ችግርና መከራ ያስከትላል። የምግብ እጥረት ሊያጋጥም፣ ንብረት ሊወድም ይችላል። የኑሮ ደረጃ ዝቅ ሊል ይችላል። እንዲህ ያለው ሁኔታ በእኛ ላይ ቢደርስ ምን ይሰማናል? ዕንባቆም እንደሚከተለው በማለት ጥሩ ምሳሌ የሚሆን ዝንባሌ አሳይቷል:- “ምንም እንኳ በለስም ባታፈራ፣ በወይንም ሐረግ ፍሬ ባይገኝ፣ የወይራ ሥራ ቢጎድል፣ እርሾችም መብልን ባይሰጡ፣ በጎች ከበረቱ ቢጠፉ፣ ላሞችም በጋጡ ውስጥ ባይገኙ፣ እኔ ግን በእግዚአብሔር ደስ ይለኛል። በመድኃኒቴ አምላክ ሐሤት አደርጋለሁ።” (ዕንባቆም 3:​17, 18) ዕንባቆም መከራ፣ ምናልባትም ረሐብ እንደሚደርስ ጠብቋል። ቢሆንም መዳን በሚያገኝበት በይሖዋ መደሰቱን አላቆመም።

  • አዳኛችን በሆነው አምላክ ደስ ይበላችሁ
    መጠበቂያ ግንብ—2000 | የካቲት 1
    • 20. ጊዜያዊ መከራ ቢኖርብንም ቁርጥ ውሳኔያችን ምን ለማድረግ መሆን ይኖርበታል?

      20 ስለዚህ ምንም ዓይነት ጊዜያዊ መከራ ቢደርስብን በይሖዋ የማዳን ኃይል ያለንን እምነት አናጣም። በአፍሪካ፣ በምሥራቅ አውሮፓና በሌሎች አገሮች የሚኖሩ ብዙ ወንድሞቻችን የሚኖሩት በከባድ መከራ ውስጥ ቢሆንም ‘በይሖዋ መደሰታቸውን አላቆሙም።’ እኛም እንደነርሱ ማድረጋችንን አናቁም። ‘የኃይላችን’ ምንጭ ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንደሆነ አስታውስ። (ዕንባቆም 3:​19) ፈጽሞ አይተወንም። አርማጌዶን መምጣቱ አይቀርም፣ አምላክ ቃል የገባለት አዲስ ዓለም ደግሞ ተከትሎት እንደሚመጣ የተረጋገጠ ነው። (2 ጴጥሮስ 3:​13) በዚያ ጊዜ “ውኃ ባሕርን እንደሚከድን ምድር የእግዚአብሔርን ክብር በማወቅ ትሞላለች።” (ዕንባቆም 2:​14) ያ አስደናቂ ጊዜ እስኪደርስ ግን የዕንባቆምን አርዓያ እንከተል። ‘አዳኛችን በሆነው አምላክ በይሖዋ መደሰታችንን እንቀጥል።’

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ